ሻቢያን የሚያውቀው ወያኔ እንጂ ተቃዋሚዎች አይደለም ሁለቱም እንደፍጥርጥራቸው።እራሳችሁ ይለያዩ ወዳጅ ሁለቱ ናቸው ተቃዋሚው ላይ አታላኩተቃዋሚው ዝምድናም እንደሌለው ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቃል የሁለቱን ስራ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሃገርቤት ተቃዋሚዎች የሚያሰሟቸው ጥያቄዎች የራሳቸው እንዳልሆኑእና እንደ እርሳቸው አባባል በተለያዩ ሃገሮች ያሉ ሌሎች ሃይሎች የሰጧቸው የቤት ስራዎችናቸው፡፡
በዚህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር፤ ለምሳሌ ሰማያዊ ፓርቲ እና አንድነት ፓርቲ የታሰሩጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች እንዲፈቱ፣ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንዳይገባ፣የኑሮ ውድነት የመሳሰሉት ጉዳዮች እንዲሻሻሉ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች መልስ አያገኙምማለት ነው፡፡ በውጭ ካሉ የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ በተመለከተ ግንቦት ሰባትየሚያደርገውን እንቅስቃሴ ባጭሩ ህልም ነው፤ ማለም ይችላሉ ያሉ ሲሆን በፓርቲያቸውውስጥ መሰንጠቅ ስለመኖሩም ለተነሳው ጥያቄ ምኞት ነው መመኘት ትችላላችሁ የሚልድፍን ያለ መልስ ሰጥተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስተር ሀይሌ ነገሮች እያዣለጣቸው ነው ግን ***አንሰማም!!!***
ዶክተር ብርሃኑ ነጋና ግንቦት 7 ስራቸውን እየሰሩ ነው ምንም ጥርጥር የለኝም ! ሰርጎ ገቦችወሬ ማናፈሱን ይቀጥሉ ግን አንሰማም!!!
ተቃዋሚ የሚባሉት ሲያዳልጣቸው ይታያሉ።እዚ ሲባሉ እዛ፣እዛ ሲባሉ እዚ ጉድ ነውዘንድሮ።
ለማንኛው ሀገር ቤት ሆነው ተቃዋሚ ነን እያሉ የሚቀየሱትንም አንሰማም!
በውጪ ያሉትንም እንደዛው እየተለጠፉ የሚቀባጥሩትንም አንሰማም!
ፍትህ አጣን ብለው ከሀገር ቤት መፃፍ መናገር አልቻንም ብለው ተሰደው የወያኔ ጀሌሆነው የህዝብ አስተሳሰብ፣አመለካከት የሚያስቱትንም አንሰማም!
ጋዜጠኛዎች በነጻነት ያለ ጣልቃ ገብነት እንዲሰሩ እንጂ ትግሉን የሚመሩት ተቃዋሚዎችየሚዲያ እድል ባስፈለጋቸው ጊዜ እዳያገኙ አይደለም።
ከኢህአዴግ ጋር የስጋ ዝምድና አላቸው እየተባሉ የሚጠረጠሩ ወዳጆቻችን መስለውየተቃዋሚውን ድርጅቶች ለመከፋፈል ሴራ የሚዶልቱ ጀሌዎች አይሳካላችሁም።አንሰማም!
ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ከአንዳች ሀይል ኢህአዴግን ለመገዳደሪያ የሚሆን ገንዘብ እንዳገኙየሚያሰማ ድምፅ አጋርተውናል፡፡ ችግሩ ግን ይህ ገንዘብ ከየት እንደተገኘ እርስ በርሳቸውስምምነት ላይ አልደረሱም፡፡ አንዳቸው ከኤርትራ ነው ሲሉ ሌላኛው ደግሞ ከግብፅ ነውይላሉ፡፡ በደንብ ጆሮ ጣል ብናደርግ ከኢህአዴግ መንግስት ነው የሚልም አይጠፋም፡፡ከምንም ይገኝ ከምንም መጥቀሙ ነው የሚፈለገው።
ደግሞ ምንድነው ማናፈስ እንዴ ወያኔ ለግንቦት 7 ወዳጁ ነው እንዴ?
አንድ ሰሞን እኮ ወዳጆቻችን ያጋሩን ድምፅ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ከሆነ ቦታ የተገኘውን ብር፤ለእንትን ይሄን ያህል፣ ለእንትና ይሄን ያህል እያሉ ሲናገሩ ያስደምጣል፡፡ በዚህ ላይያስደነቀኝን ልናገር እና እመለሳለሁ ቆይ አዲስ መስመር ላይ እንገናኝ፡፡
ዶክተሩ የሆነውን ብር እዛው ለመከላከያ እና ደህንነቱ የተበጀተ ነው፤ ሲሉ ሰማናቸው፡፡ይሄኔ በተለይ በኢህአዴግዬ ፍቅር የተለከፈ ሰው ክው!!! ማለቱ አይቀርም፡፡ ደህነነት እናመከላከያችን ከመንግስት ከሚመደብለት በጀት ውጪ በግንቦት 7 ደግሞ ሌላ በጀት አለውማለት ነው፡፡ ይቺን ነው መፍራት፤ ዶክተሩ ስራቸውን ቀጥ ለጥ አድርገው እየሰሩ ነውማለት ነው፡፡
ታድያ ለዚህ ነዋ የኢህአዴግዬ ገመናዋ ሁሉ ቀድሞ አደባባይ የሚሰጣው!!! እኔ ልሰጣ …ልበል ወይስ አልበል! (በቅንፍም ይቅርብኝ እነ እንትና ሳይሉ እኔ ቀድሜ ልሰጣ… ብልእነሱን ማሳጣት ሆንብኛል!) ከቅንፍ ስንወጣም ለኢሳትም የሆነ ብር ይሰጣል ሲሉ ዶክተሩመናገራቸውን አዳመጥኩ፡፡ በእውነት ዶክተርዬ የተባረኩ ኖት፡፡ … እንዴ… በአሁኑ ጊዜማን እንደዚህ ያደርጋል… የምር እኮ ኢሳትን ሁሉም መርዳት አለበት፡፡ ግንቦት 7 ከረዳውበጣም ጥሩ ጅምር ነው፡፡ እንኳን ሌላ ቀርቶ ግንቦት 20 ም ራሷ ኢሳትን መርዳት አለባት፡፡እንዴ ኢቲቪ የማይሰራውን በሙሉ የሚሰራው ኢሳት አይደለ እንዴ…! ታድያ እንዲህእንዲተጋገዙ ሁሉም የአቅሙን ቢያዋጣ ምን ችግር አለበት!
ወደ ዋናው መስመር ስመለስ ወዳጆቻችን "ፈልፍለው" ይፋ ባደረጉት መረጃ ዶክተሩ ለካስአልተኙም ብለናል፡፡ እና ይበርቱ ልንላቸው ይገባል፡፡
ከዚህ በፊት ገንዘቡ ከግብጽ ነው ሲባል ነበር፤
ግብፅ የምር ለኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ገንዘብ የምትረዳ ከሆነ ተጃጅላለች ማለት ነው፡፡ ሌላቀርቶ ኢህአዴግ እንኳ ያንን ሁላ አድርጋለት አልተመለሰላትም፡፡ በእውኑ ሌሎቹማከኢህአዴግ የበለጠ ለሀገራቸው ተቆርቋሪ አይደሉምን…!
ገንዘቡ ከኤርትራ ነው፤
ወይ…. ኤርትራ….!!! አሁን ማን ይሙት ኤርትራዬ ከራሷ አልፋ ለሌላ ሰው ይሄንንያክል ብር መስጠት ትችላለች…! ይሄንን ሃሳብ የሰነዘሩ ሰዎች በእርግጠኝነት ኤርትራዊያንናቸው እንዳንል እነሱንም እኛ መለየት አንችልም እራሳቸው ይለያዩ እንጂ፡፡
አላማውም ወያኔን በሚገባው ቋንቋ መልስ መስጠት ነው።
***የትም ፍጪው ኢህአዴግን አስወጪው***
ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ግንቦት 7 የሚባል ተቃዋሚ ፓርቲ መስርተው ሁለገብ በሆነ ዘዴኢህአዴግን ወግድ እለዋለሁ ብለውናል፡፡ ግንቦት 7 ይህ ከሆነለት የዘመናት ብሶትየወለዳቸው ሁሉ ተሰባሰበው ዋንጫ እንደበላ ሰው "የእርግብ አሞራ" "የእርግብአሞራ""የእርግብ አሞራ"እያሉ የሚጨፍሩለት ደስታ የሚሆን ይመስለኛል፡፡ ታድያ ለዚህአላማ ገንዘብ ከየትስ ቢያመጡ እኛ ምን አገባን…!?
ምነው እነሱ እረሱት እንዴ ከየት እየተረዱ አዲስ አበባ እንደገቡ???
ለማንኛውም አንሰማችሁም!!!!!!!!!!
ከሰብኣዊ
No comments:
Post a Comment