Sunday, October 13, 2013

ETV በቦሌ አዲስ አበባ የፈንጂ ፍንዳታ መድረሱን ዘገበ


ዘገባው የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት የተቀነባበረ ይሁን አይሁን በገለልተኛ ወገን አልተረጋገጠ የETV ዘገባ እንደወረደ አቅርቤዋለው
እሁድ 3 2006 ዓም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ የቤት ቁጥር 2333 ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ሁለት ግለሰቦች ተከራይተው በሚኖሩበት ቤት ውስጥ የፈንጂ ፍንዳታ መድረሱን የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት እና የፌደራል ፖሊስ የጋራ ጸረ ሽብር ሀይል ገለጸ፡፡
በፈንጂ ፍንዳታው ሁለቱ ግለሰቦች ህይወታቸው አልፏል፡፡

ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን የገለጸው ግብረሀይሉ በምርመራ የደረሰበትን ውጤትም በቅርቡ ለህዝብ እንደሚያሳውቅ አመልክቷል፡፡
ህብረተሰቡ ቤት እና መኪናዎችን በሚያከራይበት ወቅት የተከራዮችን ማንነት ከማወቁም ባሻገር ለፖሊስ እና ለጸጥታ ሀይሎች ማሳወቅ እንዳለበት ግብረሀይሉ አሳስቧል፡

No comments:

Post a Comment