ዛሬ ሐዋሳ ፍርድ ቤት ለመቅረብ ትናንት ምሽት ወደ ስፍራው ያመሩት የኢትዩ ምህዳር ሶስት ጋዜጠኞች ማለዳ ላይ በሲዳማ ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸውን ይመለከቱ የነበሩት ዳኛ ለከሰዓት 9፡00 ሰዓት እንዲቀርቡ ይነግሯቸዋል፡፡ጋዜጠኞቹ ጊዜውን በከንቱ ላለማባከን በማሰብ በሐዋሳ ዜና ፍለጋ ይሰማራሉ፡፡
በባጃጅ ተጭነው ወደ ሚያውቁት አንድ የሞያ አጋራቸው ማቅናት እንደጀመሩ ከፊት ለፊታቸው አንድ ሞተር ሳይክል እየከነፈ ይመጣል፡፡የባጃጁ አሽከርካሪ ሶስቱን ጋዜጠኞች ውስጥ ትቶ ሲያመልጥ ባጃጇ እንዳልነበረች ትሆናለች፡፡ ጋዜጠኞቹም ሁለቱ መጠነኛ አንደኛው ግን (ሚልዩን ደግነው )ከወገቡ በታች ክፉኛ በመጉዳቱ ለመንቀሳቀስ መቸገሩን ከደቂቃዎች በፊት በስልክ ያናገርኩት ጋዜጠኛ ጌታቸው ነግሮኛል፡፡
ጋዜጠኞቹ በአሁኑ ሰዓት በሐዋሳ የህክምና እርዳታ ለማግኘት ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ነው፡፡የምህዳር ባልደረቦች በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተፈጸመ ስለ ተባለ ሙስና በሰሩት ዘገባ ምክንያት ወደ ክልል ተወስደው ክስ የተመሰረተባቸው መሆኑ አይዘነጋም፡፡
No comments:
Post a Comment