Friday, January 24, 2014

የእነ አንዱዓለም አራጌ ቀጠሮ ተምታታ

ፍርድ ቤቱ ለጥር 30 ቀጥሯቸዋል፤ ሬጅስትራር በበኩሉ ጥር 24 ቀን 2006ዓ.ም መቅረብ አለባቸው ይላል፤

በነአቶ አንዱአለም አሬጌ ስም ያለው የክስ መዝገብን በሚመለከት በፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከተከሳሽ ጠበቆችና ከቤተሰቦች ጋር ብንቀርብም ፍርድ ቤቱ ቀጠሮው ትላንት ስለ ማለፉ ተናግሯል። የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው አጀንዳቸው ላይ የያዙት ዛሬ ጥር 16 ቀን 2006 ዓ.ም መሆኑን ቢገልፁም በዳኛ አዳነ ንጉሴ፣ ዓሊ መሐመድ፣ አልመው ወሌ እና ሙስጠፋ አህመድ የተሰየመው ችሎት በበኩሉ የቀጠሮው ቀን ትላንት ማለፉን ተናግረዋል።

ችሎቱ ቀጠሮው ዛሬ እንኳ ቢኆን መዝገቡ እጅግ ሰፊ በመሆኑ ውሳኔው እየተጻፈ በመሆኑ ምክንያት ለጥር 30 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲቀርቡ አዟል። በሌላ በኩል የፍርድ ቤቱ ሬጂስትራር ቀጠሮው ዛሬ መሆኑን አምኖ ነገር ግን ለከሳሽ አቃቤ ህግ መጥርያ ያልተላከ በመሆኑ ለአቃቤ ህግ ድጋሚ ትዕዛዝ ለማፃፍ ጥር 21 ቀን 2006 ዓ.ም ችሎት እንድቀርቡ አዟል። ከሬጂስትራሩና ከፍርድቤቱ ቀጠሮ የትኛው ትክክል እንደሆነም ለማወቅ አልተቻለም።
በሌላ በኩል አንድነት ፓርቲ ለክትትል ያመቸው ዘንድ የእስክንድር ነጋን የሰበር ሰሚ ይግባኝ ለማጣራት ሙከራ ቢያደርግም በእስክንድር ስም የቀረበ አንዳችም ይግባኝ እንደሌለ ሬጂስትራሩ አረጋግጧል። ባለቤቱን ጨምሮ ሎሎች አስተያየት ሰጪዎች ግን እስክንድር ያለ ጠበቃ ለመከራከር ይግባኝ ማለቱን አምነዋል። መንግስት ለአቶ አንዱአለም አራጌ ያቆማቸው ጠበቃና በሽብር ድርጊት ተጠርጥረዋል የተባሉትን ሰዎች ክስ የመሰረተው የመንግስት ዓቃቤ ህግ ከሀገር መሰደዳቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment