በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ሄዶ ሰርግ ለማድረግ እቅድ ነበረው ኢትዮጵያዊው ዮሴፍ ቱሉ እንደ ቴክሳሱ ፋክስ 4 ቴሌቭዥን ዘገባ። የ30 ዓመቱ ዮሴፍ በጋዝ ስቴሽን ሥራ ተግቶ የሚሰራው ሃገር ቤት ሄዶ የሚመሰርተውን ትዳር በማሰብ፤ በወግ ማዕረግ መዳርን ነበር። በተለምዶ 7/11 በሚባለው ጋዝ ስቴሽን ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራው ዮሴፍ ረዥም ህልም ያለው ዜጋ ነበር።
እንደ ወዳጆቹ ገለጻ ከሆነ ዮሴፍ መልካም፤ ተግባቢና ረዥም ህልም የነበረው ሰው ነበር። ሆኖም ግን በሚሰራበት ጋዝ ስቴችሽን በጥይት ተመትቶ ተገድሎ ሕይወቱ አለፈ። ሃገር ቤት ሄዶ ወዳጅ ዘመዱን ሊያኮራበት የተዘጋጀው ትዳርም ህልም ሆኖ ቀረ። ይህ ነገር ብዙ ወዳጆቹን እና ዘመዶቹን የበለጠ ሃዘኑን እንዳባሰባቸው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ጠቁመዋል።
የ30 ዓመቱን ኢትዮጵያዊ እዚሁ ሰሜን አሜሪዓ.ምካ የቴክሳስ ግዛት ውስጥ እንደገደለ በፖሊስ ተጠርጥሮ የተያዘው ከልተን ጃን የተባለው ወጣት የ18 ዓመቱ ሲሆን፤ በጋዝ ስቴችኑ ውስጥ የተገጠመው ካሜካ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያውን ካሸር ትናንት ማክሰኞ ጃንዋሪ 21 ቀን 2014 ሊገድል ሲገባ በቁመቱ ልክ የሆነ መሳሪያ ታጥቆ ነው። ወጣቱ ተጠርጣሪ ገዳይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ቢውልም፤ ጠመንጃውን ይዞ የፈለገውን ገንዘብ ቢወስድም በቅርቡ ወደ ሃገሩ ገብቶ ሰርግ ለማድረግ ገንዘብ እያጠራቀመ የሚገኘውን ዮሴፍ ቱሉን ከመግደል አልተመለሰም።
የጋዝ ስቴሽኑ ባለቤቶች የኢትዮጵያዊውን አስከሬን ወደ ሃገር ቤት የሚመለስ ከሆነ ወጭውን ለመቻል ፈቃደኛ ሲሆኑ ገዳዩ የ1 ሚሊዮን ቦንድ ተጠይቋል።
ዘ-ሐበሻ ፎቶዎቹን ያገኘችው ከፋክስ 4 ቲቪ መሆኑን ትገልጻለች።
No comments:
Post a Comment