Tuesday, October 8, 2013

በእሁዱ ጨዋታ 3 ታዋቂ የናይጄርያ ተጫዋቾች አይሰለፉም


(EMF) ወደ አለም ዋንጫ ግጥሚያ ለሚወስደው ወሳኝ ፍልሚያ፤ የኢትዮጵያ እና የናይጄርያ ቡድኖች በመጪው እሁድ አዲስ አበባ ላይ ይጫወታሉ። በአንዳንድ የውጭ ድረ ገጾች ላይ፤ “ማን ሊያሸንፍ ይችላል?” የሚል የጥናት ናሙና (Poll) እየተደረገ ነው። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ናይጄርያን የማሸነፍ እድሏ 10 በመቶ መሆኑን ከዚህ ጥናት መረዳት ተችሏል። በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንም ሆነ አሰልጣኙ የእሁዱን ጨዋታ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ በርግጠኝነት በመናገር ላይ ናቸው።

Ethiopia VS Nigeria

የኢትዮጵያዎቹ ጥቁር አንበሶች ከሁለት ሳምንት በፊት፤ የአካል ጥንካሬ ሲሰሩ ነበር። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ደግሞ በቴክኒክ ላይ አተኩረው ስልጠና ወስደዋል። በዚህ ሳምንት ደግሞ ሁለቱንም በማዋሃድ የአካል እና ቴክኒክ ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑን አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ተናግሯል። በንግግሩ መጨረሻም፤ “እኔ ብራዚል የምትባለው አገር ሄጄ አላቅም። ከነቡድኔ እዚያ መሄድ እፈልጋለሁ።” ብሏል። ተጫዋቾቹ በሙሉ በሚገርም ሞራል ውስጥ ናቸው፤ ሁሉም ናይጄርያን እንደሚያሸንፉ በርግጠኝነት ሲናገሩ ይሰማል።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ ነው እንግዲህ፤ ከናይጄርያ ደግሞ አሳዛኝ ዜና የተሰማው። ሶስት ታዋቂ ተጫዋቾቻቸው ከዚህ በፊት ቢጫ ካርድ በማየታቸው፤ በአዲሳባው ጨዋታ ላይ አይሰለፉም። ግብ አግቢያቸው ኢማኑኤል ኤምኒክ፣ ተከላካዮቹ ኤልደርሰን እና ጋድፍሬ ኦቦቦና በመጪው ጨዋታ ላይ አይሳተፉም። ይህ ለኢትዮጵያ ቡድን ጥሩ አጋጣሚን ሊፈጥር ይችላል። ስለ ናይጄርያ ቡድን ጥንካሬ ብዙ ሊባል ይቻላል። ካለፈው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ፤ ስለኢትዮጵያውያኑ ግን አንድ ትንሽ እና አስፈሪ ነገር ይባላል – “The giant killers”  እያሉ ይጠሯቸዋል። እናም የመጪው እሁድ ጨዋታ፤ የዳዊት እና የጎልያድ ያህል ትልቅ ልዩነት ያለው ቢሆንም፤ “The giant killers”  ሊያሸንፉ የሚችሉበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል። ለሁሉም ግን እስከ እሁድ ሞራል በመስጠት እና በጸሎት ጭምር እናስባቸው።
EMF

No comments:

Post a Comment