Saturday, October 12, 2013

የኢህአዲግ አፈና በሰማያዊ አመራሮች እና አባላት ላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል!!!


የኢህአዲግ አፈና በሰማያዊ አመራሮች እና አባላት ላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል!!!
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ዉስጥ ለሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ተከራይቶ የነበረዉን ቤት ከዛሬ ጥቅምት 1 2006 ጀምሮ ለመጠቀም
በሄዱበት ጊዜ የክፍለ ከተማዉ ፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታሁን አማረ ፤ የወረዳዉ አስተዳደር ሃላፊዎች ፤- የወረዳ 3 ስራ አስፈፃሚ አቶ አማረ ቤካ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አማረ አቡጤ ፤ መነን አካባቢ ፖሊሶች ፤ ፌደራል ፖሊሶች እና ሲቪል የለበሱ የደህንነት አካላት በጋራ በመሆን በማይመለከታቸዉ ጉዳይ የፓርቲዉን ከፍተኛ አመራሮች
1. ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት(ሊቀ መንበር)
2. አቶ ስለሺ ፈይሳ (ምክትል ሊቀመንበር)
3. አቶ ይድነቃቸዉ ከበደ (የህግ ጉዳይ ሃላፊ)
4. አቶ እንዳሻዉ እምሻዉ (የጽህፈት ቤት ሃላፊ)
5. አቶ በቃሉ አዳነ (ምክር ቤት አባል )
6. አቶ ዮናስ ከድር (የምክር ቤት አባል)
7. አቶ ብርሃኑ ተክለ-ያሬድ (አባል)
ወደ መነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እንገልፃለን፡፡አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ሰማያዊ ፓርቲ ተከራይቶት የነበረዉን ቤት ‘ለወሔነት’ ባርና ሬስቶራንት ለፔንሲዮን አገልግሎት እንዲሚጠቀምበት ቢሆንም የፔንሲዮኑ ባለቤት የሆኑት አቶ በላቸዉ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እና የወረዳ 3 አስተዳደር በግዴታ እንዲከራዩ የእያስገደዷቸዉ ሲሆን አቶ በላቸዉና የቤቱ ባለቤቶች እኛ ተገደን ነዉ ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በመነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቤቱን ለፓርቲ ጽ/ቤት እንዳይከራይ እየተከራከሩ ያሉት በአቶ ያለዉ እዉነቱ የጉለሌ ክፍለ ከተማ የህዝብ አደረጃጀት ሃላፊ የሚመሩ የመስተዳድሩ አካላት መሆናቸዉ በይበልጥ ለፓርቲዉ ጽ/ቤትነት ለመጠቀም እንዳንችል መንግስት እጁ እንዳለበት መገንዘብ ተችሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት በመነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር የነበሩት የፓርቲ አመራሮች ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መወሰዳቸዉን አሁን የደረሰን መረጃ ይገልፃል፡፡

No comments:

Post a Comment