Sunday, June 30, 2013

ተመስገን ደሳለኝ ለማን ደስ ይበለው ብሎ ጠፋ!? (ከአቤ ቶኪቻው)

ተመስገን ደሳለኝ ለማን ደስ ይበለው ብሎ ጠፋ!?

ባለፈው ጊዜ አንድ ወዳጄ ጋር አዲሳባ ስልክ ደውዬ ሳናግረው በአካባቢው ከእርሱ ድምጽ ጎልቶ የሚሰማ የመኪና ጥሩንባ ሰማሁና ይሄ ሁሉ የመኪና ጥሩምባ ምንድነው… ብዬ ጠየኩት፡፡
ሃይለማሪያም ደሳለኝ እየገቡ ወይም እየወጡ ነው መሰለኝ መንገድ ተዘጋግቷል፡፡ አለኝ፡፡Journalist Temasegan Dasaleg
ወዲያውም ቀጠል አድርጎ፤ እንደ ሀቁ ቢሆን ኖሮ መንገድ መዘጋጋት የነበረበት ለሀይለማሪያም ደሳለኝ ሳይሆን ለተመስገን ደሳለኝ ነበር… አለኝና በቁጭት፤ ይሄው የሚያጅቡትን አያቀውቁምና… እልኩ እያታዘብኩ ነው…! ሲል አወጋኝ!
ተመስገን ደሳለኝ ገዢውም ተገዢውም ፓርቲ ሊያመሰግነው የሚገባ ጋዜጠኛ ነው፡፡ ነገር ግን ገዢዎቻችን ማመስገን የሚቆጥር ይመስል ሰውን ማመስገን አይወዱም፡፡ ስለዚህ ተሜንም በማመስገን ፈንታ ከሰሱት፡፡ ጎሽ በማለት ፈንታ እንደ ጎሽ ሊወጉት ቀንዳቸውን አሾሉበት፡፡ እሰይ በማለት ምትክ ሰይ ባንከረባብት ብለው ለሁለቱም አሰቡት፡፡ (ለማሰርም ለማሰደድም) (ሰይ ባንከረባብት በልጅነታችን ብይ ጨዋታ ላይ ተወርዋሪዋ ብይ ጉድጓዳ ውስጥ ብትገባም የተቃራኒውን ብይ ብትመታም ነጥቡ እንዲያዝልን ውል የምንገባባት ቃል ነበረች፡፡)

የግል ባንኮችን ዕድገት የሚያቀጭጨው የመንግሥት እርምጃ ለግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ አደጋ ነው! (ከ33ቱ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ)

ከ33ቱ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ

በአሁኑ ወቅት መንግሥት  የአዲስ አበባ የቤቶች ልማት ቁጠባ ፕሮግራምን ይፋ አድርጓል፡፡ በፕሮግራሙ  መሠረት 1.3 ሚሊዮን የዋና ከተማው  ነዋሪዎች ባጭር ጊዜ ውስጥ ዝግ የቁጠባ የሂሳብ ደብተር በመክፈት እንደ ፕሮግራሙ ዓይነት  ይሳተፋሉ፡፡ ፕሮግራሙ የሚጠይቀው የገንዘብ መጠን  87 ቢሊዮን ብር ሊደርስ እንደሚችል  ሲገመት ዝግ የቁጠባ ሂሳብ ደብተሩ የሚከፈተው ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ነው፡፡  መንግሥት የግል ባንኮችን ከፕሮግራሙ  ሙሉ በሙሉ አግልሏቸዋል፡፡
ይህ መግለጫችን  መንግሥት የግል ባንኮችን ከፕሮግራሙ ሙሉ በሙሉ ያገለለበትና እድሉን በስሩ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ የሰጠበት እርምጃ በነፃ  የገበያ መርህና በግል ባንኮች እንቅስቃሴ እንዲሁም በግሉ ሴክተር  የደቀነውን አደጋ ይመለከታል፡፡

Saturday, June 29, 2013

ስብሃት ነጋ “እውነት” ሲያዳልጣቸው

ከኢየሩሳሌም አርአያ

ሽማግሌው ስብሃት ነጋ ከጥቂት ቀናት በፊት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስበውት ይሁን ሳያስቡት “እውነት” አምልጧቸዋል። አጥብቀው ያነሷቸው የሙስና ጉዳዮች ራሱን የቻለ “አላማና ግብ” አላቸው። የመጀመሪያው በፓርቲያቸው ውስጥ ያለው ክፍፍል (የጥቅም) እንደተዳፈነ እሳት ውስጥ ለውስጥ እየተብላላ መሆኑን በግልፅ ያሳያል። ከተናገሩት የሚከተለውን እንመልከት፤ “በጤናማ ሁኔታ የሚገኙ ሰዎችን እንቆርጣለን፣ እናስራለን ወዘተ እያሉ ሲያስፈራሩ የነበሩ የፖለቲካ፣ የመንግስት ሰዎች ነን የሚሉ የፀጥታና የስነ አእምሮ ሁከት ፈጥረዋል። መቶ ሚሊዮን የሰረቁና ያስዘረፉ፣ 10ሺህ ብር የሰረቀውን ሲያገላብጡት ያታያሉ።” ብለዋል። « እንቆርጣለን » ያሉት መለስ ዜናዊ ናቸው፤ መለስ በአደባባይ ይህን ከመናገር አልፈው ሲያስፈራሩም እንደነበር እናስታውሳለን። መለስ ያንን ያሉት በ10ሺዎች የሚገመት ቡና ከመጋዘን ጠፋ በተባለበት ወቅት ነው። ያንን ቡና የሰረቁትና ባህር ማዶ ሸጠው ገንዙቡን ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም ምንጭ ተጠቅሶ ይፋ ተደርጓል። እናም ስብሃት “መቶ ሚሊዮን የሰረቁ..» ያሉት አዜብ መስፍንን ሲሆን፣ « ያስዘረፉ» ያሉት ደግሞ ባለቤታቸው አቶ መለስን ነው። « 10ሺህ የሰረቁ..» የተባሉት በቅርቡ የታሰሩት የጉምሩክ ሰዎችን ሲሆን..እነዚህን በንፅፅር ያስቀመጡት የአዜብ (ተላላኪዎች) ስርቆት መጠነሰፊ መሆኑን ለማመላከት ነው። ስብሃት እስካሁን አድፍጠው ቆይተው በዚህ ሰሞን ይህን መናገራቸው ..« አዜብ የከተማዋ ም/ል ከንቲባ ይሆናሉ» የሚባለውን በመስማታቸው ሆን ብለው ያደረጉት ነው፥ ይላሉ ታዛቢዎች። በተለይ ሽማግሌውን በቅርብ የሚያውቋቸው የፓርቲው ሰዎች « ስብሃት ከበረሃ ጀምሮ በቀለኛ ነው። ጥርሱ ውስጥ የገባን ሰው ካላስወገደ እንቅልፍ አይወስደውም፤ ብዙ ሰው አጥፍቶዋል። አሁንም አዜብን እግር በእግር የሚከታተለው ለዚሁ ነው» ይላሉ። በማስከተልም ፥ « ሙስና ከተነሳ ስብሃትም እስከአንገቱ ተነክሮበታል። በገርጂና ሳር ቤት የሚገኘው <ሉሲ አካዳሚ > በአሜሪካ በሚኖሩ ስጋ ዘመዶቹ ስም እንዲሁም በቀድሞ የአየር ሃይል ጄ/ል ሰሎሞን ስም የሚንቀሳቀስ ግን የስብሃት የግል ንብረት መሆኑን የማይታወቅ መስሎት ነው?….ጎንደር -ሑመራ ያለው የሰሊጥ እርሻ የስብሃት አይደለም?…በ10ሚሊዮን ብር በሚገመት በመቀሌ (አፓርታይድ መንደር) ስብሃት ዘመናዊ ቪላ እንደሚገነባ አይታወቅም ብሎ ይሆን?…» ሲሉ እነዚህ ወገኖች የስብሃትን ሙስና በከፊል ይጠቅሳሉ።sebehat nega one of the founders of TPLF
ስብሃት በዚህ አላበቁም፤ « ..እስካሁን ከፍተኛ ሙሰኞች ትንሹን ሙሰኛ ከሰው አሳስረው ያስፈርዱና ያሰቃዩ ነበር ይባላል። ከፍተኛ ሙሰኞች ከመርማሪው ጀምረው አቃቤ ሕጉም ዳኛው፣ ምስክሩም ይቆጣጠራሉ። ትንሽ የሰረቀም ምንም ያልሰረቀም ሲሰቃዩና ሲያደኸዩ የነበሩም፤ አሉም ይባላል። ስልክ እየደወሉም ይፈርዱ ነበር ይባላል።» ብለው አረፉት ስብሃት። ትክክል ናቸው!! ዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ « ይህን ካልፈረድሽ በመኪና ገጭተን ነው የምንገድልሽ » ተብላለች። ያውም ከቤተ መንግስት ተደውሎ። አባተ ኪሾ ከደቡብ ባጀት ተመላሽ የሆነ ሰባ ሚሊዮን ብር (70.000.000) ለመንግስት ተመላሽ ሊያደርጉ ሲሉ …« ወዲህ በል..የምን መንግስት ነው?» በማለት ተቀብለው ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን አባተ ፍ/ቤት ጭምር ያጋለጡት ነው። ስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ ደግሞ ታምራት ላይኔ በውሸት እንዲመሰክር አምስት ጊዜ አግባብተውት እንቢ ሲል ከማስደብደባቸው በተጨማሪ ሌላ ክስ እንዲመሰረትበት አድርገዋል። አቃቤ ሕግ የነበረው ዮሃንስ ወ/ገብርኤል የነስብሃትን የውሸት ክስ ተቀብዬ ተግባራዊ አላደርግም፤ ህሊናዬ አይቀበለውም .. በማለቱ ብቻ ለአምስት አመት እንዲታሰር አላደረጋችሁም?…ብዙ ማስረጃና መረጃ መደርደር ይቻላል።..
አሁን ስብሃት ተናገሩት እንጂ…ህዝቡ ብሎ-ብሎ የታከተው ነገር ነው!! እነ እስክንድር፣መሃመድ አቡበከር፣ አንዷለም አራጌ፣ ርእዮት አለሙ….ወዘተ በርሶ ጓደኞች በስልክ ትእዛዝ የተፈረደባቸው ናቸው!!… «ፍትሃዊ ስርአትና መንግስት አለ..» እያሉ ህዝብን የሚያደነቁሩት እነበረከትና የጋሪ ፈረስ የሆኑት ሃ/ማሪያም እርቃናቸውን የሚያስቀር ነገር ነው በስብሃት የተቀመጠው።

Friday, June 28, 2013

አንድነት ፓርቲ ሰኔ 30 በጎንደር ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱን አስታወ

ኢሳት ዜና :-አንድነት ፓርቲ የሶስት ወራት የህዝባዊ እንቅስቃሴ የትግል ስልቱን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የህዝባዊ ንቅናቄው የመጀመሪያ የአደባባይ ላይ ሰላማዊ ሰልፍም በጎንደር ከተማ ሰኔ 30/10/2005 እንደሚያደርግ አስታውቋል -፡

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ” በጎንደር እየተፈጸመ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር፣ ሰዎችን በአደራ ማሰር፣ ለሱዳን ከህዝቡ እውቅና እና ፈቃድ ውጪ መሬት መሰጠቱን፣ በነጋዴዎች ላይ የሚፈጸመውን ኢ-ፍትሃዊ አሰራር፣ ለስራ የደረሱ ወጣቶች የፓርቲ አባል ካልሆኑ በስተቀር ስራ የማያገኙበትን ሁኔታ፣ በዘር ላይ የተመሰረተን ማፈናቀልና የኑሮ ውድነትን አስመልክቶ ህዝቡ የተቃውሞ ድምጹን በነቂስ ወጥቶ ” እንደሚያሰማ ለኢሳት በላከው መግለጫ ይፋ አድርጓል፡፡ ብዙ ሺ የከተማው ኗሪዎችም የተቃውሞ ፊርማቸውን ያኖራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ፓርቲው ገልጿል።

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት ከ500 በላይ ሠራተኞችን ከስራ አባረረ

ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት በሁሉም ጣቢያዎቹ ይሰሩ የነበሩ ከ500 በላይ ሠራተኞችን ከስራ ማባረሩን ለማወቅ ተችሎአል፡፡

ድርጅቱ ሰራተኞችን ከሰኔ 17 ጀምሮ ያሰናበተ ሲሆን፣ ሰራተኞች አስቀድሞ ያልተነገራቸው በመሆኑና ያለአንዳች ካሳ በመባረራቸው ለከፍተኛ የኢኮኖሚና የስነልቦና ችግር ተዳርገዋል።

Thursday, June 27, 2013

በዋልድባ ገዳም በገዳማውያኑ አባቶች ላይ እየተፈጸመ ያለውን እንግልትና መፈናቀል አስመልክቶ

በታሪካዊው በዋልድባ ገዳም ላይ በልማት ሰበብ እየደረሰ ያለውን ችግርና በገዳማውያኑ አባቶች ላይ እየተፈጸመ ያለውን እንግልትና መፈናቀል አስመልክቶ፣ ከዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት (ዋልድባን እናድን ኮሚቴ) የተሰጠ መግለጫ። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

waldiba-ethiopia

Wednesday, June 26, 2013

ፕሬዚዳንት ኦባማ በአፍሪካ ጉብኝታቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን እንዲደግፉ ተጠየቁ

ኢሳት ዜና:-አሜሪካዊው ፕሬዚዳንት ዛሬ በሚጀምሩት የሴኔጋል፣ ደቡብ አፍሪካና ታንዛኒያ ጉብኝት በችግር ተዘፍቀው የሚገኙትን የአፍሪካ የመገናኛ ብዙሀንንና የሰአብአዊ መብቶች ተሟጋቾችን እንዲደግፉ ሂውማን ራይትስ ወች ጠይቋል።

በአፍሪካ መገናኛ ብዙሀንና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጀቶች ከፍተኛ የሆነ አደጋ ተጋርጦባቸዋል። ፕሬዚዳንቱ ጉብኝት የሚያደርጉባቸው ደቡብ አፍሪካ፣  ሴኔጋልና ታንዛኒያ ሀሳብን በነጻነት በመግለጽ እና በፕሬስ ነጻነት ዙሪያ የተሻለ ሁኔታ ቢኖርም በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ያለው ሁኔታ ግን ከዚህ የተለየ በመሆኑ ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው ትኩረት እንዲሰጡ ድርጅቱ ጠይቋል።

ስለ ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ መረጃ

ቀን፡ 18/06/2013

UKእና በመላው ዓለም በስደት ላይ የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችና መላው ነጻነት ወዳድ ኢትዮጵያውያን።

ከሃገሩ ርቆ በስደት ዓላም የሚገኘው ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ በፈጣሪው ተራዳዒነት ጥሮና ግሮ ላለፉት 40 ዓመታት ያቆማትና ያሳደጋት ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያስተዳድሩና መንፈሳዊ አባት እንዲሆኑት መርጦ የሾማቸው አባ ግርማ ከበደ በገንዘቡም ሆነ በማንኛቸውም ነገር ላይ አዛዥና ፈራጭ ቆራጩ እኔ ካልሆንኩ በማለት ሆነ ብለው ያስነሱት ውዝግብ አልሰምር ሲላቸው እነሆ አሁን ደግሞ ቤተ ክርስቲያኗን ከነ ሃብትና ንብረቷ ከስደተኛው ህብረተሰብ ወስጄ በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ቀጥተኛ ቁጥጥር ሥር በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር ትሆናለች በሚል አስባብ በአውሮፓ ውስጥ በስደተኛው የተቋቋሙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናትን በቀጥታ ለመቆጣጠር ሲባል ለተቋቋመው ሃገረ ስብከት አስረክቤ ጥቅሜን አስረክባለሁ በማለት ተከታዮቻቸውን ይዘው በሚያደርጉት ትግል ትንቅንቁ ቀጥሎ ይገኛል።
ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በሃገር፤ በሕዝብና በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚከተለውን የዘረኛ ፖሊሲና አሠራር ባለመቀበል የዚህም ዘረኛ አገዛዝ ተዋናኝ ለነበሩት ለአባ ጳውሎስ ሳትበገር ለ22 ዓመታት የመንግሥትም ሆነ የፓለቲካ ተጽዕኖ ሳይኖርባት  በነፃነት ቆማ የኖረችና ነጻ በመሆኗም ለከፍተኛ የዕድገት ደረጃ የበቃች በአውሮፓ አንጋፋዋ ቤተ ክርስቲያን ነች።

“ምስጢር ካወጣህ ቤተሰቦችህን እንፈጃቸዋለን”

“ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል”

tesfaye
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ በዝዋይ እስር ቤት ለወራት ስቃይ የተፈፀመበት
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ይባላል፤ አርሲ አርባ ጉጉ ተወልዶ አዳማ/ናዝሬት አድጎ፣ በ1998 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በ2000 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ሚ/ር በሲኒየር ካልቸራል ኤክስፐርትነት የስራ መደብ እስከ ሚያዝያ 2003 ሰርቷል፡፡ ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በግልፅ ባልተረዳው ምክንያት የመንግስት ደህንነት ሀይሎች ተያዞ ለ23 ወር በዝዋይ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈፀመበት መቆየቱን ይናገራል፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ከእስራት ሲለቀቅም አንድ ጊዜም እንኳን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ ከወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን፡፡

በረከት ስምኦን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየዶለቱ ነው

ከኢየሩሳሌም አርአያ

በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሊቀመንበርንት ከሚመራው ግንቦት ሰባት ጋር በተያያዘ በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ በረከት ስምኦን የሚመሩት የመንግስት አካል በምስጢር እየዶለተ መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ። በቅርቡ በአንድ ድረገፅ ላይ የወጣውን የዶ/ር ብርሃኑን ንግግር በማስረጃነት ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አቶ በረከትና ተከታዮቻቸው በአገር ውስጥ እየተንቀሳቅሰ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ « ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አለው፤ ከግንቦት ሰባት የገንዘብ ድጋፍ ይደረግለታል» በሚል እነበረከት ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ የፓርቲውን አመራሮች «ከሽብረተኛ ቡድን ጋር በመገናኘት» ብለው ለመክሰስ ሴራ እያበጃጁ መሆኑን አስውታውቀዋል። የፓርቲው አመራሮችን ከማሰር ባለፈ «ሰማያዊ ፓርቲ በሽብርተኛ ድርጅትBereket Simon is the Ethiopian Communications Minister የሚረዳ ነው» በሚል በአገር ውስጥ የሚኖረውን የፓርቲው ቀጣይ ህልውና ለማክሰም ጭምር እየዶለቱ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ከበረከት በተጨማሪ ደብረፂዮን ይህንን ሴራ በበላይነት እየመከሩበት እንደሆነ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ ለሚገኝ አንድ ጋዜጠኛ ከገዢው ባለስልጣናት ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደተላከለት የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። መጀመሪያ 250.000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ፣ በማስከተል 50.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሃዋላ እንደተደረገለትና ባጠቃላይ 300.000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በዶላር ተመንዝሮ በእጁ እንደደረሰው ምንጮቹ ጠቁመዋል። ገንዘቡ ከነበረከት በኩል በምስጢር የተላከ መሆኑን ያጋለጡት ምንጮቹ በዚሁ መሰረት ጋዜጠኛው ለሕወሐት/ኢህአዴግ ማገልገል መቀጠሉንና በተለይ አሁን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየተሸረበ ያለው ሴራ መነሻው ይህ ሰው እንደሆነ አያይዘው ገልፀዋል።

Tuesday, June 25, 2013

በቤተመንግስት ግቢ ዙሪያ አንድ ሰው ተገድሎ ተገኘ

ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሀሙስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ጽህፈት ቤት ጀርባ  ሁለተኛው በር ከ150 እስከ 200 ሜትር  ባለ ርቀት ላይ አንድ ጎልማሳ አንገቱ ተቆርጦ  መገኘቱን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል።  -

እማኞች እንደሚሉት  ሟቹ እድሜው ከ45 እስከ 53 የሚጠጋ ጸጉር አልባ ጎልማሳ ነው። የሟቹ የራስ ቅል  ባእታ ክሊኒክ አቅራቢያ ባለ አንድ ቦታ ላይ ተጥሎ መገኘቱን የጠቆሙት ነዋሪዎች፣ ፖሊስ በአካባቢው ተገኝቶ አስከሬኑ እንዲነሳ ከአደረገ በሁዋላ ለአስከሬን ምርመራ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል እንዲወሰድ አድርጓል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንቱ ስራ የሚ ለቁ ዳኞች ቁጥር መጨመሩን ተናገሩ

ኢሳት ዜና :-የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተገኔ ኔታነህ ሰሞኑን ለፓርላማ የመ/ቤታቸውን የ11 ወራት ሪፖርት

ባቀረቡበት ወቅት  ዳኞች በርካታ ችግሮች የተጋረጠባቸው በመሆኑ መስሪያቤቱን እየለቀቁ ነው ብለዋል።
የዳኞች መኖሪያ ቤት ችግርን በዘለቄታነት ለመፍታት ሕንጻ ለመገንባት እየተደረገ ያለው ጥረት የተወሰነ መጓተት እንደሚታይበት ፕሬዚዳንቱ ጠቁመው እስከዚያ ድረስ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ መንግስት የኪራይ ቤት መስጠቱን እንዲቀጥል የተላለፈውን ውሳኔ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ተግባራዊ ባለማድረጉ ችግሩ ቀድሞ ከነበረበት ተባብሶ መቀጠሉን ፕሬዚዳንቱ  ገልጸዋል፡፡
የዳኞች እጥረትንም በተመለከተ አቶ ተገኔ ሲያስረዱ በዚህ ዓመት 58 ያህል ዳኞች በመሾማቸው የነበረውን የዳኞች
እጥረት በመጠኑም ቢሆን ለመቅረፍ የተቻለ ሲሆን ነገር ግን ቀደም ሲል በርካታ ዳኞች ፍ/ቤቶቹን የለቀቁ
በመሆናቸው ካለው ፍላጎት አንጻር በቂ ሆኖ አልተገኘም ብለዋል፡፡

አቶ ኦባንግ በእስራኤል ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያደረጉት ንግግር ቪድዮ ይመልከቱ።


qqasddddበእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አቶ ኦባንግ ሜቶ ”የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ” (http://www.solidaritymovement.org) ሊቀመንበርን ንግግር እንዲያደርጉ ጋብዘው ነበር።”ኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማህበር በእስራኤል” በሚል ማኅበር ስር የተሰባሰቡት ወጣት ኢትዮጵያውያንን በከበረ ሰላምታ በማቅረብ ንግግራቸውን የጀመሩት ኦባንግ ”አቶ መለስ የሚነዳው ባቡር የጥላቻ ባቡር ነው…..አሁን ባቡሩ እየቆመ ነው” ብለዋል።አቶ ኦባንግ ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ ምክርቤት የውጭ ፖሊስ ንዑስ ኮሚቴ ቀርበው በተናገሩት ንግግር የብዙ ኢትዮጵያውያንን ልብ አኩርተዋል። አቶ ኦባንግ በአሜሪካ ምክርቤት ቀርበው ”እኛ አሜሪካኖችንን ነፃነት እንዲሰጡን አንለምንም ይህንን እኛ ማድረግ እንችላለን” ነበር ያሉት።
አቶ ኦባንግ በእስራኤል ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያደረጉት ንግግር ቪድዮ ይመልከቱ።

አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች

አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች

(ነቢዩ ሲራክ)
ethio maids
በሪያድ “ኢትዮጵያዊቷ አሰሪዎቿን ለመበቀል የ6 አመት ህጻን ገደለች” የሳውዲ ጋዜጣ ዘገባ
ኮንትራት ስራ መጥተው ተፈናቅለው በጅዳ ቆንስል መጠለያ ከሚገኙት ቁጥራቸው ወደ 80 ከሚጠጉት እህቶች መካከል አንዷ እህት ከሁለት ቀናት በፊት  እሁድ ጁን 23 ቀን 2013 በጅዳ ቆንስል ግቢ በር  ራሷን አንቃ መግደሏ ታውቋል። ጉዳዩን ለማጣራት  የዚህችው እህት ሬሳ ከቦታው ሲነሳ በቦታው ነበሩ ወደ ተባሉት በጅዳ ቆንስል የዲያስፖራና ተፈናቃይ ዜጎች ሃላፊ ወደ ሆኑት ቆንሰል ሙንትሃን በስልክ ለማግኘት ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም።
ስለተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት አካባቢው ከነበሩ የአይን እማኞች ለማጣራት ባደረግኩት ሙከራ ሟች በኮንትራት ስራ ከወሎ ወደ ሳውዲ አረቢያ መጥታ ከአመት በላይ ከሳውዲ አሰሪዎች ቤት ስትሰራ ከቆየች በኋላ በስራ ብዛት እግሯን ስላመማት ከስራ መፈናቀሏንና ወደ ጅዳ ቆንሰል መጠለያ መጠጋቷን ገልጸውልኛል። ያም ሆኖ በመጠለያው ትኖር የነበረች ይህችው እና የአእምሮ ሁከት ይስተዋልባት ያልነበረው እህት ባልታወቀ ምክንያት ሊነጋጋ ሲል ከቆንስሉ ግቢ በር ታንቃ መገኘቷን እንዳስደነገጣቸው እማኞች በእንባ እየታጠቡ አስረድተውኛል።

Monday, June 24, 2013

“አሜሪካ አቋማን የምትፈትሽበት ወቅት ላይ ናት” ክሪስ ስሚዝ

"አሸባሪነትን መዋጋት የግፍ ማከናወኛ ሽፋን አይሆን

ኢህአዴግ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ስም ከአሜሪካ ጋር የመሰረተውን ግንኙነት አስታክኮ የሚፈጽመው ኢሰብዓዊ ድርጊት ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ ተገለጸ። አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውን ፖሊሲ የምትመረምርበት ወቅት ላይ ትገኛለች ተባለ። ኢህአዴግ ጸረሽብርተኝነትን ለአፈናና ለበጀት ማሟያ እየተጠቀመበት እንደማይቀጥል ተመለከተ።
አሜሪካና ሌሎች ለሰብአዊ መብት መከበር ዋጋ የሚሰጡ አገሮች በሙሉ በ”አዲስ አበባው” አገዛዝ ላይ ጠንካራ አቋም መያዛቸውን ያለ አንዳች ማወላወል ማሳየት እንደሚገባቸው እንደራሴ (ኮንግረስማን) ክሪስ ስሚዝ ያስታወቁት ሽብርተኛነትን አስመልክቶ ጠንካራ ማሳሰቢያ በማስቀመጥ ነው።

Sunday, June 23, 2013

የትኛው አማራጭ ለአሜሪካ? “ኢህአዴግን ምን እናድርገው? ንገሩን!”

ጎልጉል፣ የድረገጽ ጋዜጣ

አሜሪካ ከመቼውም ጊዜ በላይ ደንግጣለች። ኦባንግ እንዳሉት ለህዝባቸው “ሬት” ለምዕራባውያንና “ማር” (የቤት ቀጋ፤ የውጭ አልጋ) የነበሩት አምባገነን በድንገት እንደ ተነቀለ ቡሽ ተስፈንጥረው ከሲስተም መውጣታቸው አሜሪካንን አስጨንቋታል። በተለይም እሳቸው አፍነው የያዙት የስርዓቱ “ክፉ ጠረን” አሁን እነርሱ (አሜሪካውያኑ) ደጅ የደረሰ ያህል መፍትሄ ለመፈለግ የወሰኑ ይመስላሉ።
አውቀውና ፈቅደው ሲታለሉ የቆዩበትን ጊዜ አስልተው መንገዳቸውን የማስተካከል ስራ የጀመሩት ዛሬ አይደለም። አንዳንድ ምንጮች እንደሚሉት ከመለስ ሞት በኋላ አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ ላይ ሚዛኗን ሊያስታት የሚችል ውድቀት የሚደርስባት ኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም ማስተካከል ሲያቅታት ብቻ እንደሆነ ይናገራሉ።Obang Metho’s Testimony before the Subcommittee on Africa
“… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ እቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም ሊታመን የማይችል ነው። የሰከረ ርዕዮት ዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ የተጠመቁ፣ እንኳንስ 50 ሚሊዮን ህዝብ ያላት አገር ቤተሰብን የመምራትና የማስተዳደር ተሞክሮ የሌላቸው፣ አገርን መምራትን የሚያክል ታላቅ ሃላፊነት ማሸከም ለኔ ከአእምሮ በላይ ነው …” የዛሬ 22ዓመት ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ ከተናገሩት፡፡
“አሜሪካኖች ነጻ እንድታወጡን አንጠይቃችሁም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ነጻ እንደሚወጣ ያውቃል። እናንተ ግን በነጻነት መንገዳችን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑብን፤ (የነጻነት መንገዱን አትዝጉብን)። ከመንገዱ ላይ ገለል በሉ … እስካሁን ያልተሞከረ መንገድ አለ … እሱም እርቅ ነው … ከመንግሥትም ሆነ ከተቃዋሚው በኩል ዓመኔታ የሚጣልባቸው አሉ … ” አቶ ኦባንግ ሜቶ፡፡
“የሚታየኝ ጦርነት ነው፣ የርስ በርስ ግጭት ነው። የርስ በርስ ግጭት በኢትዮጵያ የመነሳቱ ጉዳይ የማይቀር ነው። አገሪቱ ላለፉት 21 ዓመታት በተጓዘችበት መንገድ አትቀጥልም። … ሕዝብ በጭቆና አገዛዝ እየተገዛ ዝም ብሎ የማይኖርበት ደረጃ ላይ ደርሷል … ዝም ብሎ ግን አይቀመጥም … ይፈነዳል … ይህን እንድትገነዘቡ እፈልጋለሁ” ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፡፡

Saturday, June 22, 2013

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. እና ኢትዮጵያ (ገብረመድህን አርአያ)

አቶ ገብረመድህን አርአያ*

ከአውስትራሊያ

ወደ ግንቦት 20ቀን, 1983 ዓ.ም. ከመግባታችን በፊት ትንሽ ወደ ኋላ መለስ በማለት የደርግ ስርዓትን በትንሹ እንቃኘው::

ደርግ
የካቲት ወር 1966 ዓ.ም. የዘውድ አገዛዙን ስርዓት በመቃወም በአርሶ አደሩ ፣ በተማሪው ፣ በአስተማሪው ፣ በመንግስት ሰራተኛው ፣ በወዛደሩ ፣ በነጋዴው እና በመለዮ ለባሹ ወዘተ ፣ ወዘተ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ጊዜ ሳይወስድበት በ6 ወራት ውስጥ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ ግቡን መታ::
ህዝባዊ አመጹን የሚመራው የተደረጀ ፓርቲ ባለመኖሩ በር የተከፈተለት መለዮ ለባሽ አመቺ ሁኔታ በማግኘቱ በፍጥነት ተደራጅቶ ከተራ ወታደር ጀምሮ የተለያዩ ማእረግ ያላቸው አባላቱን አስመርጦ ወደ 120 የሚጠጉ ተወካዮቹን አዲስ አበባ በሚገኘው አራተኛ ክፍለጦር አሰባሰበ::

Friday, June 21, 2013

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በወልድያ ጠንካራ ተቃውሞ አሰሙ

ኢሳት ዜና:-ተቃውሞው ከአመት በላይ የዘለቀው የድምጻችን ይሰማ ተቃውሞ አንዱ አካል ቢሆንም ፣  የዛሬው የተቃውሞ መነሻ ግን የፌደራል ፖሊሶች ሐሙስ ጧት  ከ35 አመታት በላይ ሲያገለግል የነበረውን የወልድያ እርዳታ ማህበር ቢሮ ማሸጋቸውን ተከትሎ የመጣ መሆኑን የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት ገልጸዋል።

Thursday, June 20, 2013

መሬታቸው የተወሰደባቸው ከ50-60 የሚጠጉ የመተማ አርሶአደሮች ጫካ መግባታቸውን ሲያስታውቁ ከ30 ያላነሱት ደግሞ ታስረዋ

ኢሳት ዜና:- በመተማ ዮሐንስ እና በኮኪት ቀበሌዎች የሚኖሩ አርሶአደሮች መሬታችን አድሎአዊ በሆነ መልኩ ለባለሀብቶች እየተሰጠብን ነው” በማለት ተቃውሞአቸውን ማሰማታቸውን ተከትሎ ጸረ ሽምቅ እና ልዩ ሀይል የሚባሉ የመንግስት ታጣቂዎች ከ30 ያላነሱትን የአካባቢውን ሰዎች ሲያስሩ፣ በታጣቂዎች ከሚፈለጉት መካከል ደግሞ ከ50- 60 የሚሆኑት አርሶደሮች ጫካ መግባታቸውን አስታውቀዋል።

የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ውይይት አደረገ

ኢሳት ዜና:- የአፍሪካ ጉዳዮች ሃላፊ ዶናልድ ያማማቶ፣ በአፍሪካ የዩሴ አይ ዲ ዳይሬክተር ኤሪል ጋስት፣ በአፍሪካ  ጉዳዮች ተመራማሪ  ዶ/ር ፒተር ፓሀም፣ የግንቦት7 ሊቀመንበር ዶ.ር ብርሀኑ ነጋ ፣ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር  አቶ ኦባንግ ሜቶና የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአሜሪካ ተወካይ  ሚስተር አዶቲ አኪዌ እና ሌሎችም ታዋቂ ምሁራን ፖለቲከኞች የተሳተፉበት ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ አምባሳደር ያማማቶ እና ዶ/ር ጋስት ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንድምትገኝ ገልጸዋል።

የኢህአዴግ መንግስት የኢኮኖሚ እድገት ማምጣቱን የገለጹት አምባሳደር ያማማቶና ሚስተር ጋስ፣  በሌላ በኩል ግን መንግስት ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብቶች ረገጣ በመፈጸሙ የአገሪቱን መጻኢ እድል አደጋ ላይ ጥሎታል ብለዋል።
ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ፣ አቶ ኦባንግ ሜቶ እና ሚ/ር አክዌ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን፣ ዶ/ር ብርሀኑ ከአቶ መለስ ሞት በሁዋላ ያለው የኢትዮጵያ ሁኔታ በመለስ ጊዜ እንደነበረው ምናልባትም ከዚያ በበሳ ሁኔታ አስከፊ እየሆነ መሄዱን ገልጸዋል። የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከፍተኛ ገንዘብ የዘረፉ እና ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የፈጸሙ በመሆናቸው እንጠየቃለን በሚል ፍርሀት ስልጣን በቀላሉ ለመልቀቅ እንደማይፈልጉ ዶ/ር ብርሀኑ አክለዋል።

ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንና የዘረኛው ወያኔ ሹመኞች

በሰው ቁስል ላይ ጨው እየነሰነሱ የክርስቲያን ሥራ እየሰራሁ ነው ማለት አይቻለም።

በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሃዱ አምላክ፤ አሜን።
በ09/06/2013 በዕለተ እሑድ ለንደን በሚገኘው የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከቅዳሴ በኋላ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደርና ሹማምንቶች የሚቀጥለውን ማስታወቂያ ለሕዝቡ አስተላልፈዋል።
  1. በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላለፉት ሦስት ወራት መዘጋቷን፤
  2. ለብጥብጡና ለችግሩ መንስዔ የሆነው ቤተ ክርስቲያኗ ኢትዮጵያ በሚገኘው በቅዱስ ሲኖዶስ ሥር ባለመመራቷ መሆኑን፤
  3. ቤተ ክርስቲያኗ ላለፉት 7 ዓመታት ኢትዮጵያ ከሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ተነጥላ ብቻዋን ስትንከራተት ከቆየች በኋላ አሁን ተመልሳ መቀላቀሏን። (ማስታወቂያው ከተነገረ በኋላ እንደ ተለመደው ሕዝቡ የሚጠበቅበትን ጭብጨባና እልልታ እንዲያሰማ ተደረገ)
  4. ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ችግር መንስዔ የሆነው ጉዳይ እልባት ሊያገኝ የቻለው ከቅዱስ ሲኖዶስ ተልከው በመጡት በሊቃነ ጳጳሳቱ መሆኑንና የሰጡት መፍትሔም ቤተ ክርስቲያኗ በአቡነ እንጦስና በመጋቢ ተወልደ በሚመራው የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሃገረ ስብከት ሥር እንድትደዳደር መመሪያ ሰጥተው ወደ ኢትዮጵያ መለሳቸው ነው በማለት አብራርተዋል።
በመጨረሻም ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በሃገረ ስብከቱ ሥር እስከሆነች ድረስ ማንኛቸውም ምእመን በቤተ ክርስቲያኗ የመገልገል መብት ስላለው ቤተ ክርስቲያኗ ባስቸኳይ ተከፍታ አገልግሎቷን እንድትሰጥ ሕዝቡ ማመልከቻ (Petition) ላይ እንዲፈርም የተደረገ ሲሆን በገብረኤል ቤተ ክርስቲያንም ተመሳሳይ ሁኔታ እንደተፈጸመ ለማወቅ ተችሏል።
ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ፡
  1. ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በሃገረ እንግሊዝ ከተመሠረተች ከ40 ዓመታት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ኢትዮጵያ ከሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ተነጥላ አታውቅም፤ አሁን የተፈጠረውም ችግር በቅዱስ ሲኖዶስ ሥር ትሁን አትሁን ከሚለው ጥያቄ ጋር አንዳችም ግንኙነት የለውም።በእርግጥ ቤተ ክርስቲያኗ ኢትዮጵያ በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር ሆና ብትቆይም ቤተ ክርስቲያኗ በውጪ ሃገር የምትገኝ በመሆኗ እና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተፈጠረው ችግርና መከፋፈል የተነሳ ከአንድም ሁለትና ሦስት ጊዜ በአባ ጳውሎስ አማካኝነት ከኢትዮጵያ ተልከው በመጡ እንደ ሊቀ ካህናት ብርሃኑ፤ አቡነ ኢሳያስና በመጨረሻም በአቡነ ሙሴ አማካኝነት ተደጋጋሚ ችግር ስለደረሰባት የተፈጸመባት ከቅዱስ ሲኖዶሱ ጋር ያላትን ግንኙነት ሳታቋርጥ አስተዳደሯንና ንብረቷን በተመለከተ ግን ቃለ ዓዋዲውን መሠረት በማድረግ  በUK የቻሪቲ ሕግ መሠረት ራሷን ችላ ስትተዳደር ቆይታለች። ይህንን አቋሟን ልለውጥ፤ ወይም ላሻሽል ብሎ የተነሳ ክርክርም ሆነ ጸብ የለም።
  2. ከዚሁ ጋር ቤተ ክርስቲያኗ አሁን በህይወት የሌሉት አባ ጳውሎስ በቤተ ክርስቲያኗም ላይ ሆነ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረሱትን በደልና ግፍ ከግምት ውስጥ በማስገባት ስማቸውን ቅዱስ ብሎ ላለመጥራትና አመራራቸውንም ላለመቀበል የጠራ አቋም በመያዝ በዛ አቋም መሠረት ስትመራ
ከ7 ዓመት በፊት አቡነ እንጦስ ቤተ ክርስቲያኗን መንበሬ እንዳደርግ በአባ ጳውሎስ ተሹሜአለሁ ብለው በመጡበት ወቅት የቤተ ክርስቲያኗን አቋም ተቀብለው እንዲያገለግሉ ሲጠየቁ የቤተ ክርስቲያኗን አቋም አልቀበልም በማለታቸውና የአባ ጳውሎስንም ሥም ካልጠራሁ ላገለግል አልችልም በማለታቸው ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ሳይመጡ ቀርተዋል። “ቤተ ክርስቲያኗ ኢትዮጵያ ከሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ተነጥላ ለ7 ዓመት ስትንከራተት ነበር” በማለት በስላሴ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር አማካኝነት ለሕዝቡ የተላለፈው መልዕክት ከአቡነ እንጦስ ተነጥላ በሚል ቢታረም ምናልባት ከእውነት ጋር ሊገናኝ ይችል ይሆናል እንጂ ቤተ ክርስቲያኗ ኢትዮጵያ ከሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ የተነጠለችበት ወቅትና ጊዜ የለም።

Monday, June 17, 2013

የኢትዮጵያን ደስታ የፊፋ ዜና አቀዘቀዘው( Fisseha Tegegn)

አዲስ አበባ ላይ የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድንን ያስተናገደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጌታሁን ከበደ እና የደቡብ አፍሪካው የፊታ አጥቂ በርናርድ ፓርከር በራሱ ጎል ላይ ባስቆጠሯቸው ጎሎች 2 ለ 1 አሸንፏል።
_68206993_ethiየደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን በተላይ በመጀመሪያዎቹ 20 እና 25 ደቂቃዎች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመሀል ክፍል ኳሱን እንዳይቆጣጠር ለማድረግ በሚል ተጭኖ የተጫወተ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ሰባት እና ስምንት የደቡብ አፍሪካ ተጨዋቾችን የኢትዮጵያ ቡድን ግማሽ ሜዳ ላይ ማየት የተለመደ ነበር።
ሆኖም የጨዋታውን የመጀመሪያ የጎል ማግባት እድል የፈጠረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሲሆን ሳልሀዲን ሰኢድ በግንባሩ የገጨውን ኳስ የደቡብ አፍሪካው ግብ ጠባቂ ኩኔ አድኖበታል።

ከፍተኛ የደህንነት ሹም ከስልጣን ተነሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

ከኢየሩሳሌም አርአያ

የሕወሐት አባልና የአገር ውስጥ ደህንነት ዋና ሃላፊ አቶ ወልደስላሴ ከስልጣናቸው እንዲነሱ መደረጉን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። ወ/ስላሴ ከስልጣን እንዲነሱ ያደረጉት የደህንነት ዋና ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ መሆናቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል። የሁለቱ ሹማምንት ፀብ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ ቆይቶ መጨረሻ መፈንዳቱ ታውቋል። በመቀሌ በተካሄደው የፓርቲው ጉባኤ አቶ ጌታቸው የፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባል ሆነው እንዳይመረጡ ሰፊ ቅስቀሳ ሲካሂድ የቆየው ወ/ስላሴ በመጨረሻም የአባላት ምርጫ ሲካሄድ ባቀረበው ተቃውሞ ላይ «..ጌታቸው የተሰጠውን የፓርቲና መንግስታዊ ሃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ አይደለም፤ የአልሙዲ ተላላኪና አሽከር ሆኗል… የአላሙዲ አገልጋይ ሆኖዋል… ስለዚህም በማ/ኮሚቴ አባልነት መካተት የለበትም..» ሲል መናገሩን ያወሱት ምንጮቹ፣ የወ/ስላሴ ተቃውሞ ተቀባይነት ባለማግኘቱ አቶ ጌታቸው በማ/ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲቀጥሉ መደረጉን አያይዘው ገልፀዋል።…

የቢሮ ኃላፊው በሙስና ላይ ምስክር ሳይሆኑ ተገደሉ

“ብዙ ሳይታወቅ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ”

በነበራቸው የስራ ሃላፊነት በድብቅ መረጃ ሲያሰባስቡ ቆይተው ለመንግስት ካጋለጡ በኋላ ራሳቸውን ደብቀው የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኢሬሣ ምሳ እየተመገቡ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ። አቶ ተስፋዬ ሰኞ ለጸረ ሙስና ኮሚሽን የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ከኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ቀጠሮ ይዘው ነበር።
Allegations of Corruption Emerge Against Federal Government Examiners
Former Gambella Regional President, Mr. Omot Obang Olom
በቅርቡ ወደ ፌደራል መንግስት የተዛወሩት የጋምቤላ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኡሞት ኦባንግ፣ ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ አላግባብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን፣ እንዲሁም በክልሉ የሚፈጸሙትን የተጭበረበሩ የበጀት አፈጻጸሞችንና ምዝበራዎችን የሚያጋልጡ ሰነዶችን በሚስጥር በማደራጀት ለኢህአዴግ ያቀረቡት አቶ ተስፋዬ አሟሟታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

የቢሮ ኃላፊው በሙስና ላይ ምስክር ሳይሆኑ ተገደሉ

“ብዙ ሳይታወቅ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ”

food
በነበራቸው የስራ ሃላፊነት በድብቅ መረጃ ሲያሰባስቡ ቆይተው ለመንግስት ካጋለጡ በኋላ ራሳቸውን ደብቀው የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኢሬሣ ምሳ እየተመገቡ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ። አቶ ተስፋዬ ሰኞ ለጸረ ሙስና ኮሚሽን የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ከኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ቀጠሮ ይዘው ነበር።
በቅርቡ ወደ ፌደራል መንግስት የተዛወሩት የጋምቤላ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኡሞት ኦባንግ፣ ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ አላግባብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን፣ እንዲሁም በክልሉ የሚፈጸሙትን የተጭበረበሩ የበጀት አፈጻጸሞችንና ምዝበራዎችን የሚያጋልጡ ሰነዶችን በሚስጥር በማደራጀት ለኢህአዴግ ያቀረቡት አቶ ተስፋዬ አሟሟታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።