Saturday, December 21, 2013

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ከዓለም 2ኛ ሆነች

መቀመጫውን በኒዮርክ ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ቡድኑ /CPJ/  ባለፈው ረቡዕ  ይፋ ባደረገው ሪፖርት፤ ጋዜጠኞችን በማሰር ከአለም አስር አገሮች መካከል ኢትዮጵያን በሁለተኛ ደረጃ ያስቀመጠ ሲሆን ኤርትራ ቀዳሚ ሆና፣ ግብፅ በሶስተኝነት ተቀምጣለች፡፡ 

Wednesday, December 18, 2013

“አና ጐሜዝ አሁንም ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ይቆረቆራሉ” – አቶ አስራት ጣሴ (የአንድነት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ)


ከአቶ አስራት ጣሴ (የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ)
ከአና ጐሜዝ ጋር ከአንድ ሠዓት ተኩል ለማያንስ ጊዜ ነው የቆየነው፡፡ የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላት ከእኛ ጋ የተገናኙት ገለፃ ለማድረግ አስበው ሣይሆን የእኛን አስተያየት ለመስማት ነበር፡፡ ውይይቱ፣ ኢትዮጵያ ያለችበትን ተጨባጭ ሁኔታ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን እና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችን የሚዳስስ ነበር፡፡ በወቅቱ ከሞላ ጐደል ተደጋጋፊ እንጂ የሚቃረኑ ሀሣቦች አልተነሱም፡፡ በእኔ በኩል፣ በኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል በከፍተኛ ችግርና አደጋ ላይ እንደሚገኝ፣ ኢትዮጵያም መስቀለኛ መንገድ ላይ እንደሆነች፣ ከፊታችን አሳዛኝና አስጊ ሁኔታዎች እንዳሉ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ሕዝቡ ሰላማዊ ትግሉን አስመልክቶ ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታዎች እያሣየ መሆኑን ገልጫለሁ፡፡

“ሰላማዊ ትግል” የሚለው “ሰላማዊ እንቅልፍ” የሚል ደረጃ ላይ

Tuesday, December 17, 2013

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተመሰረተበትን አንደኛ አመት አስመልክቶ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ



የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተመሰረተበትን አንደኛ አመት አስመልክቶ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ

ቀን ታህሳስ 7 2006
ታህሳስ 7 2006 ዓም የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከተመሰረተ አንድ አመት ሞላው። አንድ አመት በጭንቅና በአሳር ለተያዘች የዛሬይቱ ኢትዮጵያና ህዝቧ እጅግ ረጅም ግዜ እንደሆነ ህዝባዊ ሃይሉ በሚገባ ይገነዘባል። ባላፈው አንድ አመት ውስጥ የኢትዮጵያን ህዝብ የመከራ፣ የአሳርና የውርደት ህይወት ይበልጥ እየሰፋ፣ የሚፈጸምበት ግፍ ይበልጥ እየገዘፈ መሄዱን አይተነዋል። በሃገርና በህዝብ ላይ እየወረደ ያለውን ወያኔ ወለድ የስቃይና የፍዳ ናዳ በቅጡ ላጤነው ሃገሪቱና ህዝቧ የአዳዲስ የስቆቃና የመከራ አይነቶች መፈተኛ ቤተ ሙከራዎች እየተደረጉ ለመሆኑ ጥርጥር አይኖረውም። ለሚራበው፣ ለሚረገጠው፣ በግፍ ለታጎረው፣ በኑሮ ውድነት ለሚጠበሰው፣ ለተሰደደው ለተፈናቀለው ኢትዮጵያዊ እንድ አመት በሲኦል የቀናትና የወራት መቁጠሪያ እንደሚለካ ዘመን እጅግ የረዘመ የስቃይ ግዜ ነው።

ኮሜዲያን ዶክሌ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ታወቀ

















(ዘ-ሐበሻ) በቅርቡ ወደ ሰሜን አሜሪካ የመጣው እና ከስራ ባልደረባው ከኮሜዲያን ተመስገን ባትሪ ጋር በመሆን የኮሜዲ ሥራውን እየተዟዟረ በማቅረብ ላይ የሚገኘው ኮሜዲያን ዶክሌ (ወንደሰን ብርሃኑ) በቨርጂኒያ አሌክዛንደሪያ ሆስፒታል ኢመርጀንሲ ሩም ገባ በሚል የተሰራጨው መረጃን ተከትሎ ዘ-ሐበሻ ባደረገችው ማጣራት ኮሜዲያኑ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ አረጋግጣለች።

“ሕወሓት ከመለስ ሞት በኋላ እየተዳከመ ያለ ድርጅት ነው፤ ኢህአዴግ ለዘለዓለም መግዛት አለብኝ የሚል ድርጅት ነው” ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ


ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ ከህወሓት ጋር 17 ዓመታት በትግል ያሣለፉ እና ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዷ ነበሩ፡፡ በ1993 ዓ.ም ከፓርቲው ከተሰናበቱ አባላት አንደ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት የ“አረና” ፓርቲ አባል የሆኑት ወ/ሮ አረጋሽ በአጠቃላይ ጉዳዮች ዙሪያ ከ“ሎሚ” አዘጋጅ ቶማስ አያሌው ጋር ያደረጉት ቆይታ የመጀመሪያ ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

ሎሚ፡- የኢህአዴግ ጭቆናና፣ አፈና፣ የተንሰራፈው በመላው ሀገሪቱ ነው የሚል አቋም ካላችሁ፣ ብሔር ተኮር ፓርቲ የመሰረታችሁበት ምክንያት ምንድነው;
አረጋሽ፡- ፓርቲ የሚመሰረተው በአካባቢ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት አድርጐ ነው፡፡ ተጨባጭ ሁኔታ ስል የማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሰብዓዊ መብት፣ የኢኮኖሚ ችግሮችን ለመጥቀስ ፈልጌ ነው፡፡ ማንኛውም ድርጅት በዚህ መልኩ ነው የሚመሰረተው፡፡ አረናም በዚሁ መሠረት የተመሠረተ ፓርቲ ነው፡፡

Monday, December 16, 2013

በደቡብ ሱዳን የተደረገው መፈንቅለ መንግስት መክሸፉን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ተናገሩ

በደቡብ ሱዳን የተደረገው መፈንቅለ መንግስት መክሸፉን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ተናገሩ የአዲሲቷ አገር መሪ የሆኑት ሳልቫኪር የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ታማኝ ወታደሮች መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሌሊቱን ተኩስ መጀመራቸውን ተናግረዋል። ችግሩ በቁጥጥር ስር መዋሉን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ እንዲህ አይነቱን ድርጊት

ሁለገብ ትግል – ከኔልሰን ማንዴላ ጋር የምንጋራው የትግል ስትራቴጂ ግንቦት 7 ለፍትህና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄም በኔልሰን ማንዴላ ዜና እረፍት የተሰማውን ሐዘን በመግለጽ መግለጫ ያወጣ ቢሆንም የትግል ተሞክሯቸው ለአገራችን ስላለው ጠቀሜታ ተጨማሪ ቁም ነገሮችን ማንሳት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል። ኔልሰን ማንዴላንና የትግል ጓዶቻቸው መሣሪያ እስከማንሳት ያደረሳቸው የደቡብ አፍሪቃ አፓርታይድ አገዛዝ ዋነኛው መገለጫው የባንቱስታን ሕግ ነበር። በዚህ ህግ መሠረት ደቡብ አፍሪቃ ዘርን መሠረት ያደረጉ አስር “ባንቱስታ” የተሰኙ “ራስ ገዝ” ግዛቶች ተቋቁመው ነበር። ያኔ በደቡብ አፍሪቃ አገዛዝ ሥር በነበሩ የደቡብ ምዕራብ ግዛቶች ደግሞ ሌላ አስር ባንቱስታዎች ነበሯቸው።

በእያንዳንዱ ደቡብ አፍሪቃዊ መታወቂያ ባንቱስታው እንዲገልጽ ህጉ ያስገድዳል። የአንዱ ባንቱስታ ነዋሪ ያለልዩ ፈቃድ ወደሌላው ባንቱስታ መሄድ አይችልም። ከዚህም ሌላ ለነጮች ብቻ በተከለሉ ቦታዎች ጥቁሮች ለሥራ ካልሆነ በስተቀር ለሌላ ማናቸው ተግባር እንዳይገኙ ህጉ ያዛል። አፓርታይድ የደቡብ አፍሪቃ ዜጎችን በየዘር ክልሎቻው ውስጥ አጉሮ አገራቸውን እስር ቤታቸው እንዲሆን አደረገው። ይህንን ለመቃወም ኔልሰን ማንዴላ እና የወቅቱ ታጋዮች በመጀመሪያ ሰላማዊ ትግልን ሞከሩ፤ ያ አላዋጣ ሲል መሣሪያ አነሱ። በአሁኑ ሰዓት ባንቱስታን መሰል የክልል አስተዳደር ያለው በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው። ልክ በአፓርታይድ ደቡብ አፍሪቃ እንደነበረው ሁሉ የኛም መታወቂያዎች ዘራችንና ክልላችንን ይገልፃል። በአፓርታይድ ደቡብ አፍሪቃ እንደነበረው ሁሉ እኛም ከክልላችን ውጭ ተንቀሳቅሰን መሥራትና መኖር አንችልም።

Saturday, December 14, 2013

የጠላቶቻችን ተግባርና፤የወዳጆቻችን ዝምታ

ደ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዳሉት ‹‹የጠላቶቻችንን ቃሎች ከምናስታውስ ይልቅስ የወዳጆቻችንን ዝምታ እናስበዋለን›› እኔ ደግሞ፤ የጠላቶቻችንን ተግባርና ግፋዊ ድርጊት እያሰብነው ይቅርታንም እንቸራለን የሚያደርጉትን አያውቁትምና፡፡ የሚፈጸመውን ግፍ፤የሕዝብ መብት ገፈፋ፤ የሰብአዊ መብት መጣስን፤የፍትህን እጠትና ሌላውንም ሁሉ እያዩ እነዳላዩ እየሰሙ እንዳልሰሙ በመሆን ጀሯቸውን የጠቀጠቁትን፤ አፋቸውን የለጎሙትን፤ አንደበታቸውን የዘጉትን ወዳጀቻችንን ግን ይቅርታም አልቸር ልረሳውም አልፈቅድም፡፡

በእስር ስር ያሉትን ዘወትር አብረናቸው እንዳለን ከማሳወቅና እንዳልረሳናቸውና እንዳልተውናቸው ከማሳየት የላቀ ምንም ተስፋ የለም፡፡ እስክንድር ነጋ አንዱዓለም አራጌ ርእዮት ዓለሙና ሌሎችም የግፍ ታሳሪወች በጨካኝና ግፈኛ ገዢ ዋሻ ውስጥ ናቸው፡፡ በየእለቱ ነፍሳቸው እንዲሳሳና እንዲንበረከኩ እየተደረጉ ነው፡፡ ይህን ደግሞ አንሰማውም ዋሸው ጥልቅ መዝጊያው ድርብ ነውና፡፡ ድምጻቸው ታፍኗልና ድምጻቸው ልንሆንና ልንጨህላቸው ይገባል፡፡ ያሉበት ቦታ የግፈኛው አገዛዝ የግፍ ዋሻ በትንፋገት የተሞላና ለበሽታ የሚያጋልጥ በመሆኑ ስቃያቸው ሊሰማን ተገቢ ነው፡፡ ስለኢትየጵያ የፐለቲካ እስረኞች ጉረሯችን እስከሰል መጨህ ያለብን ለታይታ

Friday, December 13, 2013

አጋጣሚዎችን ሁሉ ለራሳቸው ጥቅም የሚያውሉ ነውረኞች ! – አበራ ሽፈራው/ከጀርመን


መንግሥትና ዘመናዊ የሌብነት ስልቶቻቸው
እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጥር ጥቅምት መጨረሽና  ህዳር ወር 2006 እጅግ አሳዛኝና በህይወት እስከአለን ድረስ የማንረሳው ክፉ አጋጣሚ በእህቶቻችንና በወንድሞቻችን ላይ ግድያን፣ መድፈርን፣ እስርን፣ መታረድንም፣ በመኪና እየተገጩም ጭምር መሞትንም መጀመሩን ያየንበትና የሰማንበት:: ክፉ ወር:: ብዙዎቻችን በውስጣችን ከራሳችን ጋር የተሟገትንበት፣ ምን እናድርግ? ብለን ከቅርብ ጓደኞቻችን ጋር የተነጋገርንበት:: ሌሎቻችንም ተሰባስበን በውስጣችን ያለውን ሃዘን በግልጽና በአደባባይ ዓለም ሁሉ እየሰማ የተነፈስንበት::  ሳውዲ አረቢያዎች ለዘመናት አብሮአቸው የነበረውን ጭካኔ በአይናችን የተመለከትንበት ምን አልባትም እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ከዚህ በላይ ሲጨቆኑና ሲረገጡ መኖራቸውንም ለማየት የቻልንበት ጊዜ ይህ ይፋ ወጣ እንጂ::

ጄነራል ሳሞራ የኑስ በውጭ ተቃዋሚዎች የመለስን የበላይነት መስክረዋል አሉ


(ዘ-ሐበሻ) ኢሕአዴግ ለይስሙላ ያከብረዋል እየተባለ በሚተቸውና ለ8ኛ ጊዜ የተከበረውን የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሕገ መንግሥት ቀን በዓል ምክንያት በማድረግ መንግስት ባሳተመው ‘ሕብረ ብሔር’ መጽሔት ላይ ቃለ ምልልስ የሰጡት የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጀነራል ሳሞራ የኑስ መለስ ከሞተ በኋላ በውጭ ያሉ ተቃዋሚዎች የሟቹን አቶ መለስ ዜናዊን የበላይነት መስክረዋልና እናመሰግናቸዋለን አሉ። በሰራዊቱ ውስጥ እኩልነት እንዳለ መናገራቸውም ብዙዎችን አስገርሟል።

Thursday, December 12, 2013

በፖለቲካዊ ውሳኔ የህዝብን ስነልቦና መርታት አይቻልም!!!

ሀሙስ ታህሳስ 3/2006


ለህዳር 23 ተቀጥሮ የነበረው በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ የተመሰረተው
ክስ የውሳኔ ቀጠሮ የህግ አግባብነት በሌለው እና የፍርድ ቤቶችን ከፖለቲካዊ
ተፅእኖ ነፃ በሆነ መልኩ የመንቀሳቀስ ዴሞክራሲያዊ መርህ በጣሰ አካሄድ ወደ
ታህሳስ 3 መዛወሩን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ እነዚህ መረጃዎች አሁንም

Wednesday, December 11, 2013

በጅዳ ቆንስል በር ውላ የምታድረው እህት ክራሞት…

ነቢዩ ሲራክ

Ethiopian woman in Saudi Arabia, Jiddah Ethiopian embassy
ይህችን እህት በጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት በር ተቀምጣ ካየኋት ሳምንት አልፏል። አልፎ አልፎ ላነጋግራት ብሞክርም መልስ አትሰጥም። መጀመሪያ ያየኋት ቀን አካባቢ ከስራ ለተፈናቀሉ እህቶች አነሰም በዛ መጠለያ እያለ ፣ ለምን በር ላይ ትሆናለች? ብየ የጠየቅኳቸው የቆንስሉ ጸጥታ አስከባሪ “አንተየ የዚህች እህት ጉዳይ አስቸጋሪ ነው ።

አንዱዓለም አራጌ ከእስር ቤት “እኔ እስሩ አልከበደኝም፤ በጣም ያሳዘነኝ ግን በኔ መታሰር ልትጠቀሙበት አልቻላችሁም” አለ


(ዘ-ሐበሻ) የ2005 ዓ.ም የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ምርጥ ተብሎ የተሰየመውና በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት የሚገኘው ወጣቱ ታጋይ አንዱዓለም አራጌ እስር ቤት ሊጠይቁት ለሄዱት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች መልዕክት አስተላለፈ። በጣም ማዘኑንም ገለጸ። ዕድሜ ልክ እስራቱን ተቀብሎ እስር ቤት የሚገኘው አንዷለም አራጌ “ይቅርታ አልጠይቅም” በሚል እስካሁን በእስር ቤት እየማቀቀ ሲሆን “በእኔ መታሰር ብዙ ልትጠቀሙበት ስትችሉ አለመጠቀማችሁ ያሳዝነኛል:: እኔ አሁን በእስር ባለሁበት ሰዓት የኢትዮጵያን ሕዝብ የነፃነት ትግሉን ወደ ፊት ለመግፋት አጋጣሚ ሊሆንላችሁ ቢችልም አልተጠቀማችሁበትም ” ሲል የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን መውቀሱን የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።

Monday, December 9, 2013

የመንግስት ወሮበላ ሚልዮነሮች ወይ ቢልዮነሮች እነማን ናቸው?


የኢትዮጵያ ‘ሚልዮነሮች’!አብረሃ ደስታ
ከአንድ መቶ ዘጠኝ ሺ በላይ ዜጎች ወደ አንድ ሀገር የሚሰደዱባት ሀገረ ኢትዮጵያ ባለ ብዙ ሚልዮነሮች ሆነች አሉን። ወጣት ዜጎቻችን ስደት የሚመርጡበት ምክንያት ምንድነው? እውን መንግስት እንደሚለን ‘ቸግሯቸው ሳይሆን ባቋራጭ ለመበልፀግ ፈልገው ነው’? ወይስ የወላጆቻቸው የማዳበርያ ዕዳ ተሰደው ሰርተው ለመክፈል ነው?

Sunday, December 8, 2013

ወያኔ ቁጥርና ቀጠሮ አያውቅም

30ሺ አይሞሉም የተባሉት ስደተኞች ከ150ሺ በላይ ሆነዋል

ወያኔ እንደሚለው በየአመቱ ከ2ሚ. በላይ የስራ እድል ቢፈጠር፣ ከውጭ ሰራተኛ እናስመጣ ነበር፡፡
የአዲስ አበባ አስተዳደር ባለፈው ሳምንት ባሰራጨው ማስታወቂያ፣ በበርካታ አካባቢዎች ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ የውሃ አገልግሎት እንደሚቋረጥ ገልፆ ነበር፡፡ አዲስ መስመር ለማገናኘው ሦስት ቀን ሙሉ ውሃ ማቋረጥ፣ ግራ ያጋባል፡፡ ሁሉም ነገር ከተዘጋጀኮ፣ አዲሱን መስመር  በጥቂት ሰዓታት አገናኝቶ ሥራውን ማጠናቀቅ አያቅትም፡፡ ደግነቱ ቅዳሜ በቀጠሮው ውሃ አልጠፋም፡፡ እሁድ ግን ተቋረጠ። ሰኞና ማክሰኞም እንደዚያው፤ ረቡዕ  ሀሙስም… ትናንት አርብም አልመጣም፡፡ መንግስት ጋ ቀጠሮ አይሰራም፡፡ “የአገሪቱና የአህጉሪቱ መዲና” በምትባል ከተማ…ውሃ ከጠፋ ስድስት ቀን ተቆጠረ።

Saturday, December 7, 2013

ከሳውዲ ተመላሽ ዜጎች ንብረታቸው በጉምሩክ እንደተወሰደባቸው ተናገሩ


ህገወጥ ናችሁ ተብለው ከሳውዲ አረቢያ ወደ አገራቸው የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን፤ ለበርካታ አመታት ለፍተን ያፈራነውን ንብረት ይዛችሁ መግባት አትችሉም ተብሎ ተነጥቀናል፡፡ የፍተሻ ሰራተኞች ሻንጣዎቻቸውን በመፈተሽ፣ ሞባይል ከአንድ በላይ ከያዙ ትርፉን በማስቀረት፣ አዳዲስ አልባሳት እና ኤሌክትሮኒክስ ቁሰቁሶች የተወሰኑትን ብቻ በመፍቀድ እና ያመጡትን ወርቆች ግራም በመቀነስ ንብረታቸውን እየወሰዱባቸው እንደሆነ ተመላሾቹ ገልፀዋል፡፡ መሃመድ አባመጫ የተባለ የሳኡዲ ተመላሽ፤ ከሳውዲ ስድስት ሻንጣ ይዞ መምጣቱን ገልፆ፤ ቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ ግን ከሁለት ሻንጣ በላይ ይዞ መግባት እንደማይችል፣ ከአምስት ሞባይሎችም ሁለቱ ብቻ እነደተፈቀደለት ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡ የሳውዲ መንግስት ከአንድ ኪሎ በላይ ወርቅ ይዛችሁ መውጣት አትችሉም የሚል መመሪያ ማሳለፉን የጠቆመው ተመላሹ፤ ንብረቱን እዚያው ጥሎ ለመመለስ መገደዱን ገልጿል፡፡ የሳኡዲ መንግስት እንኳን ከወርቅ በስተቀር ሌላ ንብረታቸውን ሁሉ ይዘው እንዲወጡ መፍቀዱን የገለፀው መሃመድ፤ በአገራቸው ንብረታቸውን እንዳያስገቡ መከልከላቸው እንዳሳዘነው ይናገራል፡፡

በመዲናዋ ምስጢራዊ የወሲብ ገበያ ደርቷል

የትላልቅ ድርጅቶች ፀሃፊዎች፣ ሞዴሎችና ተዋናዮች አሉበት
ድንግልናን በ10ሺ ብር የሚያሻሽጡ ደላሎች ሞልተዋል
የከተማዋ ቱባ ባለሃብቶች “የአገልግሎቱ” ተጠቃሚዎች ናቸው
An hoping to survive. Looking for cheap sexሲኤምሲ ሣሚት ማዞሪያ አካባቢ ካሉት ዘመናዊ ቪላ ቤቶች በአንደኛው 12ሺ ብር ወርሃዊ ኪራይ እየከፈለች ትኖራለች፡፡ የምታሽከረክረው ኤክስኪዩቲቭ ቶዮታ፣ በየዕለቱ የምትቀያይራቸው እጅግ ውድ ዋጋ ያላቸው አልባሳቶቿና በየመዝናኛ ሥፍራው የምትመዘው ረብጣ ብር የተንደላቀቀ ኑሮ እንደምትመራ ይመሰክራሉ፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናትና መዲናችን አለማቀፋዊ ስብሰባዎችን በምናስተናግድበት ጊዜያት እሷን ፈልጐ ማግኘት የማይታሰብ ነው፡፡
ቦሌ ፍሬንድሽፕ ሕንፃ ላይ በከፈተችው ቡቲክ የምታገኘው ገቢ ይሄን ያህል ሊያዝናናት እንደማይችል የታወቀ ነው፡፡ ገቢ ወጪዋን አጥብቃ የማትቆጣጠርበትን ይህንኑ ቡቲኳን ታናሽ እህቷ ትውልበታለች፡፡ እሷም አልፎ አልፎ “ሥራ” በማይኖራት ጊዜ ብቅ እያለች ትጐበኘዋለች፡፡ ታናሽ እህቷ ቤተሰቡን ሁሉ ቀጥ አድርጋ የምታስተዳድረው እህቷ፤ ስለምትሰራው ምስጢራዊ ሥራ አንዳችም የምታውቀው ነገር ያለ አይመስልም፡፡ እሷ የምታውቀው ከተለያዩ የውጪ አገር ሰዎች ጋር የአየር ባየር ንግድ

Thursday, December 5, 2013

ሰበር አስዛኝ ዜና !!! ከወደ ደቡብ አፍሪካ !! ታላቁ አፍሪካዊ መሪ ክቡር ኒሰን ማዴላ ከዚህ አለም በሞት ተለዩን

ሰበር አስዛኝ ዜና !!! ከወደ ደቡብ አፍሪካ !! ታላቁ አፍሪካዊ መሪ ክቡር ኒሰን ማዴላ ከዚህ አለም በሞት ተለዩን ! BBC – South Africa’s Nelson Mandela dies
Mr Mandela, 95, led South Africa’s transition from white-minority rule in the 1990s, after 27 years in prison.
He had been receiving intense home-based medical care for a lung infection after three months in hospital.

Wednesday, December 4, 2013

ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወዳገራቸው የመመለስ ግዴታው የህወሃት/ኢህአዴግ ነው!

ኦባንግ ለቴድሮስ መልክት ላኩ

obang and tedros


ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን)
ኅዳር 23፣ 2006 ዓም
ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወዳገራቸው የመመለስ ግዴታው የህወሃት/ኢህአዴግ ነው!
ግልጽ ደብዳቤ ለሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ገ/የሱስ

Monday, December 2, 2013

የወያኔ አገዛዝ በመልዕክተኞቹ በኩል ላቀረበው የ“እንደራደር” ጥያቄ ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ምላሽ

ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የገነባዉ ሥርዓት በከፍተኛ ችግሮች የተወጠረ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመሪው ሞት በወያኔ መሀል ያስከተለው ቀውስ፤ የሕዝብ ሁለገብ ትግል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበት መሄድ የፈጠረበት ስጋት እና ምርጫ በደረሰ ቁጥር የሚደርስበት ጭንቀት መጨመር ተደማምረው ውጥረቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እያደረሱት መሆኑን የሚያሳዩ በቂ ምልክቶች አሉ። የእስካሁኑ ተሞክሮዓችን እንደሚያሳየው ወያኔ ውጥረት ሲበዛበትና መዉጪያና መግቢያዉ ሲጠፋዉ ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችን “እንወያይ፣ እንደራደር” በማለት ለውጥረት ማስተንፈሻ ጊዜ የሚገዛ መሆኑን ነው። ሰሞኑን በወያኔ አገዛዝ መልዕክተኞች በኩል የደረሰንን “የእንደራደር” ጥያቄ ንቅናቄያችን በዋናነት ያየው ወያኔ እንደለመደው ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻነት ለመጠቀም እየሞከረ መሆኑን ነው።

ሰበር ዜና ኢህአዴግ-ለግንቦት ሰባት የእንደራደር ጥያቄ አቀረበ።

ሰበር ዜና ወያኔ -ለግንቦት ሰባት የእንደራደር ጥያቄ አቀረበ። ኢሳት በምሽት የዜና እወጃው ዝርዝሩን ያቀርባል። ግን እናተ በቀቀኖች የናተን እንደራደር ተቀብሎ የነጻነት ትግሉን የሚያቆም ድርጅት አይደለም ግንቦት 7 ውስጥ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን የናተን ዘረኝነት እና ደደብነት ጠንቅቀው የሚያውቁ ሽንታም ያላቹህትን ህዝብ ያውረዳቹህትን ሀገር ያጠፍቹህትን ነጻነት ደረቴን ለአረር ብሎ ትግሉን የተቀላቀለ ኢትዮጵያዊ ነው የተሰባሰበበት ስለዚህም ሳትቆነጠጡ ላፈሰሳቹህት ደም ላጠፋቹህት ሀገር ቅጣታቹህን ሳትቀበሉ

Sunday, December 1, 2013

‹‹ድኅረ ምርጫ 97 በኢትዮጵያ ያለው ዲሞክራሲያዊ ምህዳር ጠቧል›› አና ጐሜዝ፣ የአውሮፓ ኅብረት የፓርላማ አባል

ምርጫ 97ን ተከትሎ የአውሮፓ ኅብረትን የምርጫ ታዛቢ ቡድንን የመሩት አና ጐሜዝ ምርጫውን ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ በኢትዮጵያ መንግሥትና በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ላይ የሰላ ትችትና ወቀሳ በመሰንዘር ይታወቃሉ፡፡
ከዘጠኝ ዓመታት ቆይታ በኋላ በ26ኛው የአፍሪካ፣ ካሪቢያን፣ ፓስፊክ እና የአውሮፓ ኅብረት የጋራ የፓርላማ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ የመጡትን አና ጐሜዝን በዴሞክራሲ፣ በእስረኞች አያያዝ፣ በሰብአዊ መብት አጠባበቅ እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ነአምን አሸናፊ አነጋግሯቸዋል፡፡

ከ“ፎርጅድ” ፖለቲከኞች፣ባለሥልጣናት፣ ፓርቲዎች፣ … ይጠብቀን!


ሰሞኑን ፖሊስ በቁጥጥር ሥር የዋለውን የፎርጅድ “ስፔሻሊስት” ጉድ ሰምታችሁልኛል? የመቶ ምናምን መስሪያ ቤቶችን ማህተም፣ ቲተር፣ ወዘተ… በመቅረፅ ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ (ሳይማሩ ድግሪ እኮ ነው!)፣ መንጃ ፈቃድ፣ የጋብቻ ሰርተፊኬት፤ ውክልና፣ ሊብሬና ሌሎች ሰነዶችን “ሲያመርት” መክረሙን የሰማሁት ከኢቴቪ የፖሊስ ፕሮግራም ነው፡፡ (ፎርጅድ በፎርጅድ ሆነናላ!) ይሄኛውን የፎርጅድ “ስፔሻሊስት” ከቀድሞዎቹ ልዩ የሚያደርገው ምን መሰላችሁ? ያልደፈረው የመንግስት መስሪያ ቤትና የግል ተቋማት የለም፡፡
(አይዞህ ያለው ማነው?) የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ የፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የግል ክሊኒኮች፣ የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲዎች፣ ወዘተ (የማን ቀረ ታዲያ!) ማህተሞችን … ፎርጅድ እየሰራ የተለያዩ ማስረጃዎችን ያቀርባል ወይም ይቸበችባል፡፡ (ፎርጅድ ፈላጊው “በሽ” ነው ማለት እኮ ነው!)