ካጠፋሁ ልጥፋ
ትላንት ማለዳ ኮምፒውተሬን ከፍቼ ከወዳጅ ዘመዶቼ ልገናኝ ወዲህ ወዲያ ስል ከዘመዶቼ አንዱ ስዎች ስለ እርሱ የሚሰጡትን አስተያየቶች አስመልክቶ ከአንድ የራዲዮ ጣቢያ ጋር ቃለ ምልልስ ሲያደርግ ሰማሁት፡፡ ታድያ ይህ ዘመዳችን አስተያየት ሰጪዎቹን በሙሉ እነዚህ ጠላቶቻችን ናቸው… የሚል አንድምታ ያለበት ንግግር ሲናገር ሰማሁ ለጠቅላላው ማህበረሰብ ይቺን ሀሳብ አንፀባረኩ፤
እኔ የምለው…
አስተያየት መስጠት እኮ ጠላትነት አይደለም፤ በዚች ምድር ላይ የማይተች ማንም የለም….! ተቺዎቻችንን በሙሉ በጠላትነት መፈረጅ ነውር ነው!
አይመስላችሁም… ?
አስተያየት መስጠት እኮ ጠላትነት አይደለም፤ በዚች ምድር ላይ የማይተች ማንም የለም….! ተቺዎቻችንን በሙሉ በጠላትነት መፈረጅ ነውር ነው!
አይመስላችሁም… ?
ታድያልዎ በዚች አስተያየት ስር ስለራሴው የተሰራ በምስል እና ድምፅ ያጌጠ ሌላ አስተያየት አየሁ…. የሚያደንቁንን ብቻ ሳይሆን የሚነቅፉንንም መስማት እና ማሰማት ተገቢ ነውና፤ እስቲ ላጋራዎ ወዳጄ…እግረ መንገድም ነቀፋው አግባብ ነው ወይስ አግባብ አይደለም የሚለውን ያየው እንዲፈርድ ያደርጋል፡፡
ስለዚህ እባክዎ ወዳጄ በዚህ ቪዲዮ ላይ የተሰጡኝን አስተያየቶች ይመልከቱ እና እርስዎም ይጨምሩልኝ…. ይህ አስተያየት የብዙሃኑ ከሆነ፤ “ብዙሃን ይመውዕ” እንዲል መፅሀፉ…! መቼስ ማል ጎዳኒ…. ብዬ ይቅርታ ከመጠየቅ ውጪ ምርጫ የለኝም… የእኛ ሰፈር ሰው ካጠፋሁ ልጥፋ ይላል፡፡
እውነቱን ለመናገር በዚህ ቪዲዮ ላይ የተሰጠኝ አስተያየት ከጠላትነት የመጣ አይመስለኝም ያልኩትን በቅጡ ካለመረዳት ነው፡፡ እስቲ ዱዓ አድርጌ በዚህ ጉዳይ ላይ እመለስበት እና ያልኩትን በአግባቡ ለማስረዳት እሞክራለሁ!
እስከዛው ግን የተባልኩትን እነሆ…
No comments:
Post a Comment