ጥቁር ሽብር ወያኔ ቁምጣ የለበሰ ደርግ ነው ! እመኑኝ በየትኛውም የታሪክ ገጠመኝ የሳወዲ መንግስት የዚህ አይነት ድፍረት ያውም በአደባባይ በዜጎቻችን ላይ አሳይቶ አያውቅም ፡፡ ነገሮችን ተመልሰን ከተመለከትን ይህ ግፍና በደል የእኛው ባለስልጣናት ሳውዲወችን አደፋፍረው ያስፈፀሙት ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ሁለት ፖለቲካዊ ምክንያቶች አሉት ፡፡ የመጀመሪያው ፡- የወያኔ ባለስልጣናት በሳውዲ የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያንን ቦንድ እንዲገዙ በሰበሰቡበት ወቅት ተደጋጋሚ ተቃውሞ ደርሶባቸው እንደነበር የሚታወቅ ነው ፡፡ ይህም ድምፃችን ይሰማ ባሉ ሙስሊሞች ላይ በሃገር ውስጥ የሚደርሰው በደል ይቁም ለጥያቂያቸውም አጥጋቢ መልስ ይሰጥ በሚል ምክንያት ነበር ፡፡ ቂመኛው መንግስታችን ይህን እንደበደል በመቁጠር በእጅ አዙር ዜጎቻችንን እያስጋዘ ይገኛል ፡፡ ለዚህ በደሉ ሽፋን እንዲሆነው በቅርቡ በተለያዩ ሚዲያወቹ አረብ አገራት ላይ ያተኮሩ ወሬወችን ሲነዛ ቆይቷል ፡፡ የሳዲ መንግስት በሰጠው የጊዤ ገደብ የሚያስፈልጋቸውን መረጃ ሊጠይቁ ወደ ‹‹ኢትዮጲያ ኤምባሲ ›› የሄዱ ሚስኪን ለፍቶ አደሮች ቦንድ ግዙ እየተባሉ ሲመላለሱ የጊዜ ገደቡ አልቆላቸዋል ፡፡ ሁለተኛው ምክንያቱ ፡- አገር ውስጥ ያለው ‹‹የድምፃችን ይሰማ ›› እንቅስቃሴ አረብ አገራት ባሉ ኢትዮጲያዊያን የገንዘብ ድጋፍ ያገኛል በሚል ፍርሃት ነው ፡፡ፍርሃት ብቻ ሳይሆን በግልፅም በወቲቪ (የ ወያኔ ቴሌቪዥን ) በተደጋጋሚ ተናግሮታል ፡፡ በመሆኑም ይህን የራሱን ስጋት ለማስታገስና መመለስ ያልቻለውን የማይችለውንም የመብት ጥያቄ ለማፈን የገቢ ምንጭ ናቸው ያላቸውን በአረብ አገር የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያንን ሰላም ደህንነትና ሂወት ጭምር በእጅ አዙር እየነጠቀ ነው ፡፡ (እዚህ ላይ ሳውዲወች የቴውድሮስ አድሃኖም ስምምነት አለበት ማለታቸውን እንዳንዘነጋ) አሁን ከወደኪዌት እንደምንሰማው ደግሞ ከስራቸው በገፍ የተፈናቀሉ ኢትዮጲያዊያን ሰልፍ እንወጣለን አልያም ስራ ይሰጠን እያሉ ነው ፡፡ እኒህ ኢትዮጲያዊያን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከስራቸው የተፈናቀሉ ናቸው ፡፡
ወያኔ እና የወያኔ ጭፍን ደጋፊወች ማወቅ ያለባችሁ ጉዳይ ድህነት ትግልን ያባብሳል እንጅ አያዳፍንም ‹‹አፈር እየቃምን ድንጋይ እየቆረጠምን ደርግን ጣልነው ›› እንደምትሉት ይህም ህዝብ ሆነ ብላችሁ የምትጭኑበትን ድህነትና እንግልት ተቋቁሞ ድል ማድረጉ የማይቀር ነው ፡፡ ታውቁታላችሁ እናውቀዋለን ! ወያኔ ማለት ቁምጣ ለብሶ የመጣ ደርግ ነው ፡፡ ደርግ ቀይ ሽብር ብሎ ህዝብ ፈጀ ፤ ወያኔ በተዳፈነና የህዝብን መብት ፣ ነፃነትና ሂወት ጭምር በጋረደ ጨለማ አገዛዙ ጥቁር ሽብሩን አወጀ፡፡ እነሆ አገራችን በጥቁር ሽብር ውስጥ ወድቃለች ንጋትን ናፍቆ የተሰደደ ህዝብ በገፍ እየተሰቃየ ነው ፡፡
No comments:
Post a Comment