Tuesday, July 9, 2013

ዳዊት ከበደ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ (ወያኔ) ኢምባሲ

(ECADF) – ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተቃዋሚ ፖለቲከኞችና በተለይም በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ላይ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በማካሄድ የሚታወቀው የአውራምባ ታይምስ ኢዲተር ዳዊት ከበደ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ (የወያኔ ኢምባሲ) ሲገባ መታየቱን ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።

ሰኞ፣ ጁላይ 8፣ በዋሽንግተን ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በሗላ 4 ሰዓት ላይ ነው ዳዊት ከበደ ወደ ግርማ ብሩ ቢሮ ከሌሎች ካድሬዎች ጋር ሲገባ የታየው።
የዋሽንግተን ምንጮቻችን ጉዳዩን እንዳብራሩት ከሆነ የኢምባሲው ሰራተኞች አመሻሹ ላይ ወደየቤታቸው ሲሄዱ ያስተዋሉ ሲሆን ዳዊት ከበደ ግን ከገባበት ቢሮ ለሰዓታት ሲወጣ አልታየም።

ዳዊት ከበደ በባለቤትነት ያስተዳድረው የነበረው “የአውራምባ ተይምስ ጋዜጣ” ባልደረቦች በወያኔ ቁንጮዎች የሀሰት ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ቤት በመሰቃየት ላይ እያሉ ነው ወደ አሜሪካን ሀገር ቪዛ ተመቶለት የወጣው። ሁኔታው በአንዳዶች ላይ ጥርጣሬን አጭሮ የነበረ ሲሆን፣ ይባስ ብሎ ዳዊት ከበደ አወጣጡን በተመለከተ የሚናገረው የተጣረሰ ታሪክ ይበልጥ እንዲጠራጠሩት አድርጓቸዋል።ዳዊት ከበደ እየበራ ነው እየጠፋ!?
በቅርቡ እየወጡ ባሉት መረጃዎች መሰረት ዳዊት ከበደ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) የመቀጠር ፍላጎት አሳይቶ የነበረ ሲሆን.. በተለያዩ ምክንያቶች ጥያቄው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
ይህ በዚህ እንዳለ “አለማቀፉ የበቃ ንቅናቄ በኢትዮጵያ” (BEKA – Global Civic Movement for Change in Ethiopia) ዳዊት ከበደ በውይይት መድረኩ እንዳይሳተፍ መታገዱን ለአባላቱ ባሰራጨው ደብዳቤ አሳውቋል።
የበቃ ንቅናቄ ባሰራጨው ደብዳቤ ጨምሮ እንደገለጸው ከሆነ፣ ከወራት በፊት ዳዊት ከበደ በአንድ የተቃዋሚ ፖለቲከኛ መኖሪያ ተጋብዞ በተገኘበት ወቅት በግብዣው ላይ የተገኙትን እንግዶች ተደብቆ ቪዲዮ ሲቀርጽ ተይዟል።

No comments:

Post a Comment