Thursday, November 28, 2013

በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች በወገኖቻችን ስም በእጅ አዙር ገንዘብ ማሰባሰብ መጀመራቸው እየተነገረ ነው ።

በሪያድ መለዝ አካባቢ የሚገኝ፡አሚራ ኑራ ዩንቨርስቲ ግቢ ሜዳ ላይ ያለዳስ ብርድ እና ጸሃይ የሚፈራረቅባቸው ከ 7 ሺሕ የሚበልጡ ወገኖቻችን በመግብ ወሃ እና የመጸዳጃ ቦታ እጦት እየተሰቃዩ ነው ። የተጠቀሰው መጠለያ ውስጥ ያሉት ወገኖቻችን አብዛኛዎቹ ሴቶች ህጻናት እና አረጋውያን እንደሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ።


* በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች በወገኖቻችን ስም በእጅ አዙር ገንዘብ ማሰባሰብ መጀመራቸው እየተነገረ ነው ። በተለይ በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ የኮሚኒቲ ት/ቤት አንዳንድ መምህራኖችን ለዚህ ድብቅ አጀንዳዎቻው ማስፈጸሚያ በማድረግ ላይ መሆናቸው እይተሰማ ነው ። ለዚህም ሰሞኑንን ት/ቤቱ ለወገኖቻችን መርጃ የሚውል ገንዘብ ከወላጆች እና ከተማሪዎች ለመሰብሰብ እቅድ መያዙን ከት/ቤቱ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ ።
* በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እንደተቋቋመ የሚነገርለት ይህ የእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚተ ቀደም ሲል በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ውስጥ ለሚገኙ 12 ነስፈስ ጡሮችን ጨምሮ ከ 200 የሚበልጡ ወገኖቻችን ከስቃይ እና መከራ ለመታደግ በሚል « የአይሮፕላን ትኬት መግዣ በሚል ሽፋን ቀደም ብሎ 1 መቶሺህ ሪያል አሊያም ግማሽ፡ሚልዮን ብር መሰብሰቡን የሚናገሩ ውስጥ አውቂ ምንጮች ግር ግር ለሌባ ያመቻል እንዲሉ የመንፉሃውን የሁከት ተከትሎ ዲፕሎማቱ እህቶቻችን ወደ አልታወቀ ግዜያዊ መጠለያ በመብተን የተጠቀሰውን ገንዘብ ለምን እንዳዋሉት እንደማይታወቅ ምንጮች ከሪያድ ገልጸዋል። ።
* ሪያድ ውስጥ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በአሰሪዎቻቸው « በከፊሎቻቸው» የመኖሪያ ፈቃዱ በመስረዙ ለህገወጥ፡ነት የመዳረጋቸው ጉዳይ እያነጋገረ ነው ።
*ከሪያዱ የመንፉሃው ከሁከት በሃላ ጸጥ ረጭ እንዳለች የሚነገርላት የሃበሾቹ መንደር ዛሬ በአያሌ ወገኖቻችን ላይ ፊቷን ያዞረች ትመስላለች ! የተለያዩ ንግድ ስራዎች ላይ ተሰማርተው የኖሩ የነበሩ ወገኖቻችን በአጋጣሚ በተፈጥረው ሁከት በሚልዮን የሚቆጠር ገዘባቻቸውን ማጣታቸውን አሊያም ባለ እዳ መሆናቸው እይተነገረ ነው ። በዝች የሃበሾች መንደር ከሚገኙ ጥቂት ሱቆች ውስጥ የፈጅር ሱቅ ባለቤት አቶ መሃመድ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ትላንት ቤታቸው ውስጥ እራሳቸውን ሰቅለው ተገኝጠዋል። በተያያዘ ዜና የአምባሳል ንግድ ቤት ባለቤት እሳካሁን ያለበት ባታ እንደማይታወቅ መረጃዎች ይገልጻሉ ።
* አንዳንድ ቪዛ ነጋዴዎች « የኤጀንሲ ባለበቤቶች » ኢትዮጵያውያኑን ከሃገር በማስመጣቱ ረገድ በአቋራጭ ወደ ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያኑንን እይሰገቡ መሆኑ እይተነገረ ነው ።
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

No comments:

Post a Comment