ሰማያዊ ፓርቲ በተከራየው ቢሮ ምክንያት ከፖሊስ ጋር ወዝግብ ውስጥ መግባቱ የሚታወስ ሲሆን ተከራይ ነኝ ባዩ ግለሰብ «በሩ ላይ የሰቀልኩትን ባነር በጥሰውብኛል» ብሎ ኢንጂነሩ ላይ ክስ መስርቷል። ፖሊስም የሰማያዊን ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃልን ለማሰር እንቅስቃሴ የጀመረ መሆኑ ታውቋል። ኢ/ር ይልቃል ግን በቤተሰብ ጉዳይ ከአዲስ አበባ ውጪ መሆናቸው ተሰምቷል።
ይህበእንዲህ እንዳለ ሰማያዊ ፓርቲ የተከራየው ቢሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ፖሊስ ሕግን ጥሶ ፅ/ቤቱን መጀመሪያ ተከራይቼዋለው ለሚለው ግለሰብ እቃ እንዲያስገባና እንዲያስወጣ የፈቀደለት ሲሆን ዛሬ ጠዋትም እቃ ሲያስወጣና ሲያስገባ ታይቷል።

ኢንጂነር ይልቃል በወያኔ ፍረሃት በተጨናገፈውና አስደሳች በነበረው ሰልፍ ወቅት የወያኔው ጋዜጠኛ ለጠየቃቸው ጥያቄ «በቅርቡ ሴራ ጠምጥማችሁ ታስሩኛላችሁ፤ ግን ከትግላችን ልታቆሙን አትችሉም፤ እኛ ብንታሰርም የኢትዮጵያ ህዝብ ግን በቅርቡ ነፃነቱን ያውጃል» ማለታቸው አይዘነጋም።
The Voice Of Freedom
No comments:
Post a Comment