Monday, October 28, 2013

አደባባዩ ምን ያህል ይርቃል? – ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ


እነሆ ይቺ ሀገር ኢትዮጵያ ናትና የመብት (የለውጥ) ጥያቄዎች፣ እንደ አህጉር ተጋሪዎቿ ሁሉ መልስየሚያገኙት ከአደባባይ ጩኸት ብቻ ይሆን ዘንድ ባህል ሆኖአል፡፡ ትውልድ ተሻጋሪ ታሪኳም የሚነግርህ  በየወቅቱ ከተፈራረቁ ገዥዎቿ አንዳቸውም እንኳ ለህዝብ ፍላጎትና ውሳኔ ተገዝተው አለማወቃቸውን ነው፤ ጠመንጃ አሊያም ተፈጥሮ ወደ ግብአተ መሬት ካልሸኛቸው በቀር፡፡ የሩቁን (የጨለማውን ዘመን) ትተን፣ የቅርቡን እንኳን ብንመለከት በወጡበት መንገድ፣
ቁልቁል ተምዘግዝገው መውደቃቸውን መረዳቱ አይቸግርም፡፡ አዛውንቱ አፄ ኃይለስላሴ፣ ‹‹ቆራጡ›› ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም እና ‹‹ታጋዩ›› አቶ መለስ ዜናዊ እጅ የሰጡት ለህዝብ ፍላጎት ሳይሆን ለጠመንጃና ለተፈጥሮአዊ ኃይል ነው፡፡የሶስቱም የአመፃ ‹‹የዳቦ ስም›› ደግሞ ተመሳሳይ ነበር፡- ‹‹ለሀገርና ህዝብ ጥቅም››፡፡

No comments:

Post a Comment