Wednesday, October 30, 2013

ፉዓድ ኢብራሂም ዳግም ዋሊያዎቹን ተቀላቀለ


የቀድሞው የአሜሪካ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ተጨዋችና ኢትዮጵያዊ የዘር ሀረግ ያለው ፉዓድ ኢብራሂም ዛሬ ዋሊያዎቹን ተቀላቀለ፡፡
ፉዓድ ኢብራሂም በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዋሊያዎቹ ከታንዛኒያ ባደረጉት ጨዋታ ለዋሊያዎቹ ጎል ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡
ዋሊያዎቹ ከናይጄሪያ ጋር ባደረጉት የመጨረሻ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ጨዋታ ከእረፍት መልስ የዋሊያዎቹን መለያ ለብሶ ተጫውቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት በፊንላድ በሚገኘው ኤሲ ካጃኒ ክለብ የሚጫወተው ፉዓድ ፥ በዚህ ዓመት ብቻ በ10 ጨዋታዎች 3 ጎሎችን ለክለቡ በስሙ አስቆጥሯል፡፡
ፉዓድ ኢብራሂም ከወሳኙ የናይጀሪያ ጨዋታ በፊት ዋሊያዎቹ ከቡርኪናፋሶ ለሚኖራቸው የወዳጅነት ጨዋታ ፥  የዋሊዎቹን መለያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያጠልቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የፊት መስመር ተጨዋቹ ፉዓድ ለዋሊያዎቹ ዳግም መጠራቱ የፊት መስመር ተጨዋቾችን አማራጭ ለማስፋት ይረዳል ተብሏል፡፡

ምንጭ:  ኢሬቴድ

No comments:

Post a Comment