Wednesday, July 31, 2013

ንብረትነቱ የራሽያ የሆነ ሪኮፕተር ኢትዮጵያ ውስጥ ተከሰከሰ

_68494928_68494904

አራት ሰው ይዛ ከራሽያ የተነሳችው ሪኮፕተር ትራንዚታን ኢትዮጵያ በማደድረግ ነዳጅ ሞልቶ ጉዞዎን ወደ ጁባ በማድረግ የሜሽን ስራ ለመስራት ነበር የተነሳው ምክንያቱ ምን

መረጃ በጨዋታ፤ በዱባይ ኤንባሲያችን ሆኗል አሉ “ገዳይ”

burj_khalifa_aka_burj_dubai-wide

መረጃ በጨዋታ፤ በዱባይ ኤንባሲያችን ሆኗል አሉ “ገዳይ”
ዱባይ ሆይ የእህቶቻችን ሀገር እንደምን ነሽ… ለመሆኑስ እህቶቻችንን እንዴት ናቸው…በሻርጃ እና አቡዳቢ ጉያዎችሽ የደበቅሻቸው ጎረምሶችሽ በዚህ ሰዓት ምን እያሏቸው ይሆን… “ማዳሞችሽስ” ስንቷን የሀገሬ ሴት እየገላመጡ ስነቷንስ እያመናጨቁ ይሆን…
በፌስ ቡክ የመልዕክት ሳጥኔ አንድ መልዕክት መጣ፡፡ እንዲህ ይላል “በዱባይ ኤንባሲያችን እየሆነ ስላለው ነገር ልነግርህ ነበር” እኔስ ማነኝ፤ እስቲ አምጪው አልኳታ፤
በዩናይትድ አረብ ኢምሬት ዱባይ ኢትዮጵያ ኤንባሲ አሰራሩ ከይሲ ቢባል ይቀላል፡፡ እህቶቻችን ፓስፖርት ለማሳደስ ወይም ለአንድ ጉዳይ ወደ ኤንባሲ ደጃፍ ልክ ሲደርሱ የድሮ ቀበሌ አቀባበል ይደረግላቸዋል፡፡ ቀበሌ ትዝ ይልዎታል ወዳጄ… ዘበኛውም ሊቀመንበሩም እኩል ሰው የማመናጨቅ ስልጣን የተሰጣቸው ቦታ እኮ ቀበሌ ነው፡፡ (በነገራችን ላይ አሁን ግን ቀበሌ ተሸሽሏል፡፡ እኔ ሽሮሜዳን ትቼ “ልነካው” የነበረ ሰሞን ቀበሌ የሄደ ሰው የሚደረግለት እንክብካቤ… እንደው ያ ደህንነት ወዳጄ “ወግሞ” ባይዘኝ ኖሮ ለቀበሌያችን ፀባይ መሻሻል ስልስ እዛው ብኖር እመርጥ ነበር፡፡)

Tuesday, July 30, 2013

“ጴጥሮስ ያቺን” ቃል!


abunepetros1


ፋሺስቶች ያገራችንን አርበኞች ሽፍታ ቢሏቸው እውነት እንዳይመስላችሁ፡፡ ሸፍታ ማለት ያለ አገሩ መጥቶ የሰውን አገር የሚወር ይህ በመካከላችሁ መጥቶ የቆመ አረመኔው የኢጣሊያ ፋሺስት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለእርሱ እንዳይገዛ ውጉዝ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መሬት እንዳትቀበለው የተገዘተች ትሁን፡፡” አቡነ ጴጥሮስ፡፡
ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን ጀግናው ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስ በግፍ የተገደሉበት ቀን ነው፡፡ እኒህ ታላቅ አባት ለሰማዕትነት ያበቃቸው ዋናው ምክንያት በወቅቱ ለተጠየቁት ቀላል ለሚመስል ጥያቄ “ቃሌን አልክድም” ብለው በመቆማቸው ነበር፡፡

በወልድያ ከተማ 3 ሰዎች ተገድለው ተገኙ

ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ወኪል ከስፍራው እንደዘገበው ሁለቱ ሰዎች በአንድ ቦታ ላይ ተገድለው ተጥለው ሲገኑ፣ አንደኛው የተገኘው በተለየ ስፍራ ነው።

የሀዘን መግለጫ፣ አንድነት ፓርቲ በቁርጥ ሰዓት ጀግናውን ኢትዮጵያ ልጅን በማጣቱ ታላቅ ሐዘን ተሰምቶታል


ፍኖተ ነፃነት
አቶ ግርማ ወ/ሰንበት በ1984 ዓ.ም. መዐህድን በመመስረት፣ ህይወታቸው እስካለፈበት ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ ደግሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) የብሄራዊ ም/ቤት አመራር አባል በመሆን ታግለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በፓርቲያችን አንድነት ከፍተኛ አመራር ሰጭ በመሆን ሌት ተቀን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የኢትዮጵያን ህዝብ የነፃነትና የዴሞክራሲ ጥያቄን ለማሳካት ግንባር ቀደም አርበኛ በመሆን ሲታገሉ የቆዩ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጅ ናቸው፡፡

Monday, July 29, 2013

የዘመኑ መንፈስ (በእውቀቱ ስዩም)

በእውቀቱ ስዩም

ባገራችን ባሁኑ ጊዜ ብዙ ተከታይ ያለው ሃይማኖት ብሄርተኝነት ይባላል፡፡የብሄርተኝነት ምእመን ከሆንክ የነፍስ አባት ይኖርሀል፣በጭፍን የምትቀበለው ቀኖና ይኖርሀል፣ነገ የምትገባባት የተስፋ ምድር ይኖርሀል፣ከሁሉ በላይ ደግሞ ብርቱ ችግርህን የምትደፈድፍበት የመስዋእት በግ ይኖርሀል፡፡
ሃይማኖቶች ምእመናንን ብቻ ሳይሆን መናፍቃንንም ያፈራሉ፡፡ብሄርተኞች በስሜት የሚነድደውን ምእመን ብቻ ሳይሆን የኔ ቢጤውን መነፍቅም እንደሚያፈሩ አንርሳ፡፡በነገራችን ላይ ሃይማኖትን መካድ ማለት ሃይማኖት የሚያነሳቸውን አብይ ጥያቄዎች መካድ ማለት አይደለም፡፡እንዲሁም፣ ብሄርተኝነትን መካድ ማለት የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች ህልውና መካድ ማለት አይደለም፡፡በዚህ ጉዳይ ፣መናፍቅ መሆን ማለት፣ የብሄርተኛ ነቢያት ሰለ ጭቆና ስለ ነጻነት ብሎም ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚያቀርቡትን አጉል እምነት መጠራጠር ማለት ነው፡፡
ከኢትዮጵያዊነት እንጀምር፡፡
ከዘመናችን የብሔርተኝነት ነቢያት አንዱ ጃዋር መሐመድ በቅርቡ ከእንቁ መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለመጠይቅ ላይ ስለኢትዮጵያዊነት የሚከተለውን ይላል፡፡

Sunday, July 28, 2013

! …. የህወሓት የድሮ ታጋይ ‘አሸባሪ’ ተባለ

….! Abraha Desta

ስዒድ አሕመድ ይባላል። የድሮ የህወሓት ታጋይ ነው። በትጥቅ ትግሉ ወቅት የትግራይ ህዝብ ለትግሉ በማነሳሳትና ትግሉ በመምራት ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ግንባር ቀደም ሚና ተጫውቷል።
የደርግ ስርዓት ከተገረሰሰ በኋላ እንደሌሎች ታጋዮች ከውትድርና ተቀንሶ በግል ስራ ተሰማርቶ ህይወቱ ሲመራ ቆየ። ባለፈው ሓሙስ (ሓምሌ 18) የፌደራል ፖሊሶች የትጥቅ መሳርያው እንዲያስረክብ ይጠይቁታል። ስዒድ ደግሞ አሁን ምንም ዓይነት መሳርያ እንደሌለውና የድሮ ትጥቁ ደግሞ ከዓስር ዓመት በፊት በሕጋዊ መንገድ ለመንግስት አካላት ማስረከቡ በማስረጃ ያስረዳል። ፖሊሶቹም ‘በሽብር ተጠርጥረሃል’ በሚል ሰበብ ዓፍነው ይወስዱታል።

ካጠፋሁ ልጥፋ

ሎጎ

ካጠፋሁ ልጥፋ
ትላንት ማለዳ ኮምፒውተሬን ከፍቼ ከወዳጅ ዘመዶቼ ልገናኝ ወዲህ ወዲያ ስል ከዘመዶቼ አንዱ ስዎች ስለ እርሱ የሚሰጡትን አስተያየቶች አስመልክቶ ከአንድ የራዲዮ ጣቢያ ጋር ቃለ ምልልስ ሲያደርግ ሰማሁት፡፡ ታድያ ይህ ዘመዳችን አስተያየት ሰጪዎቹን በሙሉ እነዚህ ጠላቶቻችን ናቸው… የሚል አንድምታ ያለበት ንግግር ሲናገር ሰማሁ ለጠቅላላው ማህበረሰብ ይቺን ሀሳብ አንፀባረኩ፤
እኔ የምለው…
አስተያየት መስጠት እኮ ጠላትነት አይደለም፤ በዚች ምድር ላይ የማይተች ማንም የለም….! ተቺዎቻችንን በሙሉ በጠላትነት መፈረጅ ነውር ነው!
አይመስላችሁም… ?

Saturday, July 27, 2013

ትዝታ ዘ ባንዲራ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘቀዘቁት ባንዲራ

2012-03-02t171851z_319859376_gm1e83303nh01_rtrmadp_3_kenya

ትዝታ ዘ ባንዲራ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘቀዘቁት ባንዲራ
ትላንት በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ላይ ኢቲቪ አንድ ግለሰብ የሆነ ነገር ሲያውለበልብ አሳየንናተቃዋሚዎቹ  ለባንዲራ የሚሰጠውን ክብር በማንቋሸሽ የተቀዳደደ ባንዲራ ሲያውለበልቡ ነበር ብሎ አሳየን… 1ኛ … ያ ሰውዬ የተቃዋሚዎቹ ተወካይ ስለመሆኑ ምንም ማስረጃ የለም፡፡ 2ኛ የያዘው ነገር ባንዲራ ስለመሆኑም መለየት አልተቻለኝም… የሆነ ሆኖ… ይቺ ዜና ወሬ ከየት ትዝ እንዳለችኝ እንጃላቷ…  ድጋሚ አትሜያታለሁ….
ጤና ይስጥልጅ ወዳጄ እንዴት አሉልኝ። ጤና ኑሮ ሁሉ አማን ሁሉ ሰላም ነው? የኔ ነገር መቼም ሰሞኑን ሳቀርባቸው የነበሩ አጫጭር ጨዋታዎች ላይ አንድም ግዜ እንኳ ሰላም ሳልልዎት ቀጥታ ወደ ወሬዬ ስገባ “እንዴት ያለው ወሬኛ ወጥቶታል!?” ብለው ሳይታዘቡኝ አይቀሩም። ለዚህ ነው ዛሬም ሌላ ትዝብት ሳይከተለኝ ቀድሜ ሰላምታ ያቀረብኩት። “ምናለ ሁሉ ሰው እንዳተ ከጥፋቱ ቢፀፀት” ይበሉና ያኩሩኝ እንጂ…

ሰበር ዜና፣ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ቤት በፖሊሶች እየተበረበረ ነው

ብርበራው ቀኑን ሙሉ እንደሚደረግ ታውቋል

በደቡብ ወሎ ዞን በሀይቅ ከተማ የሚገኙ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ቤት ላይ ዛሬ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ብርበራ እንደተጀመረ የዞኑ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡
የአንድነት ፓርቲ የወረባቡ ወረዳ ሰብሳቢ አቶ እድሪስ ሰኢድ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት ዛሬ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ “የጦር መሳሪያ ሰውራችኋል” በሚል ፖሊሶችና ሚኒሻዎች በሀይቅ ከተማ ባሉ ከ16 በላይ በሚሆኑ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት መኖሪያ ቤት ውስጥ ብርበራ አካሂደዋል፡፡ ብርበራው ከተካሄደባቸው አመራሮች መሀከል አንዱ የሆኑት የወረዳው የአንድነት ፓርቲ የፋይናንስ ኃላፊ አቶ አራጌ ሑሴን ለሪፖርተራችን እንደገለፁት 5 ፖሊሶችና 1 ሚሊሻ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምረው መኖሪያ ቤታቸውን ፈትሸዋል፡፡ አቶ አራጌ ሁሴን አክለውም “እኔ ሰላማዊ ሰው ነኝ ምንም አታገኙም አልኳቸው፤እንዳልኩትም 2 ሰዓት የፈጀ ብርበራ አድርገውም አንዳች ሳያገኙ ወጥተዋል” በማለት ገልፀዋል፡፡

Dr. Wondimu says Semhal Meles deposits $5 billion

De Birhan

የመለስ ዜናዊ የመጀመሪያ ልጅ ሰመሃል መለስ ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኝ አንድ ባንክ ውስጥ 5 ቢሊዮን ዶላር በ2011 ኣስገብታለች። ይህን ያሉት እንግሊዝ አገር እሚገኙት ምሁር እና የመንግስት ተቃዋሚ የሆኑት ዶክተር ወንድሙ መኮንን ናቸው። ዶክተር ወንድሙ የቼኩን ኮፒ አያይዘው ለእንግሊዝ ፓርላማ ሃውስ ኦፍ ኮመንስ አቅርበዋል። ሙሉውን እዚህ ያገኛሉ
Semehal Meles Zenawi, the daughter of the late Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi
Semehal Meles Zenawi, the daughter of the late Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi, “has deposited $5 billion in one of the banks in New York”, said Dr. Wondimu Mekonnen, an academic and opposition figure, during a recent presentation at the House of Commons in the U.K.
Celebrity Net Worth site said Meles Zenawi got a net worth of $3 billion.
Semehal Meles Zenawi, the daughter of the late Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi
Wondimu also showed and distributed to the members of the House who attended his presentation, what he called a “copy of the cheque of the money” she lodged.
Celebrity Net Worth site said Meles Zenawi got a net worth of $3 billion. What a shame! That is wrong guys. Absolutely wrong. I have got a copy of a cheque signed by Semhal Meles Zenawi, the daughter of Meles Zenawi himself, depositing in one of the New York banks $5 billion. I have got and I will give you the copy. Don’t ask me how it came into our possession but that is a fact.

Friday, July 26, 2013

ስለተፈናቀሉ ሰዎች ሰማያዊ ፓረቲና መኢአድ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ አስገቡ

ከቤንሻንጉል-ጉምዝና ከደቡብ ክልሎች ለተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ጉዳይ መፍትሔ እንዲሰጡ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ የፃፉት ደብዳቤ ምላሽ አለማግኘቱን ሁለት ተቃዋሚ ፓርቲዎች አስታወቁ፡፡

የአርሶ አደሮቹ ጉዳይ መፍትሔ የሚያገኝ ከሆነ መንግሥትን ለመክሰስ በጀመሩት ሂደት እንደሚገፉበትም ተቃዋሚዎቹ መኢአድ እና ሰማያዊ ፓርቲ ጠቁመዋል፡፡
ሁለቱ ፓርቲዎች ለዚሁ ዓላማ በዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም የሚመራ የጠበቆች ቡድን ማዋቀራቸው ይታወሣል፡፡
ለተጨማሪና ዝርዝር የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬው ዘገባ አለው ያዳምጡ፡፡

Thursday, July 25, 2013

“ለዚህ (መንግሥት) ታላቅ ክብር አለኝ”

ሃይሌ! ወደ ፓርላማ?

haile gebreselasse


የዛሬ 10 ወር የሻለቃ ሃይሌ ገ/ሥላሴ ወደ ፖለቲካ የመምጣት ሁኔታን አስመልክቶ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ሃተታ አቅርቦ ነበር፡፡ (እዚህ ላይ ይመልከቱት) ሰሞኑን አትሌቱ ወደ ፖለቲካው የመግባት ፍላጎቱንና “በምርጫ” ለመወዳደር መፈለጉ ብዙ እየተባለበት ይገኛል፡፡ ከዚህ አንጻር አሁን ላለው ሁኔታ ግንዛቤ ይሰጣል በማለት ከዚህ በፊት ያቀረብነውን ሃተታ በድጋሚ አትመነዋል፡፡

“ለኢትዮጵያ የጥምር መንግስት ያስፈልጋታል” በማለት በ1997 ምርጫ አጥብቆ ሲከራከር የነበረውና በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ኢንቨስትመንት ውስጥ የገባው ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ በኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከነበሩት መንግስታትና ትውልዶች ይልቅ አሁን ላለው ትውልድ ከበሬታ እንዳለው በመግለጽ አስተያየቱን ሰነዘረ። የክብር ሪኮርዶቹን በሙሉ ለቀነኒሳ ያስረከበው ሃይሌ በእጁ የሚገኘውን ብቸኛ ሃብቱን (የህዝብ ክብር) እያሟጠጠ መሆኑ እየተገለጸ ነው።

ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሁለተኛ ዙር መዋጮ የመንግስት ሰራተኞች ፈቃደኛ አልሆኑም ተባለ

ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው አመት የወር ደሞዛችን በአመት ከፍለናል አሁን ግን ዳግመኛ ለመከፈል አቅሙ ስሌለለን እና እየተባባሰ የመጣውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም  ስለማንችል፣ ከእንግዲህ ወዲህ ገንዘብ ልንከፈል   የምንችለው ባገኘንበት  ጊዜ ብቻ ነው ” በማለት በአማራ ክልል የሚገኙ የመምህራን ማህበራት አስታውቀዋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ እንቅስቃሴ የወያኔን ቁንጮዎች ስጋት ላይ ጥሏል

ህዝብን ለማስፈራራት በታቀደ መለኩ እንደተለመደው የወያኔ ባለስልጣናት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ እጅግ ስላሰጋቸው የሰማያዊ ፓርቲ እንቅስቃሴ የሚከተለውን አስፍረዋል፣

ye semayawi party selamawi self
የሰማያዊው ፓርቲ ጥቁር ተግባራት
ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሕዝባዊ ሰልፍ ላይ ያቀረባቸው ጥያቄዎች የተሰላፊዎች ጥንቅርና መሰረታዊ ዓላማ በእጅጉ አነጋጋሪ ለሆኑ ጉዳዮች መነሻና መንደርደሪያ ሆነውኛል።
ሰማያዊ ፓርቲ ከአንድነት ፓርቲ ባለመስማማትና በልዩነት ራሳቸውን ያገለሉ፣ መርህ ይከበር በሚል ተሰባስበው የነበሩ ግለሰቦች የመሰረቱት ፓርቲ ነው፡፡ ወደ ኋላ ስንመለስም በ1997 ዓ.ም ቅንጅትን ከመሰረቱትና የከሸፈውን አመጽ በማስተባበርና በመምራት ከፊትና ከኋላ የነበሩ፤ ዛሬ ደግሞ የቀድሞውን ማንነታቸውን ሳይለቁ በአዲስ መልክና በአዲስ ኮፍያ ለመንቀሳቀስ እየሞከሩ ያሉ ናቸው፡፡

Wednesday, July 24, 2013

የፓርላማው ውይይት መታፈኑን በይፋ ያጋለጠው ጋዜጠኛ ከስራ ተሰናበተ


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈፃሚ ተቋማት ኃላፊነት” በሚል ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም ያደረገውን ውይይት በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በኩል ተቆራርጦና ተዛብቶ እንዲተላለፍ ተደርጓል በሚል አንድ ዜና መዘገቡ ይታወሳል።


ይህን ዜና በሰንደቅ ጋዜጣ የህዳር 5 ቀን 2005 ዓ.ም ዕትም “ኢቲቪ የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ውይይት በማፈን ተወቀሰ” በሚል ርዕስ ከቀረበ በኋላ፤ በዚህ ዘገባ ላይ ተመድቦ የሠራው የቀድሞ የኢቲቪ ባልደረባ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ ረቡዕ ህዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም በጉዳዩ ላይ ለዝግጅት ክፍላችን ምላሹን ሰጥቷል።

እነዚህ ዘገባዎች ከተስተናገዱ በኋላ፣ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ ለሰንደቅ ጋዜጣ መረጃ እንደሰጠና ሚስጢር እንዳወጣ ተቆጥሮ የዲስፒሊን ክስ ቀርቦበታል። ኢ.ሬ.ቲ.ድ በዲስፒሊን ክሱ ላይ  አራት ከፍተኛ የሥራ አመራሮች በምስክርነት ዘርዝሮ አቅርቧል። የድርጅቱ የዲስፒሊን ኮሚቴ በከሳሽ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እና በጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ መካከል የክስ ዝርዝር እና የመልስ መልስ ደብዳቤዎች ሲያዳምጥ ከሰነበተ በኋላ ግንቦት 9 ቀን 2005 ዓ.ም በቁጥር ቴ02.1/131-304/02/8/ በተፃፈ ደብዳቤ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ  ከግንቦት 10 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ከሥራ የሚያሰናብተውን ቅጣት አሳልፏል።

መንግስት ሕዝበ ሙስሊሙን ለማውገዝ የሠላም ኮንፈረንስ ጠራ

ሐምሌ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር  የሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላትን በማንቀሳቀስ አገር አቀፍ የሠላም ኮንፈረሰንስ ለማካሄድ መዘጋጀቱን ይፋ አደረገ፡፡

መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ እንደማይገባ ሕገመንግስቱ ቢደነግግም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በሕገመንግስት አስተምህሮ ስም የሃይማኖት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጭምር በማቋቋም የመብት ጥያቄ በማቅረባቸው ምክንያት የታሰሩና የሽብርተኝነት ክስ የቀረበባቸውን የሕዝበ ሙስሊም ማህበረሰብ አባላትና ደጋፊዎቻቸውን እንቅስቃሴ ለማፈን አሁንም
በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል ሲሉ አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የሙስሊም ጉዳዮች አስተባባሪ ለኢሳት ዘጋቢ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር “ሀይማኖቶች በሰላም አብሮ የመኖር እሴት በማጎልበትና ህገ-መንግስታዊ ድንጋጌዎችን በማክበር የሀገራችን ሕዳሴ ጉዞ ለማሳካት እንረባረብ” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ ከነሐሴ 21 – 23 ቀን 2005 ዓ/ም ድረስ የሃይማኖቶች የሰላም ኮንፈረንስ እንደሚያካሂድ ይፋ አድርጓል።
በዚህ ኮንፈረንስ የዘጠኙ ክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ክልል የሚካሄድና    በፌዴራል ደረጃ በሚካሄደው ኮንፈረንስ የሚጠናቀቅ ሲሆን ሰፊ የሕዝብ ንቅናቄ ይፈጥራል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጿል።

እስቲ ቂማችንን ጥቂት እናቆየው


ይህንን ርዕስ የመረጥኩት ያለምክንያት አይደለም፤ ከጠላት ጎን ተሰልፈው ንፁሃን ዜጎችን በጠራራ ፀሐይ ሲያስጨፈጭፍ አገር ሲሸነሽኑና የአገር ሀብት ዘርፈው ሕዝብ ለሕዝብ ሆድና ጀርባ አድርገው ሲያበቁ ሌላ ማሊያና ሜዳሊያ አጥልቀው ሲመጡ ርችት ተኩሰን ስለምንቀበላቸው የጭቃ ውስጥ እሾሆች ጥቂት ለማለት ነው።
ጨካኙን የወያኔ አምባገነን አገዛዝ ከድተውና አውግዘው የሚመጡትን ግለሰቦች ከመቀበልም አልፎ የተቃዋሚው ጎራ ፓርቲ አመራር ያደርጋቸዋል። አንድ ሰሞን ከበሮአቸውን እንደልቅላቸዋለን ጥቂት ቆይተው ያፌዙብናል፣ ያላግጡብናል፣ ያላዝኑብናል ተመልሰው ጓዳ ጎድጓዳችን ፈትሸው፣ ሰልለው አሰልለው ወደ ጨካኝ ጓደኞቻቸው ቤት ከብዙ መረጃዎቻችን ጋር ይመለሳሉ።
ወያኔዎች በተመሳሳይ መልኩ የሕዝብን ትግል ለከርሣቸው ለውጠው ተቀበሉን ያሉዋቸውን የአንድ ሰሞን መበሸሸቂያ አድርገው እንደሸንኮራ መጥጠው ይተፏቸዋል፣ እንደሲጋራ ቁራጭ ሜዳ ላይ ይጥሏቸዋል፣ የውሃ ላይ ኩበት ያደርጓቸዋል። አቶ ልደቱ አያሌውና ሟቹ መለስ ዜናዊን ወገባቸው እስኪንቀጠቀጥ አጎንብሰው ይቅርታ የጠየቁትን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አዛውንት እንደምሳሌ ብጠቅሳቸው ብዙዎች በሀሳቤ ይስማማሉ። እነዚህ ማፈሪያዎች ዛሬም አሉ በቴሌቪዥኑ መስታወት አይናቸውን በጨው አጥበው በተቃዋሚ ፓርቲ ስም ያላግጣሉ፣ እኛም ቂማችን ጥቂት አላቆየነውም፣ ጥቂቶቻችን ለይቅርታ ምክንያቶችን እንደረድርላቸዋለን። አዎ ዛሬም አይናችሁን ጨፍኑ እናሞኛችሁ እያሉን ነው።

Monday, July 22, 2013

በአንድ ሳምንት ሁለተኛ አደጋ!

“አውሮፕላኑ አየር ላይ እያለ ሊፈነዳ ይችል ነበር”

ethiopian


ከአዲስ አበባ ወደ አክሱም ይጓዝ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ረቡዕ ለት በጭንቅ እንዲያርፍ መደረጉ ተገለጸ፡፡ አደጋው ከአምስት ደቂቃ በፊት ቢከሰት ኖሮ አውሮፕላኑ አየር ላይ እያለ ሊፈነዳ ይችል እንደነበር ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡
78 መንገደኞችንና ሠራተኞችን አሣፍሮ ይጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ (Bombardier Q400) አውሮፕላን ከክንፎቹ በአንዱ ጭስ መነሣቱን የሚጠቁም ማስጠንቀቂያ በመደወሉ እጅግ አስጨናቂ በሆነ መልኩ እንዲያርፍ መደረጉን ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል፡፡ ጋዜጣው ስማቸው ከመግለጽ የተቆጠቡ ባለሥልጣንን ጠቅሶ እንደጻፈው አውሮፕላኑ ከማረፉ ከአንድ ደቂቃ በፊት የግራው ክንፍ እየጨሰ መሆኑን ማስጠንቀቂያው ማመልከቱንና አንዱ ሞተር ደግሞ እንደሚገባው ይሰራ እንዳልነበረ ገልጸዋል፡፡

Monday, July 15, 2013

የኦሮሞ ሙስሊሞችን የበላይነትን በኦሮሞ ክርስቲያን ና ኦሮሞ ባልሆኑ ሙስሊሞች ላይ ለመጫን የታለመ ድብቅ አጀንዳ ይፋ ሆነ

hqdefault

ጃዋር ማህመድ የተባለው ግለሰብ ባገኘው መድረክ ላይ ሁሉ በጣም የተሳሳቱ አዘናጊና አግላይ ንግግሮችን በማድረግ ይታወቃል :ባለፈው ወር በሙስሊም ኦሮሞች ስብሰባ ላይ በመገኘት የሰጠውም በጣም አደገኛ አስተያየት ብዙ ሰዎችን አስደንግጥዋል:: ጃዋር በንግግሩ ሙስሊሞች ያለኦሮሞ ነጻነት ሊሳካላቸው እንዳማይችልና የኦሮሞ ድል የ ሙስሊም ድል እንደሆነ ገልጽዋል::ክርስቲያን ኦሮሞዎችን እንዲሁም አማራና እንዲሁም ሌሎች ብሄሮችን ባገለለ መልኩ ጃዋር ጅቡቲ ና ሶማሊ ስላሉ ሙስሊሞች ሲናገር ተደምጥዋል:: የዘር ጉዳይና ሀይማኖት ሲደባለቁ ምን አይነት ችግር እንደሚፈጥሩ ያልተገነዘው ጃዋር በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የተወሳሰብ የህዝብ ግንኙንት ባላገናዘብ መልኩ በየመድረኩ ላይ የሚሰጣቸው ይተጣመሙና በውሸት ላይ ይተመሰረቱ አስተያየቶች ብዙ ኢትዮጵያውያን እያስቆጣ ይገኛል::

Saturday, July 13, 2013

ድሃው ሕዝብ ጉዳዩን ማስፈጸም አይችልም

"ጉቦኝነት 44% ሆኗል"

city


“ዕድገት”፣ “ትራንስፎርሜሽን”፣ “ህዳሴ”፣ “የመለስ ውርስ (ሌጋሲ)”፣ … በሚመሯት ኢትዮጵያ ሙስና እየከፋ መሄዱ ታወቀ፤ ከመቶ ሰዎች ውስጥ ከ40 በላይ የሚሆኑት ጉቦ የሚሰጡ መሆናቸውን አስታወቁ፡፡

Friday, July 12, 2013

በሮመዳን ጾም ጅማሮ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጠንካራ ተቃውሞ አሰሙ

ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በአንዋር መስጊድ ከፍተኛ ህዝብ በተገኘበት ተቃውሞ ተካሂዷል። መንግስት የለም ወይ፣ የሼክ ኑር ኢማም ግድያ ድራማ ነው፣ ድራማው ይብቃ፣      መሪዎቻችን ይፈቱ፣ መሀይም አይመራንም፣ በፍትህ እጦት ድፍን አንድ አመት መንግስት ራሱ ገዳይ ራሱ ከሳሽ፣ ።

ዛሬ በደሴ ‹‹የሼኽ ነሩአዊ ሐረካት›› ድራማ ቀረጻ በመንግስት ተካሄደ (ድምፃችን ይሰማም)

መንግስት የቱን ሕዝብ ነው ሊያታልል የሚሞክረው?
ከመንግስት ከፍተኛ የሚዲያ ዘመቻ ጀርባ ያለው ድብቅ አላማ ምንድን ነው?
ከሳምንት በፊት የተገደሉትና ምንም አይነት የአስከሬን ምርመራ (Autopsy) ሳደረግባቸው በችኮላ እንዲቀበሩ የተደረጉትን የሼኽ ኑሩን ግድያ መንግስት ባሰበው መልኩ ፖለቲካው ጥቅም ሊያፍስበት በመጣር ላይ ይገኛል፡፡ ይህን ለማሳካት እንዲቻለውም የተለመደውን ስልት በመጠቀም በደሴና አካባቢው በሚገኙ ከተሞች የግዳጅ ሰልፍ በማስወጣት በሚዲያዎች የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ያደረገ ሲሆን፣ በመንግስት ብዙሀን መገናኛዎች በተለይም በኢቴቪና በአዲስ ዘመን ከፍተኛ የማራገብ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ መንግስት በተጨማሪም በሚኒስቴር መስሪያቤቶች እንዲሁም በፓርቲ ደረጃ ትናንት መግለጫ አውጥቷል፡፡ መንግስት በዚሁ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻው በመቀጠል ሼኽ ኑሩአዊ ሀረከት ድራማን በዜናና በሌላ የፕሮግራም ፎርማት ለማቅረብ የሚረዳውን ቀረጻ አካሄዷል፡፡ ይህ ድራማም ተቀናብሮ ዛሬ ምሽት ወይም ከሰሞኑ ለማታለያነት ለሕዝብ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡Ethiopian Musilms
ይኽው ዛሬ በደሴ ከተማ ሰኞ ገበያ ባድራ ጊቢ በተለምዶ አጠራሩ ረሺድ መስጊድ አካባቢ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የድራማ ቀረጻ በከፍተኛ ጥንቃቄ በመካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን የድራማው ግብአት እንዲሆኑ እየተደረጉ ያሉትም የደሴ ከተማ ወጣቶች ናቸው፡፡ እንደምንጮች ዘገባ ሼኽ ኑሩ ከመገደላቸው በፊትና ከተገደሉም በኋላ የተያዙ የከተማው ሙስሊሞችን የዚሁ ወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ዝግጅት ሲደረግ የቆየ ሲሆን በዛሬው እለትም ይህንን ውንጀላ በድራማ መልኩ ሲቀርጹ ውለዋል፡፡ ቀረጻው በሚካሄድበት ቦታ ዛሬ ከፍተኛ ጥበቃ ሲደረግ የቆየ ከመሆኑም በላይ በአካባቢውም ማንም ዝር እንዳይል ተደርጓል፡፡

Tuesday, July 9, 2013

ዳዊት ከበደ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ (ወያኔ) ኢምባሲ

(ECADF) – ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተቃዋሚ ፖለቲከኞችና በተለይም በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ላይ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በማካሄድ የሚታወቀው የአውራምባ ታይምስ ኢዲተር ዳዊት ከበደ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ (የወያኔ ኢምባሲ) ሲገባ መታየቱን ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።

ሰኞ፣ ጁላይ 8፣ በዋሽንግተን ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በሗላ 4 ሰዓት ላይ ነው ዳዊት ከበደ ወደ ግርማ ብሩ ቢሮ ከሌሎች ካድሬዎች ጋር ሲገባ የታየው።
የዋሽንግተን ምንጮቻችን ጉዳዩን እንዳብራሩት ከሆነ የኢምባሲው ሰራተኞች አመሻሹ ላይ ወደየቤታቸው ሲሄዱ ያስተዋሉ ሲሆን ዳዊት ከበደ ግን ከገባበት ቢሮ ለሰዓታት ሲወጣ አልታየም።

Monday, July 8, 2013

በጋሞጎፋ ዞን በተነሳው ተቃውሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታሰሩ ብዙዎችም ተደበደቡ

ኢሳት ዜና :-እሁድ ሰኔ 30፣ 2005 ዓም በደቡብ ክልል በጋሞ ጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ በሰላም በር ከተማና አካባቢዋ የሚኖሩ ከ7 ሺ በላይ ነዋሪዎች፣ የታሰሩ መሪዎቻችን ይፈቱትልን የሚል ጥያቄያቸውን በወረዳ ጽህፈት ቤት ተገኝተው ለማቅረብ በተጓዙበት ወቅት የዞንና የወረዳ ፖሊሶች በነዋሪዎቹ ላይ ድበደባ መፈጸማቸውን 300 የሚሆኑትን   ደግሞ ማሰራቸውን ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል።

አንዳንድ ቤተሰቦች ለኢሳት እንደገለጹት ፖሊሶች እድሜያቸው ከ13 አመት በላይ የሆኑ ልጃገረዶችንና ወንዶችን ሳይቀር ከቤታቸው እያወጡ በመደብደብ አስረዋቸዋል።  አቶ ብርሀኑ የተባሉ ነዋሪ ፖሊሶች የፈጸሙት ድርጊት ጨካኝ በሚባለው የደረግ ስርአት ጊዜ እንኳን ያልታየ ነው ብለዋል ። የችግሩን አሳሳቢነት ለክልል ባለስልጣናት ለማስረዳት  አዋሳ ከሚገኙት የአገር ሽማግሌዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ መሰቦ ማዳልጮ  እንደተናገሩት ፖሊሶቹ እርምጃውን የወሰዱት ጥያቄያቸውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማቅረብ በመሰባሰብ ላይ በነበሩበት ጊዜ ነው ።

Saturday, July 6, 2013

በረከት ስምዖን አደጉ ወይስ ተገፉ?

ወርቅነህ ገበየሁ ለምን ወደ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት?

workneh and bereket


ሰሞኑንን ይፋ የሆነውን የአዲስ የሚኒስትሮችና የ”ከፍተኛ” ባለሥልጣናት ሹመት ተከትሎ ከውስጥም ከውጭም የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው። ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ሹመቱን ይፋ ከማድረጋቸው በፊት ሪፖርተር “ምንጮቼ ነገሩኝ” በማለት አቶ በረከት ስምዖንን የደህንነት አማካሪ ሚኒስትር የሚያደርጋቸው አዲስ ሹመት እንደሚሰጣቸው ዘግቦ ነበር። ይህንኑ ዜና ተከትሎ “ኢትዮጵያ በኦፊሴል በኤርትራ መመራት ጀመረች” በማለት ቅድመ አስተያየት የሰነዘሩ ጥቂት አልነበሩም።
ሚዲያውን መዳፋቸው ስር አኑረው የቆዩት አቶ በረከት ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትርነታቸው ተነስተው የጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም የፖሊሲና ጥናት አማካሪ ሚኒስትር ተደርገው መሾማቸው “በረከት አደጉ ወይስ ተገፉ?” የሚል ጥያቄ አስነስቷል።

Wednesday, July 3, 2013

የብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አዋጅ ጸደቀ

ኢሳት ዜና :-በሚኒስትር ማእረግ ደረጃ እንዲቋቋም የታሰበው የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት መ/ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ከአንድ ሳምንት ዕይታ በኋላ ዛሬ ለፓርላማው ቀርቦ እምብዛም ውይይት ሳይደረግበት መጽደቁ ታውቋል፡፡

የኣመቱ ሥራውን ሰኔ 30 የሚያጠናቅቀውና ለዕረፍት የሚዘጋው ኢህአዴግ መራሹ ፓርላማ በተጣደፈ አሰራር ያጸደቀው በዚሁ አዋጅ መሰረት የሚቋቋመው መ/ቤት መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የመተንተንና የማቅረብ እና የደህንነት አገልግሎት የመስጠት እንዲሁም በአገር ውስጥ የጸረ ሸብርተኝነት እና የበረራ ደህንነትን የማስጠበቅ ሥራዎችን በኃላፊነት ይሰራል።

ሩሲያ ተዋጊ ጄቶችን ለኢትዮጵያ ለመሸጥ እየተደራደረች ነው

ኢሳት ዜና :-አር አይ ኤ የተባለው የዜና ማሰራጫ የሮስቦሮን ኤክስፖርት አርምስ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑትን አሌክሳንደር ሚካሄቨን ጠቅሶ እንደዘገበው ሩሲያ 18 ኤስ ዩ 30 ከ የተባሉ የጦር ጄቶችን ለኢትዮጵያ ለመሸጥ በድርድር ላይ ናት።

ለጅምላ ጭፍጨፋ ህጋዊ ሽፋን?

በእስከ ነጻነት
  • ሰሞኑን በጣም እጅግ በጣም አስደናቂ፣ አስገራሚና ዘግናኝ ዜናዎች እየተሰማ ነው።
  • በርግጥ ለትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር አዲስ ነገር አደለም ሊሆንም አይችልም።
የህወሃትን ባህርይ ለምናውቅና የነጻውን አለም ህይወትና ሰብአዊ መብት አክብሮት ለቀመስነው ግን በጣም እጅግ በጣም የሚያስገርም፤ የሚያስደነግጥ: ከዚያም አልፎ  ይህን መቀበልና መዚህ መቀጠል አንችልም  ወያኔ ካልጠፋ ስራም: ኑሮም፤ ትምህርትም እምነትም የለም ክተት የሚያሰኝ ነው:

Tuesday, July 2, 2013

መንግስት በእስራኤል አገር የሰለጠኑ የደህንነት ሀይሎችን አሰማራ

ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የብሄራዊ ጸጥታና  ደህንነት መስሪያ ቤት በእስራኤል አገር በታል አራድ ኔጊቭ ማሰልጠኛ ጣቢያ ያሰለጠናቸው  987 የደህንነት ሰራተኞች በመላ አገሪቱ በሚገኙ 572 ታላላቅ መስጊዶች እና በቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት ማሰማራቱን ከደህንነት መስሪያ ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል ፡፡

ከሰልጣኞች መካከል 11 ዱ ብቻ የእስልምና እምነት ተከታዮች ሲሆኑ ቀሪዎቹ አረብኛ  አቀላጥፈው የሚናገሩ ፣ ቁራንን በስርዓት የተማሩ እና እስልምናን ስርዓቶች ሙሉ በሙሉ የሚፈጽሙ ናቸው፡፡
ቀሪዎቹ ሰልጣኞች በቴሌ ኮሚኒኬሸን መስሪያ ቤት የተመደቡ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ በስልክ ጠለፋ  ስራ ላይ ይሰማራሉ፡፡ ከሰልጣኞች መካከል 631 ዱ የትግራይ ብሄር ተወላጆች ሲሆኑ፣ በትምህርት ደረጃም የ2002 ምሩቃን በብዛት ይገኙበታል።

በሰዉ ድርቅ የተመታዉ የቦንድ ምንተፋ በተቃዋሚዎች የድምጽ ማእበል እየታመሰ ነበር

አትላንታ ጆርጂያ፥

ሳዲቅ አህመድ
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራን የሚያዉለበልቡ ብቻ ሳይሆን የለበሱም ነበሩ።የኢትዮጽያ መንግስት አባይን ለመገደብ በሚል ስም ቦንድን ለመመንተፍ የሚያደርገዉን ሴራ እንቃወማለን አባይ ከመገደቡ በፊት ነጻነት፣ ዲሞክራሲ፣ ፍትህ ለመላዉ ኢትዮጵያን ያሻል በማለት በዘር በሃይማኖት ሳይለያዩ እስከ 200 የሚደርሱ ሰዎች ድምጻቸዉን ያሰማሉ።
Protest in Atlanta, Georgia
ቁጥራቸዉ የተመናመነ ግለሰቦች ሃፍረት በተሞላበት መልኩ ወደ አዳራሹ ቢያመሩም ከመካከላቸዉ አንዳንዶቹ አንዳንዶቹ  በአልሞት ባይ ተጋዳይነት የሟቹን መለስ ዜናዊ ቲሸርት በመልበስ ቢንጎማለሉም በፍርሃት እየነፈሩ መሆናቸዉ ግን ያስታዉቅ ነበር። “ተከብረሽ የኖርሽዉ ባባቶቻን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይዉደም” በማለት ኅብረ-ዜማን የሚያሰሙት ኢትዮጵያዉያን “ተመልከቱ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ዝግጅት ቢያዘጋጁም የኢትዮጵያን ባንዲራን ለማዉለብለብ ግን ፍላጎቱ የላቸዉም! እኛ ግን በአባይ ስም አትነግዱ ስንላችዉ የኢትዮጵያን ባንዲራ እያዉለበለብን ነዉ” ይላሉ።
Ethiopians Protest in Atlanta, Georgia
“እኛ  ኢትዮጵያዉያን ነን ወደ አዳራሹ ለመግባት የዘር መለዮ ሳይሆን  ኢትዮጵያዊ ማንነት ነዉ የሚያሻን” ብሉዉ ለመደራደር ቢሞክሩም አዘጋጆቹ የአባይ ጉዳይ በዘር የተደለደለ እንዲመስል አድርገዉታል። ያም ሆኖ ቁጥራቸው ከሰላሳ የሚያንሱ የቦንድ ተመንታፊዎች በሰአት 400 ዶላር በሚከፈልበት አዳራሽ ዉስጥ ሲገቡ ተስተዉሏል። በአዳራሹ ዉስጥም መዝጋቢ ሰዉ እንደሌለ ፣እንኳን ደህና መጣቹ ባይ እንዳልነበረ አንድ በተክለ ሰዉነቱ የስብሰባዉን አዘጋጆች የዘር መስፍርት የሚያሟላ ልቦናዉ ግን ለኢትዮጵያዊነቱ የጸና ግለሰብ ዉስጥ ገብቶ የታዘበዉን ገልጿል።
Rally in Atlanta, Georgia
በተገቢዉ መልኩ ጥናት ያልተደረገበት አባይን የመገደቡ ሙከራ የዲፕሎማሲና የደህንነንት አደጋ አለዉ፤ ስልጣንን ለማራዘምና አቅጣጫን ለማስቀየር በሚደረግ ደፋ ቀና ነዉ አባይን መገደብ በሚል ስም የኢትዮጵያ መንግስት የሚንቀሳቀሰዉ የሚሉ ተቺዎች ብዙ ናቸዉ። ባንጻሩ አባይ አሁን አይገደብ የሚሉት ፖለቲካውዊ ክፋት የተጠናወታችዉ ናቸዉ በማለት የኢትዮጵያ መንግስት ለማጣጣል ይሞክራል። አንድ የጋራ እዉነታ ግን አለ  በአባይ የመገደብ ጉዳይ ኢትዮጵያዉያን የተለያየ ሃሳብ የላችዉም! ህዝባዊ ዉክልና የሌዉ ህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ያላዋቂ ሳሚ ምን ይለቀልቃግድቡን   አያርገዉ  ባዮች ቢኖሩ እንጂ…
ጁን 30 በሰዉ ድርቅ የተመታዉ የአትላንታ ጆርጂያ የቦንድ ምንተፋ ሂደት ክዉ ድንግጥም ያለ ነበር።