Tuesday, July 30, 2013

በወልድያ ከተማ 3 ሰዎች ተገድለው ተገኙ

ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ወኪል ከስፍራው እንደዘገበው ሁለቱ ሰዎች በአንድ ቦታ ላይ ተገድለው ተጥለው ሲገኑ፣ አንደኛው የተገኘው በተለየ ስፍራ ነው።

ሰዎቹ በምን ምክንያት ተገድለው እንደተገኙ ለማወቅ አሳት ወደ አኳባቢው ፖሊስ  በመደወል ላቀረበው ጥያቄ፣ ፖሊስ ሰዎቹ ተገድለው መገኘታቸውን አረጋግጦ፣ ስለአሟሟታቸው ምክንያት ማጣሪያ እያደረገ መሆኑና ምርመራውንም እንደጨረሰ መረጃውን ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል።
ኢሳት በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱት ዝርዝር ሪፓርቱን በስፋት  ያቀርባል።

No comments:

Post a Comment