Friday, January 24, 2014

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከ250 በላይ ሰዎችን አሰረ

ኢሳት ዜና :-ኮሚሽኑ ተጠርጣሪዎቹ የተሳሩት በአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለከተሞች በመኪና ስርቆት፣ ማጅራት በመምታትና ሌሎች ወንጀሎች መፈጸማቸውን ጥናት ካካሄድኩ በሁዋላ ነው ብሎአል።

ተያዙ የተባሉት ተጠርጣሪዎች ፍድር ቤት ስለመቅረባቸው ኮሚሽኑ ያስታወቀው ነገር የለም።

በአዲስ አበባ ውስጥ ከጊዜወደ ጊዜ ሚታየው ስርቆት ነዋሪዎች ማስመረሩን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በከተማዋ ውስጥ ዘመናዊ ስለኮችን በአደባባይ መያዝ፣ ውድ ጌጣጌጦችን አድርጎ መጓዝ አደጋ እየሆነ መምጣቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ። አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ፖሊስ እስከዛሬ ዝም ብሎ ቆይቶ አሁን አርምጃ መውሰዱን ከምርጫ ቅስቀሳ ጋር ሲያይዙት ሌሎች ግን ቢረፍድም ይሻላል ይላሉ።
ዘጋቢያችን እንደሚለው አንድአንድ አስተያየት ሰጪውም መንግስት በመጪው ምርጫ ሁከት ይፈጥራሉ ብሎ የሚያስባቸውን ሰዎች በወንጀለኛ ስም ማሰር መጀመሩም ሊሆን ይችላል በማለት አስተያየት ይሰጣሉ።

No comments:

Post a Comment