በመቶዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ስደተኞችን ይዛ ወደ ላምቤዱሳ ደሴት በማቅናት ላይ የነበረች አንዲት ጀልባ እሳት ተቀስቅሶባት በመስጠሟ 92 ሰዎች ሞቱ ።
በጀልባዋ ላይ የተቀሰቀሰውን እሳት ለማምለጥ ስደተኞቹ ወደ ባህር መዝለላቸውና ጀልባዋም መስጠሟ ተነግሯል ። 150 የሚጠጉ ሰዎችን ህይወት ማትረፍ እንደተቻለ ፖሊስ አስታውቋል ።
200 የሚሆኑ ስደቶች ግን እስካሁን የደረሱበት ያልታወቀ ሲሆን ፥ የሟቾች ቁጥርም አሁን ከተጠቀሰው በላይ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል ።
በአሁኑ ወቅት የሜዲትራኒያን ባህር የተረጋጋ ሁኔታ ያለው በመሆኑ በየእለቱ አፍሪካውያን ስደተኞችን የያዙ ጀልባዎች በደቡባዊ የጣሊያን የባህር ዳርቻ እንደሚደርሱ ነው የሚነገረው ።
ሆኖም ስደተኞቹን የሚጭኑት ጀልባዎች ጤንነት አሳሳቢ በመሆኑ አሳዛኝ ክስተት በአከባቢው እየተደጋገመ መጥቷል ።
የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ደርጅት እንደሚለው በዚያ አከባቢ ችግር ባለባቸው ጀልባዎች በመሰፈራቸው በየዓመቱ በተንሹ 1 ሺህ 500 የሚሆኑ ስደተኞች ባህር ላይ የቀራሉ ።
ምንጭ ፦ ቢቢሲ
No comments:
Post a Comment