Friday, October 18, 2013

ሂውማን ራይትስ ወች – የፖለቲካ እስረኞች እንዲሰቃዩ ይደረጋል (የድምጽ ስርጭት )


የድምጽ ስክሪፕት
የቀድሞ የፖለቲካ እስረኞች ጋር የተደረገ ቃለ-መጠይቅ፤ ከመስከረም 24 – 28፣ 2006ዓ.ም ባለው ግዜ ውስጥ የተቀረጸ፡፡(ሁሉም መረጃ ያለምንም ገደብ ሊሰራጭ የሚችል ነው)
1. ላቲሽያ ባዴር የሂውማን ራይትስ ወች ሪሰርቸር ፡ ማዕከላዊ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ መሐል አዲስ አበባ ላይ የሚገኝ አንዱ ዋና የፖሊስ ጣቢያ ነው፡፡ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በማዕከላዊ የሚገኙ አብዛኞቹ መርማሪዎች ህጋዊ የምርመራ መንገድ ሳይሆን የሚጠቀሙት ከእስረኞቹ መረጃ ለማውጣጣት ብሎም በግድ ለማሳመን እና ቃል ለመቀበል ጎጂ መንገድ ነው የሚከተሉት፤ አብዛኞቹ ጉዳዮችም እውነታነት የላቸውም፡፡ በማዕከላዊ ቀድሞ የታሰሩ እና በተለይ ደግሞ በሁለቱ የማቆያ ክፍሎች የነበሩ ያናገርናቸው የቀድሞ እስረኞች አስከፊ ሁኔታ እና አያያዝ እንደተደረገባቸው ገልጸዋል፤ እስረኞቹ እንደነገሩን እና እንዳብራሩት በምርመራ ወቅት ተደብድበዋል፣ በጥፊ ተመተዋል እንዲሁም ጎጂ ቃላቶች ተሰንዝሮባቸዋል፡፡]

Read more in PDF Amharic

የቀድሞ የፖለቲካ እስረኞች ጋር የተደረገ ቃለ-መጠይቅ – ድምጽ

No comments:

Post a Comment