Saturday, December 14, 2013

የጠላቶቻችን ተግባርና፤የወዳጆቻችን ዝምታ

ደ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዳሉት ‹‹የጠላቶቻችንን ቃሎች ከምናስታውስ ይልቅስ የወዳጆቻችንን ዝምታ እናስበዋለን›› እኔ ደግሞ፤ የጠላቶቻችንን ተግባርና ግፋዊ ድርጊት እያሰብነው ይቅርታንም እንቸራለን የሚያደርጉትን አያውቁትምና፡፡ የሚፈጸመውን ግፍ፤የሕዝብ መብት ገፈፋ፤ የሰብአዊ መብት መጣስን፤የፍትህን እጠትና ሌላውንም ሁሉ እያዩ እነዳላዩ እየሰሙ እንዳልሰሙ በመሆን ጀሯቸውን የጠቀጠቁትን፤ አፋቸውን የለጎሙትን፤ አንደበታቸውን የዘጉትን ወዳጀቻችንን ግን ይቅርታም አልቸር ልረሳውም አልፈቅድም፡፡

በእስር ስር ያሉትን ዘወትር አብረናቸው እንዳለን ከማሳወቅና እንዳልረሳናቸውና እንዳልተውናቸው ከማሳየት የላቀ ምንም ተስፋ የለም፡፡ እስክንድር ነጋ አንዱዓለም አራጌ ርእዮት ዓለሙና ሌሎችም የግፍ ታሳሪወች በጨካኝና ግፈኛ ገዢ ዋሻ ውስጥ ናቸው፡፡ በየእለቱ ነፍሳቸው እንዲሳሳና እንዲንበረከኩ እየተደረጉ ነው፡፡ ይህን ደግሞ አንሰማውም ዋሸው ጥልቅ መዝጊያው ድርብ ነውና፡፡ ድምጻቸው ታፍኗልና ድምጻቸው ልንሆንና ልንጨህላቸው ይገባል፡፡ ያሉበት ቦታ የግፈኛው አገዛዝ የግፍ ዋሻ በትንፋገት የተሞላና ለበሽታ የሚያጋልጥ በመሆኑ ስቃያቸው ሊሰማን ተገቢ ነው፡፡ ስለኢትየጵያ የፐለቲካ እስረኞች ጉረሯችን እስከሰል መጨህ ያለብን ለታይታ
ሳይሆን፤ግዴታችን፤ክብራችን፤ትክክልና እውነትም በመሆኑ ነው፡፡ በመጨረሻም፤ የኢትየጵያ ፍጻሜ ሊሆን የሚገባው የግፍ ገዢዎችና ፈላጭ ቀራጮቹ እንደሚያስቡት ግልብነት አይደለም፤ ጭካኔ፤ግፍ፤ኢሰብአዊነት ሳይሆን፤ ያለሃጢአታቸው ለተዘጋባቸው ወገኖቻችን ክብር ስንል  በሰብአዊነት፤ በክብር፤በመደማመጥ፤ በመግባባት፤ በአንድነት መሆን አለበት፡፡ለዚህም ነው በአንድ ላይ እጅ ለእጅ በመያያዝ ላለመድከም ለራሳችን ቃል ገብተን፤ጥሪዎችን በማዳመጥ ብቻ ሳይሆን አዳምጦ በመቀላቀል፤ ያለ እረፍት በኢትዮጵያ ያሉትን የፐለቲካ እስረኞች የነጻነት መድረሻ ማፋጠን አለብን፡፡
በኢትዮጵያ ያሉ ሁሉም የፐለቲካ እስረኞች ይፈቱ!
የእትዮጵያ ነጳ ፕሬስ ነጳ ይሁን!
ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ:
source: EMF al-mariam-amharic

No comments:

Post a Comment