Sunday, November 3, 2013

ወይዘሮ አዜብ መስፍን የፓርቲ መልቀቂያ አቀረቡ:



ወይዘሮ አዜብ መስፍን የፓርቲ መልቀቂያ አቀረቡ: ተቀባይነት አላገኘም::#Ethiopia
ሕወሓት ለወይዘሮ አዜብ ስልጣን በመስጠት በስልት ልታጠምዳቸው ነው::#TPLF

"ለእኔ ስም የሚያወጡልኝ ተቃዋሚዎች ሳይሆኑ የሕወሓት ሹሞች ናቸው::" የሚሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት የሆኑት እና የሙስናዋ ወይዘሮ በመባል የሚታወቁት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ለፓርቲያቸው ያቀረቡት የፖ
ለቲካ በቃኝ ማመልከቻ ተቀባይነት ማጣቱ ሲገለጽ የሕወሓት ከፍተኛ ሰዎች ወይዘሮ አዜብን ለማጥመድ በሚያስችል ስልጣን ላይ ሊያስቀምቷቸው እንዳሰቡ ምንጮቹ ጠቁመዋል::የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው በወይዘሮ አዜባ ጋር በዋዛ አንላቀቅም በማለት ቂም በቀላቸውን ሊወጡባቸው ይችላሉ የሚል ግምቶች በሕወሓት አከባቢ እየተነገሩ ነው::

ለወይዘሮ አዜብ የታሰበው ስልጣን የትኛው እንደሆነ ባይታወቅም በስልት ከፖለቲካ ለማፈግፈግ እና ለመልቀቅ ከአገር ለመውጣት እንደማይቻል ተነግሯቸዋል:: ወይዘሮ
አዜብ በድጋሚ ማመልከቻ ማቅረባቸው እንደማይቀር የጠቆሙት ምንጮቹ ምንኛውም ስልጣን ቢሰጣቸው በአዲስ አበባ መስተዳደር ምክር ቤት ውስጥ አባል ሆነው የመቀጠል ፍላጎት እንዳሌላቸው በግልጽ ተናግረዋል::ባልቤቴ ከሞተ በኋላ በሕወሓት ተገፍቻለሁ የሚሉት ወይዘሮ አዜብ ምንም ነገር ሊመቻቸው እንዳልቻለ እና ስለ እሳቸው ውስጥ ለውስጥ የሚነዙ ፕሮፓጋንዳዎች እያበሳጯቸው እንደሆነ ተናግረዋል በተጨማሪም ለእኔ ስም የሚያወጡልኝ ተቃዋሚዎች ሳይሆኑ የሕወሓት ሹሞች ናቸው ሲሉ አማረዋል::ምንሊክ ሳልሳዊ.

No comments:

Post a Comment