Saturday, November 30, 2013

እስራኤል ስደተኞችን ከሃገሯ አስወጣለሁ አለች:: ኢትዮጵውያኑም የገፈቱ ቀማሽ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡


Israeli immigration officers escort an African migrant in south Tel Aviv
እስራኤል ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 60ሺህ የሚጠጉ አፍሪካውያን ስደተኞችን ከሃገሯ እንደምታስወጣ ያስታወቀች ሲሆን በህገወጥ መንገድ በሊቢያ የሚኖሩ ከ120 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ወደ ሃገራቸው ይመለሳሉ ተብሏል፡፡ የእስራኤል ካቢኔ ባለፈው እሁድ ስደተኞቹን የሚያስወጣ አዲስ ህግ ካፀደቀ በኋላ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያዊን ኔትያሁ፣ ህገወጥ ስደተኞቹን ከሀገራቸው እንደሚያስወጡ አስታውቀዋል፡፡
የአገሪቱ ካቢኔ ባፀደቀው መመሪያ መሰረት እስራኤል

Friday, November 29, 2013

ከቤሩት የተሰማ አሰቃቂ መረጃ (ይህን ቪድዮ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ እንዲያዩት አይመከርም)

የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም! (ግንቦት 7)

በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሁንም መከራና ስቃይ ላይ ናቸው። የደረጃ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተንሰራፋ ነው። በመላው አለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ካለማቋረጥ ያደረገው ወገንና ሀገር አኩሪ ጩኸትና አቤቱታ ችግሩ በአለም ዙሪያ ትኩረት እንዲያገኝ ባያደረግ ኖሮ የወገኖቻችን መከራ ከዚህም በከፋ መልክ ይቀጥል እንደነበር ጥርጥር የለውም። አንድ ቀን እንኳን ለሚገዛው ህዝብ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ተሰምቶት የማያውቀው የወያኔ ጉጅሌ መንግስት እግሩን እየጎተተ ቢሆንም ወደ ችግሩ አቅጣጫ እንዲመለከት የተገደደው በዚሁ የወገን ጩኸት መሆኑ ግልጽ ነው።

የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ከተቃዋሚዎችን ጋር ተወያዩ

ለአውሮፓ፣ ኤዥያ፣ ካሪቢያን፣ፓስፊክና አፍሪካ ጉባኤ አዲስ አበባ የተገኙት የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች በቢሮአቸው ከተቃዋሚዎች ጋር ተወያዩ፡፡ ከስፔን፣ ፖርቱጋል፣ ማልታ፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ የተወከሉ ልኡካን በኢትዮጵያ ስላላው አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ ከተቃዋሚዎች በኩል ከመድረክ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ከአንድነት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና አቶ አስራት ጣሴ፣ ከመኢአድ አቶ አበባው መሀሪ፣ ከሰማያዊ ፓርቲ አቶ ይልቃል ጌትነት እንዲሁም ከኢዴፓ አቶ ልደቱ አያሌውና የፓርቲው ፀሀፊ ተገኝተዋል፡፡ ከተወካዮቹ በኩል የተነሱት ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው፡- 1. የፓርቲዎች ቁጥርስ ለምን በዛ? 2. በህግ አግባብ የተመዘገቡ ስንት ናቸው? 3. በፕሮግራምና በርዕዮተ ዓለም ልዩነታቸውና

Thursday, November 28, 2013

በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች በወገኖቻችን ስም በእጅ አዙር ገንዘብ ማሰባሰብ መጀመራቸው እየተነገረ ነው ።

በሪያድ መለዝ አካባቢ የሚገኝ፡አሚራ ኑራ ዩንቨርስቲ ግቢ ሜዳ ላይ ያለዳስ ብርድ እና ጸሃይ የሚፈራረቅባቸው ከ 7 ሺሕ የሚበልጡ ወገኖቻችን በመግብ ወሃ እና የመጸዳጃ ቦታ እጦት እየተሰቃዩ ነው ። የተጠቀሰው መጠለያ ውስጥ ያሉት ወገኖቻችን አብዛኛዎቹ ሴቶች ህጻናት እና አረጋውያን እንደሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ።

‹‹ሰው ለሰው›› የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትእዛዝ ስክሪፕቱን እንዲቀይር ተገደደ፡፡

ኢሳት ዜና :-በኢትዩጵያ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ በረዥምነቱ ቀዳሚውን ቦታ በመያዝ የሚታውቀው ሰው ለ ሰው ተከታታይ ድራማ 109 ክፍሎች ያህል ከተላለፈ በኃላ፣ ሰዎች በማህበራዊ ድህረ ገጾች የድራማው ተዋንያን የሆነውን በትወና ስሙ አስናቀ የተባለውን  ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር  በማመሳስል ገጸባህሪውና ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለስልጣናትን በገንዘብ ይገዛሉ ፤ ፍትህን ይረግጣሉ ፤ በሰው ህይዎት ይነግዳሉ፡ ፤ ሰው ያስገድላሉ፤ ህዝብን ያስለቅሳሉ ፤ በወንጀል ይነግዳሉ፤ ሰው በላ እና ነፍሰ ገዳይ አምባገነን ናቸው ሲሉ እንደሚተቹዋቸው ይታወቃል፡፡

Wednesday, November 27, 2013

በዜጎች ህይወት የተደራደረው አገዛዝ ማለፉ አይቀርም

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር)
ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡

በኢህአዴግ አባላት ስም ፓርላማውን በመቆጣጠር ኢህአዴግን ሊጎዱት ይችላል ሲሉ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ተናገሩ

የግንቦት7 እና አክራሪ የእስልምና ሀይሎች 

ኢሳት ዜና :-ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ይህን የተናገሩት ” በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመንግስት ቀጣዩ የምርጫ ፈተና” በሚል ርእስ ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ባቀረቡት ጽሁፍ ነው።ኢሳት የሚኒስትሩን  ሙሉ ንግግር የያዘ ሰነድ የደረሰው ሲሆን፣ በሰነዱ ግርጌ ላይ ” ለመደበኛ አባላት የማይነገር፣ ለከፍተኛ አመራሮች ብቻ” የሚል ተጽፎበት ይታያል።  በዚህ ርእስ ስር ደግሞ ” ቀጣዩ የምክር ቤት አባላት ምርጫ የግንቦት ሰባት እና አክራሪ እስልምና ሀይሎችን የሚያስቀጥሉ አባላት ወንበሩ በኢህአዴግ አባላት ስም ሊነጠቅ ይችላል። ” ብሎአል። ሚኒስትሩ ለዚህ አስተሳሰባቸው የምርጫ 97ትን ሁኔታ እንደማጠቃሻ ተጠቅመዋል። ” የ97 የቅንጅት አሸናፊት አካሄድ ስልት ማለትም የተቃዋሚ አባላት ሁነው በህቡእ ተደራጅተው በኢህአዴግ የአባላትን ካርድ ሙሉ በሙሉ ፓርቲውን ሊጎዱት ይችላሉ” ሲሉ ሚኒስትሩ ጽፈዋል።

[አሳዛኝ ዜና]በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት ውስጥ ዳናይት ኪዳነ የተባለች ልጁን በጩቤ ወግቶ ከገደለ በኃላ እራሱን በእሳት ለኩሶ ሲያቃጥል ፖሊስ ደርሶ ወደ ሆስፒታል ወሰደው

[አሳዛኝ ዜና] በአሜሪካ ቴክሳስ ክፍለ ግዛት ውስጥ አቶ ሙሉጌታ ተረፈ የተባለ አባት ዳናይት ኪዳነ የተባለች ልጁን ቤቱ ውስጥ በጩቤ ወግቶ ከገደለ በኃላ ከአካባቢ በመሰወር መኪና ውስጥ እራሱን በእሳት ለኩሶ 98% ሰውነቱን ካቃጠለ በኃላ ፖሊስ ደርሶ ወደ ሆስፒታል ወስዶታል:: ዝርዝሩን ከዚህ ቭዲዮ ያግኙ::

CORPUS CHRISTI 

Tuesday, November 26, 2013

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ሰራዊት በጋራ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀሙ

የጋራ ትግል አስፈላጊ መሆኑን በፅኑ የሚያምኑት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢሕአግ/

Ethiopian freedom fighters
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ /ጋሕነን/ በሕዳር 13/2006 ዓ.ም በሁመራ ሉግዲ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ለሶስት ሰዓት ያህል በወሰደው ውጊያ የወያኔው 24ኛ ክፍለ ጦር ድባቅ ተመቷል።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በ24ኛው ክፈለ/ ጦር ላይ በተመሳሳይ ሥፍራ  ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱ ይታወሳል።

ሰሞኑንን ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ 12 ነፍሰጡሮችን ጨምሮ ወደ 200 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ጉዳያቸው ባሉበት አልቆ ለሃገራቸው መብቃት እየቻሉ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ መጠለያ መወሰዳቸው እያነጋገረ ነው ።

* ትላንት ማምሻውን በ 17 አውቶብስ ከሪያድ ድንበር ግዜያዊ መጠለያ ተጭነው አሚራ ኑራ እይተባለ የሚጠራ ዩንቨርስቲ ግቢ ባዶ ሜዳ ላይ አንተኛም ኤርፖርት ውሰዱን ብለው ከተሳፈሩበት አውቶብስ አንወርድም ብለው ያመጹ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ዛሬ ረፋዱ ላይ ሪያድ ሺሜሲ አካባቢ ወደ ሚገኝ አስርቤት ተወስደው የጣት አሻራ ሰጥተው መጨረሳቸውን እና ሊሴ ፓሴ መቀበላቸውን ማረጋጋጥ ተችሏል።

ጠጉረ ልውጦች ከአራት ኪሎ እንጅ ከሶማሊያ ወይንም ከኢራቅ ይመጡ ይሆን?

ጠጉረ ልውጡ ‹‹መንግስት››

………
ሰሞኑን በኢቲቪና በሬዲዮ፣ እንዲሁም ህዝቡን እየሰበሰቡ ‹‹ጠጉረ ልውጥ ሰው ካያችሁ ጠቁሙን!›› ሲሉ ሰንብተዋል፡፡
ጠጉረ ልውጥ ማለት አገሪቱን አሊያም ህዝቡን የማያውቅ ማለት አይደለም፡፡ እሱማ ፈልጎም ሆነ አፈላልጎ ወደዛው ደርሷል፡፡ ጠጉረ ልውጥ የሚገኝባት አገርም ሆነ ህዝብ በውል የማያውቁት በዕድ ማለት ነው፡

Monday, November 25, 2013

“አንዱዓለም አራጌ በትግራይ ሕዝብ የሚወደድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ነው” አብርሃ ደስታ

ከመቀሌ ኢትዮጵያ በየጊዜው በፌስቡክ እና በተለያዩ ድረገጾች ወቅታዊ መረጃዎችን በማድረስ የሚታወቀው አብርሃ ደስታ አንዷአለም አራጌ በትግራይ ሕዝብ የሚወደድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ነው አለ።

የ ታላቁ ሩጫ ተሳታፊዎች ተቃዉሟቸዉን አሰሙ!!!

ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባል ወገኖች ዛሬ በተካሄደዉ የ ታላቁ ሩጫ ላይ በሳዑዲ ስለሚሞቱና ስለሚንገላቱ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸዉን ሲያሰሙና በመንግስትም ላይ ወቀሳቸዉን በመፈክር እዲዲሁም በዜማ አሰምተዋል፡፡ መንግሰት በዚህ ሩጫ ላይ ህብረተሰቡ የሰማያዊ ፓርቲን ጥሪ እዳይቀበል በአዘጋጀቹ በኩል ቢያሳስብም(ጥቁር ሪቫን እንዳይደረግ) የሀገር ፍቅር ያቃጠላቸዉና የወገኖቻቸዉ ጥቃት ያተሰማቸዉተሳታፊዎች ከፍተኛ የፖሊስና የደህንነት ቁጥጥር ከቁብ ሳይቆጥሩ “በሳዑዲ ነገር እንነጋገር የሳዑዲን ነገር ” ሲሉ አርፍደዋል፡፡ ገና ከመግቢያዉ ጀምሮ ከፍተኛ ፍተሻ ሲደረግ የነበረ ቢሆንም አብዛኞቹ ተሳታፊዎች ሪቫኑን ትተዉ በጥቁር ኮፍያና ሱሪዎች ሩጫዉን መካፈል ችለዋል(በተቃዉሞዉ የተሳተፉቱ)፡፡

Sunday, November 24, 2013

ለዜጎቹ የማይቆረቆርና ጥብቅና የማይቆም መንግስት (ከአስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚኬኤል)

saudi and ethiopians

በዚሁ ባለንበት ዘመን ያለፉት ስርአቶች ወደኃላ ተመልሰን ስናስታውስና አሁን ያለውን የህ.ወ.ሓ.ት መንግስት ስንመለከት ኢትዮጵያውያንን  ለስድት የሚዳርጓቸዉ ችግሮች ነበሩ።

“እኔ ራሴ ስድስት ያበዱ ሴቶችን ይዤ መጥቻለሁ..” ራውዳ ጀማል – ከሳዑዲ ተመላሽ ኢትዮጵያዊት (ቃለ ምልልስ)

በሃገር ቤት እየታተመ የሚወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ ኢትዮጵያውያን ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። ቃለ ምልልሱ ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም ትዘግባቸው የነበሩ የሳዑዲ ሕይወቶችን የሚያጠናክሩ በመሆናቸው ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው ያደረገችውን ቃለምልልስ ለአንባቢዎቻችን እንደወረደ ይኸው፦

Saturday, November 23, 2013

ከሳኡዲ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

ሰሞኑን በህገወጥ መንገድ ሳኡዲ አረቢያ ከገቡ ብዙ ሺ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች መካከል ዓለም አቀፍ የስደተኞ ተቋም ከ350 በላይ የሚሆኑትን ወደ አገራቸው መልሷቸዋል፡፡ ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው በተቋሙ መጠለያ ጣቢያ ያገኘቻቸውን ሦስት ተመላሾች አነጋግራለች፡፡
“ሳኡዲ ወርቅ እየዘነበ ነው ቢሉኝ አልሰማም” አብዱ እንድሪስ
“ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት እየተሰቃዩ ናቸው” እንድሪስ መሃመድ
“አበሻ ለእነሱ ርካሽ እቃ ማለት ነው” እንድሪስ የሱፍ

በሳውዲ ለሚገኙ ወገኖቻችን በአፋጣኝ እንድረስ፤ በወያኔ ላይ በጋራ እንነሳ!!!

በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው መጠን የለሽ የመብት ጥሰት ለመቃወም በተለያዩ የዓለም አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በየአገራቱ የሚገኙ የሳውዲን ኢምባሲዎችን በተቃውሞ እያጨናነቁ ነው። በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ዘግኛኝ በደል የተሰማቸውን ጥልቅ የመጠቃት ስሜት ኢትዮጵያን በተቃውሞ ሰልፎቹ ላይ በሚያሰሟቸው መሪር የሐዘን እንጉሮችና የቁጭት ንግግሮች እየገለፁ ነው። ከሐዘንና ቁጭት ባለፈም ለበደል ለተጋለጡ ወገኖቻችን አስቸኳይ ሰብዓዊ ርዳታ ለማድረስ እና የዲፕሎማሲ ድጋፍን ለማሰባሰብ ዓለም ዓቀፍ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ሥራውን ጀምሯል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ይህንን ዓለም ዓቀፍ ጥረት ለመደገፍ በውጭ አገራት የሚገኙ አባላቱ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ መመሪያ አስተላልፏል።

[የሳዑዲ ጉዳይ]፦ የዮሴፍን ውለታ የማያውቅ ሌላ ፈርኦን ተነሳ

 ከመልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ገብረሚካኤል

(በሚኒሶታ የቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክ አስተዳዳሪ)
aba
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። አሜን።
ቅዱሱ መጽሐፍ የሃይማኖት ብቻ መጽሐፍ ሳይሆን የታሪክም ምስክር ነው። ዮሴፍ በተሰደደበት በምድረ ግብጽ ኑሮውን ብቻ እያሸነፈ የኖረ አልነበረም። የግብጽ አስተዳደር በመልካምና ፍትሃዊ በሆነ የገንዘብ አከፋፈልና በንብረት አጠባበቅ ያገለገለ ለግብጽ ህዝብና መንግስት ባለውለታ ነበር። ህዝበ እስራኤል በችግር ምክንያት ተሰደው በመልካም ጸባይ ኑሯቸውን እያሸነፉ ምድረ ግብጽን እያለሙ፤ እግዚአብሔርን እያመለኩ፤ ሀገራቸውንም እያሰቡ፤ የሚመለሱበትንም ቀን በተስፋ እየጠበቁ ይኖሩ ነበር። በሁዋላ ግን የዮሴፍን ውለታ የማያውቅ ሌላ ፈርኦን ተነሳ። በህዝበ እስራኤል ላይ ግፍና መከራ ፤ ሰቆቃና ሞት አጸናባቸው። እግዚአብርሔርም ካህኑን አሮንንና መስፍኑን ሙሴን አስነሳ፤ ህዝቡንም ይዘው ወጡ ይላይ ቅዱሱ መጽሐፍ። ቅድስቲቷ ሀገር ኢትዮጵያ ለዜጎቿና ለሌላው ዓለም ባለውለታ ናት።

ሰበር ዜና፡- በአሜሪካ፣ ሜሪላንድ ክፍለ ግዛት፣ በዛሬው እለት ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ቢኒያም አሰፋ እና ባለቤቱ፣ የ3 ወር ህፃን ልጃቸውም በጥይት መሞታቸው ተዘገበ፤

ሰበር ዜና፡- በአሜሪካ፣ ሜሪላንድ ክፍለ ግዛት፣ በዛሬው እለት ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ቢኒያም አሰፋ እና ባለቤቱ፣ የ3 ወር ህፃን ልጃቸውም በጥይት መሞታቸው ተዘገበ፤ ባልና ሚስቱ ራሳቸውን ያጥፉ ወይም ይገዳደሉ አልታወቀም። ይሄ ሁሉ ሲካሄድ የ5 አመት ልጃቸው ወደ ጎረቤት አምልጣ ተርፋለች። ሙሉ ዜናው እነሆ!


NEW MARKET, Md. (WUSA9) — The Frederick County Sheriff’s Office have identified the three people, including an infant, who died after a shooting Wednesday night.

Friday, November 22, 2013

ኦባንግ – ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር እየሠራሁ ነው አሉ. የሳዑዲ ልዑል አንጋቾቻቸውን አወደሱ

 

በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ፈር የለቀቀ አስነዋሪ ግፍ ዓለምአቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡ የሳዑዲ ልዑል ሰብዓዊነት የረገፈበትንና በግፍ የተሞላ የወሮበላ ተግባር የሚፈጸምበትን አሰቃቂ ተግባር የሚከናውኑትን አንጋቾች አሞካሹ፡፡
ያለ አንዳች ልዩነት ኢትዮጵያውያን በኅብረት ድምጻቸውን በማሰማት እየተቃወሙት ያለውን ኢሰብዓዊ ተግባር አስመልክቶ በተለያዩ መንገዶች ይፋ ከሆኑት በተጨማሪ ድብቅ መረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ የጋራ ንቅናቄው ከዓለምአቀፍ የመብት ተቋማት ጋር በቅርበት እየተሰራ ስላለው ዝርዝር ጉዳይ ግን ከሁኔታው ምስጢራዊነት አኳያ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

የህወሓት እኩይ ተግባር እያደረ ይገለጣል!! (ኢንጂኔር አብደልውሀብ ቡሽራ – መቀሌ)

 ከሁለት ሳምንታት በፊት ወደ ሽሬ ለመሄድ ወደ መቀሌ አውቶብስ ተራ ሄድኩና በሰላም ባስ አውቶብስ ተሳፍሬ ጉዞየን ጀመርኩ:: እየተጓዝን እያለን በተቀመጥኩበት ወንበር አጠገብ ሁለት ሰዎች ነበሩ:: ሰዎቹ ከዛ በፊት አይቻቸው አላውቅም:: ሁለቱም አካል ጉዳተኞች ናቸው:: በመንገዳችን እየተጓዝን እያለን ሁለቱ ሰዎች የድሮ ትዝታቸው እያነሱ እያወሩ ነበሩና እኔም የነሱ ወሬ አዳምጥ ነበርኩ:: እንደዛ ቆየሁና ወሬያቸው

Thursday, November 21, 2013

በመልሶ ማልማት ፕሮግራም 16 ሔክታር ላይ ያረፈው «አሜሪካ ግቢ» ሊፈርስ ነው

በመልሶ ማልማት ፕሮግራም 16 ሔክታር ላይ ያረፈው «አሜሪካ ግቢ» ሊፈርስ ነው

•በዚህ ዓመት 200 ሔክታር መሬት ላይ ያረፉ ቤቶች ለመልሶ ልማት ይፈርሳሉ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመልሶ ማልማት ፕሮግራሙ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከታላቁ አንዋር መስጊድ ፊት ለፊት በሚገኘውና «አሜሪካ ግቢ» ተብሎ በሚጠራው መንደር የሚገኙ መኖሪያ ቤቶችንና ንግድ ቤቶችን ሊያፈርስ ነው፡፡

የስዊድን የጦር ፍርድ-ቤት አቃቢ-ህግ በኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ወሰነ፡፡

ኢሳት ዜና :-የጦር ፍርድ ቤቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በቅርቡ በኦጋዴን የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በተመለከተ፣ የክልሉ የወጣቶች ሊቀመንበርና የፕሬዚዳንቱ የግል ዌብሳት ማኔጀር እና አማካሪ የነበረው ወጣት አብዱላሂ ሁሴን በኦጋዴን የጦር ወንጀልና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸሙን የሚያሳይ ማስረጃ ለፍርድ ቤቱ አቃቢ ህግ ማቅረቡን ተከትሎ ነው።

Monday, November 18, 2013

የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ስደተኛ እንጂ ህገወጥ/ወንጀለኛ ዜጋ የለንም::




Image


ምንሊክ ሳልሳዊ :- ይህ በአለም ላይ የማይካድ እውነት ነው:: ምንም ከሃገሩ ካለምክንያት አይሰደድም የአንድን ሃገር ድንበርም ጥሶ ካለምክንያት አይዘልቅም:: ኢትዮጵያውያን በተለያዩ መንገዶች ወደ አረብ አገራት ገብተዋል:: የይልፍ ወረቀት ገዝተው በአየር የወጡትን ጉዳይ ለጊዜው ተወት እናድርገው እና በዛሬው ወቅት ህገወጥ እየተባሉ በአረቦቹ እና በስርኣቱ መሪዎች ስለሚወነጀሉት ኢትዮጵያውያን አጠር ያለ ነገር እናንብብ::

በገዛ ሀገራችን መንግስታዊ ሽፍቶችም ሆነ በተሰደዱበት ሀገር ሰዎች መደፈሩ ፣ መዋረዱ መቼ ይሆን የሚቆመው ?

“… በየምሽቱ ሁላችንንም ወደ ምርመራ ክፍል ይወስዱናል ፡፡ ከዚያም እያንዳችንን ለያይተው ይገርፉናል ፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ስጠራ ሶስት ወንዶች በክፍል ውስጥ ይጠብቁኝ ነበር ፡፡ ወዲያዉኑ ሶስቱም በየተራ እየተፈራረቁ ደፈሩኝ ፡፡ ወደነበርንበት ጉድጓድ ስመለስ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃየሁ ነበር ፡፡ አሁን ድረስ ህክምና ማግኘት አልቻልኩም ፡፡

Sunday, November 17, 2013

ይድረስ ለኢትዮጵያ ፖሊሶችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት

ዋና ጠላታችን የትግሬ ነፃ አውጪ ወያኔ ነው!

በየቦታው ተበትናችሁ ለአገር የሚበጅ ስራ እየሰራን ነው ለምትሉ የፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሙሉ። እንዴት ከርማችሁልኛል? እንደ አገር ልጅ ብናፍቃችሁም እንኳ የናንተ እንጀራና የኔ ኑሮ አልገጥም ብሎ ካጠገባችሁ ከራቅሁ አመታት አልፈዋል። ብዙ ሰዎች የሰው ልብ ያላችሁ፣ አዛኝ አንጀት ያላችሁ መሆናችሁን ይጠራጠሩ ይሆናል። እኔ ግን እንደሱ አላስብም ብዙዎቻችሁ ድህነት በግዱ ገፍትሮ እዚህ ውስጥ እንደ ጨመራችሁ አውቃለሁ። ምክንያቱም ብዙ ጓደኞቼ የሚላስ የሚቀመስ ሲያጡ፣ እንደኔ ለመሰደድ መድፈር ሲያቅታችውና ቢፈልጉም እንኳን ሱዳንና ኬንያ የምታደርስ ገንዘብ በማጣታቸው እንጀራ ብለው የገቡ ብዙ እንዳሉ አውቃለሁ። እነዚህ በሙሉ የድሀ ልጆች ቤት ተቀምጦ በረሀብ ከመሞት የምችለውን አድርጌ እኖራለሁ ብለው እንደሚኖሩ አውቃለሁና በተለይ እናንተ ከዚህ የመከራ ማጥ እንድትወጡልኝ አምላኬን መለመን አልተውኩም። ግምገማ ፈርታችሁ የራሳችሁን ወገን በዱላ መጨፍጨፍ እንዴት እንደሚሰማ አውቀዋለሁ። ባዶ እጁን ያለን ሰውማ በጥይት መግደል የባሰ ነው። በተለይ ያልበላን ሆድ ተርቦ የሚያውቅ ሆድ እንዲህ ያለውን ግፍ በደንብ ያውቃል። ዞሮ ዞር የሚመታውም ሆነ የሚገደለው የናንተ ዘመድ እንኳን ባይሆን አንዱ ቦታ ተመድቦ የሚሰራ የባልደረባችሁ ዘመድ መሆኑ መች ይቀራል።

Friday, November 15, 2013

አዲስ አበባ ላይ በሳዑድ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ ሊካሄድ የነበረ የተቃዉሞ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ። አሶሲየትድ ፕረስ እንደዘገበዉ ፖሊስ በመቶዎች የሚቆጠሩን ሰልፈኞች ለመበታተን ኃይል ተጠቅሟል።

NOV 15,2013

0,,17229922_303,000,,17229927_404,000,,17229898_404,00
የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት እርማጃና ተቃዉሞዉ
አዲስ አበባ ላይ በሳዑድ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ ሊካሄድ የነበረ የተቃዉሞ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ። አሶሲየትድ ፕረስ እንደዘገበዉ ፖሊስ በመቶዎች የሚቆጠሩን ሰልፈኞች ለመበታተን ኃይል ተጠቅሟል።

ህወሃት ፈቀደ እኛም ተዋረድን ,መንግሥት አልባ አገር!

የብዙ ሺህ ዘመናት የመንግሥትነት ታሪክ የነበራት አገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ መንግሥት አልባ አገር ናት ብሎ ደፍሮ መናገር የሚቻልበት ወቅት ላይ ደርሰናል።
ኢትዮጵያ የፀረ ቅኝ አገዛዝ ትግል ፋና ወጊና የበርካታ ጥቁር ሕዝብ የነፃነት ትግል ማነቃቂያ ምሳሌ ሆና ቆይታለች፤ ህዝቧም ክብር ያለው ነበር። አሁን ባለንበት ዘመን ግን  ኢትዮጵያዊነት የሚያሳፍር የኢትዮጵያውያንም ዋጋ ከእንስሳት ይልቅ የወረደበት ወቅት ላይ እንገኛለን።

መቋጫ ያጠው የወገኖቻችን ስቃይ እና ሞት በሳውዲ አረቢያ ፡አሁንም ቀጥሏል !

ትላንት አመሻሹ ላይ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፍሃ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገርሽቶ በዋለው ተቃውሞ የተጓዳ የሞተ ባይኖርም ኢትዮጵያውያኑ ድምጻቸውን ከፍ አድረገው አንድነን አንድነን … መብታችን ይከበር ….እኛም ሃገር አለን ወዘተ… በሚል መፈክር ታጅበው ብሷታቸውን ሲያሰሙ መዋላቸውን የሚገልጹ የአይን እማኞች የሳውዲ የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞውን ለመብተን በከፈቱት ቶክስ ይሰማ በነብረው የጥይት ድምጽ አካባቢውን ወደ ጦርነት አውድማ ለውጦት ማምሸቱን የገልጻሉ። 
ይህንንም ተከትሎ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ተጨማሪ ልዩ ፈጥኖ ደራሽ፡ ኮማንዶዎች ቦታው በመድረስ ተቃውሞውን መግታት ተችሎል ብለዋል ። እንዚህ ምንጮች ትላንት ተቀስቅሷ በነበረው ሁከት ጥቂት ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መደሱን ገልጸዋል። ሰምኑን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በውጭ፡ሃገር ነዋሪዎች ላይ ያወጣው ህግ የግዜ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች በኢትዮጵያውያኑ ላይ እየወስዱ ባሉት የተናጥል እርምጃ አያሌ ወገኖቻችን ወደ ሃገሩ ለመምለስ ከየመኖሪያ ቤቱ ነቅሎ አደባባይ ቢወጣም ወደ ሃገር መግባት የሚያስችሉት ነግሮች በመንግስ በኩል ባለመኖሩ ከእልቂት ተርፈው ወደ እስርቤት የተጓጓዙ ከ 20 ሺህ የሚበልጡ ወገኖቻችን በምግብ ወሃ እና የመጸዳጃ ቦታ እጦት እይተሰቃዩ እንደሚገኙ ተግልጾል።

Thursday, November 14, 2013

ዳግማዊ ሆሎኮስት በኢትዮጵያውያን ላይ? ከዲያቆን ዓባይነህ ካሤ

ኢትዮጵያውያን ደማቸው የዐረብን አስፋልት አቀለመው፡፡ ባንዲራውን በራሱ ላይ ሸብ ያደረገው የእማማዬ ልጅ የእኔ ጀግና ማንነቱን እየተናገረ በአናቱ ላይ የወረደውን የድንጋዩን ናዳ በሀገሩ ፍቅር ተቋቁሞ በክብር አሸለበ፡፡ ለእርሱ ከዚህ በላይ ሌላ ድል አልነበረምና፡፡ ድንጋዩስ እርሱን አሳርፎታል፡፡ ነፍሱን ይማርልን እንጂ! ባንዲራችን ግን እንደተመታች እንደታመመች ናት፡፡ እውን ይኽ የሆነው በእኛ ላይ ነው?

 
ይህቺ ባንዲራ እኮ ጨርቅ አይደለችም፡፡ ያ በሳኡዲ መሬት ተወግሮ የሞተው ወንድሜ የኮራባት በሞቱ ጊዜ የለበሳት የክብሩ፣ የማንነቱ መገለጫ እንጂ፡፡ ማንም ባይደርስለት ባንዲራው ነበረችለት፡፡ በእርሷ ተጽናና፡፡ ሞተ አልለውም መሰከረ እንጂ፡፡ ባንዲራ ለብሶ መከራን መጋፈጥ የሰማእታት ወግ ነው፡፡

Wednesday, November 13, 2013

ብሄራዊ ውርደት፤ የምንመጻደቅበት ‘ሌጋሲ’


The suffering of Ethiopians in Saudi Arabia
ክንፉ አሰፋ 
ወገናችንን በጥይት ሲደፉት በራሱ ላይ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንድራችንን ጠምጥመውበታል[1]። ጭካኔ በተሞለበት መንገድ የተገደለው ይህ ኢትዮጵያዊ አስከሬኑም በሰላም አላረፈም። በአካሉ ላይ ያረፈውን ጨርቅ በሴንጢ እየቆራረጡ በሰብአዊ ፍጡር ላይ ሊደረግ የማይገባውን ሁሉ አደረጉበት። ድርጊቱ ናዚዎች በኦሽዌትስ ይፈጽሙት የነበረውን አሰቃቂ ግፍ ያስታውሰናል። በ21ኛው ዘመን እንዲህ አይነቱ ክስተት ይደገማል ብሎ የሚያስብ የለም። እነሆ ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመችው ነው። በስውር ሳይሆን በግልጽ። እንደ ኦሽዊትስ በታጠረ የማጎርያ ካምፕ ሳይሆን በአደባባይ።

Tuesday, November 12, 2013

የኢሕአዴግ መንግሥት አሳምሮ ይፈራል! በኃይሉ አርአያ (ዶ/ር)

የኢሕአዴግ መንግሥት አሳምሮ ይፈራል! በኃይሉ አርአያ (ዶ/ር) ሰሞኑን የኢሕአዴግ መንግሥት ይፈራል አይፈራም የሚል ጉዳይ ከፓርላማ ተነስቶ ወደ መገናኛ ብዙኃንም ደርሷል። ጉዳዩ የተነሳው የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ አዲሱ ፕሬዚዳንታችን በፓርላማ ያደረጉትን ንግግር አስመልክቶ ባቀረቧቸው የማማሻሻያ ሐሳቦችና ጠቅላይ ሚኒስትራችን በሰጡት ምላሽ ዙሪያ ነው። ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዝ ሪፖርተር ጋዜጣ ጥቅምት 13 ቀን 2006 ዓም በአወጣው ዕትሙ ‹‹’ፈሪ’ መንግሥት?›› በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ የማነ ናግሽ ጥሩ ትንተና አቅርቧል። የፍርኃት ነገር ከተነሳ ጋዜጠኛው

መከራው ቀጥሏል- ኩዌት ደግሞ ሌላ የኛን ትኩረት የሚሻ ነገር ዛሬ ተፈጽሟል።

መከራው ቀጥሏል – የኛም ጩኸት እንዲሁ ይቀጥላል! ኩዌት ደግሞ ሌላ የኛን ትኩረት የሚሻ ነገር ዛሬ ተፈጽሟል። በኩዌት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መካከል 1ሺ የሚሆኑት የሚሰሩት በአንድ የጽዳት ኩባንያ ውስጥ ነው። ነገር ግን በምን ምክንያት እንደሆነ ባልተገለጸ ሁኔታ ይኸው የጽዳት ኩባንያ 1ሺዎቹንም ኢትዮጵያውያን ከትናንት እሁድ ጀምሮ ከሥራ አባሯል። ኩዌት ታይምስ ዛሬ ህዳር 2 (ኖቬምበር 11) እንደጻፈውና

ወያኔ ማለት ቁምጣ ለብሶ የመጣ ደርግ ነው ፡፡

ጥቁር ሽብር ወያኔ ቁምጣ የለበሰ ደርግ ነው ! እመኑኝ በየትኛውም የታሪክ ገጠመኝ የሳወዲ መንግስት የዚህ አይነት ድፍረት ያውም በአደባባይ በዜጎቻችን ላይ አሳይቶ አያውቅም ፡፡ ነገሮችን ተመልሰን ከተመለከትን ይህ ግፍና በደል የእኛው ባለስልጣናት ሳውዲወችን አደፋፍረው ያስፈፀሙት ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ሁለት ፖለቲካዊ ምክንያቶች አሉት ፡፡ የመጀመሪያው ፡- የወያኔ ባለስልጣናት በሳውዲ የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያንን ቦንድ እንዲገዙ በሰበሰቡበት ወቅት ተደጋጋሚ ተቃውሞ ደርሶባቸው እንደነበር የሚታወቅ ነው ፡፡ ይህም ድምፃችን ይሰማ ባሉ ሙስሊሞች ላይ በሃገር ውስጥ የሚደርሰው በደል ይቁም ለጥያቂያቸውም አጥጋቢ

Monday, November 11, 2013

ሰበር ዜና አርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ በተማሪዎች በተነሳ ተቃውሞ ግቢው በከፍተኛ ውጥረት ላይ ይገኛል፡፡

ሰበር ዜና 

አርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ እየተማሰ ነው፡፡ በውሃ እጥረት ችግር በተማሪዎች በተነሳ ተቃውሞ ግቢው በከፍተኛ ውጥረት ላይ ይገኛል፡፡ የፌድራልና የአጋዚ ወታደሮች ግቢው ውስጥ ገብተዋል፡፡ ተማሪዎችን እየደበደቡ ነው፡፡ ወደ ላይ እየተኮሱ ነው፡፡ በርካታ ተማሪዎች እየተደበደቡ ወደ መኪና እየተጫኑ ነው፡፡ውጥረቱ አይልዋል፡፡ ፖሊሶች ወደ ላይ እየተኮሱ ነው፡፡ ግቢው ውስጥም የተነሳ እሳት መኖሩን ቦታው ድረስ በመደወል ያነጋገርናቸው ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ ዝርዝሩን በዛሬው ፕሮግራም ይጠብቁን

Sunday, November 10, 2013

ለዜጎች ስደት እንዲሁም በስደት ለሚደርስባቸው ሰቆቃ ተጠያቂ ሥርዓቱን የሚመራው መንግሥት ነው!!



ቀደም ባሉት ዘመናት ወደ ውጭ ሀገር በተለያየ ምክንያት የተጓዙ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትን፤ የእናት ሀገራቸውን ምድር የሚረግጡበትን ቀናት ይቆጥሩና ይናፍቁ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን በዋናነት ወደ ውጪ ሀገር የሚሄዱት ለትምህርት ሲሆን የዚያን ዘመን ወጣት ትምህርቱን ጨርሶ በመመለስ የሀገሩን እና የሕዝቡን ውለታ ለመክፈል የነበረው ጉጉት ከፍተኛ ነበር፡፡ ተምሮ በውጪ ሀገር መቅረት ሀገርን እንደመክዳት የሚያስቆጥር በመሆኑ በኢትዮጵያውያን ህሊና ስደት ተቀባይነት አልነበረውም፡፡
ዛሬ ዛሬ ሁኔታዎች ሁሉ ተለዋውጠው የኢትዮጵያ ህዝብ እጣ ፋንታ ፍልሰትና ስደት ሆኗል፡፡ ስደት የማያባራ የኢትዮጵያውን የሕይወት ገጽታ ሆኗል፡፡ የገጠሩም የከተማውም ሰው ወደ ውጭ ሀገር ይሰደዳል፡፡ ወጣቶች ይሰደዳሉ፡፡ እህቶቻችን ይሰደዳሉ፡፡ ሕፃናት ጭምር በጉዲፈቻ ስም ይሰደዳሉ፡፡ ‹ሕጋዊ› በተባለውም ሆነ በሕገ-ወጥ መንግድ ሕዝባችን ወደ ውጭ ሀገር ይነጉዳል፡፡ በዚህ የተነሳም በወሊድ ምጣኔ ሳይሆን በሰደት ምክንያት አምራች የሆነው የህዝብ ቁጥር ሊቀንስባቸው ከሚችሉ ሀገሮች ኢትዮጵያ አንዷ ሆናለች፡፡

ቴዎድሮስ አድሃኖም ህገወጥ ኢትዮጵያውያን እንዲያዙ የተስማማበት ሰነድ አለን"የሳኡዲ ባለስልጣናት,


በሪያድ የዛረው ሰልፍየሚመጣውን አደጋ በመፍራትተበትኗል::
999410_10201428110199302_1866404023_n“ቴዎድሮስ አድሃኖም ህገወጥኢትዮጵያውያን እንዲያዙየተስማማበት ሰነድአለን”የሳኡዲ ባለስልጣናት
አምስተኛ ቀኑን የያዘው የሳኡዲጸረ ኢትዮጵያውያን ዘመቻእንደቀጠለ ሲሆን ሁኔታዎችንለመፍታት የተደረጉ ጥረቶችከዚህ
ቀደም የኢትዮጵያመንግስት እና የቆንስላውዲፕሎማቶች በሰርኡት ስህተትመስመር ሊይዝ አልፈለገም::
እንደ ሳኡዲ ባለስልጣናትአነጋገው የውጪ ጉዳይሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ባደረጉት ጉብኝት ሃገራቸው ህገወጥ ኢትዮጵያውያንን እንዲያስወጣ እና በምትኩ40,000 ህጋዊ ስደተኞችን እንደሚልኩ የፈረሙበትን ማስረጃ ይዘዋል::

Saturday, November 9, 2013

ኢትዮጵያውያኑ በሳዑዲ አረቢያ የሚፈጸምባቸውን ግፊት ተቃውመው አደባባይ ወጡ


ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ እንደዘገበው፦ 


ዛሬ ረፋድ ላይ…
በሳውዲ ዋና ከተማ ዛሬ ከረፋዱ ጀምረው እስከ እኩለቀን በሪያድ መንፉሃ ወደ ሃገራችን ስደዱን በሚል መንፉሃ ባንክ አልራጅህ አካባቢ በርካታ ኢትዮጵያውያን መንግስት የወሰደውን እርምጃ ተቃውመው ወጡ። ቤተሰቦቻቸውን እና ሻንጣቸውን ይዘው አውራ መንገድ የወጡት ኢትዮጵያውያን ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ግማሾቹ ወደ ሪያድ ኢምባሲና ኮሚኒቱ መስሪያ ቤት በእግራቸው ያመሩ ሲሆን መንፉሃ አካባቢ የቀሩት ከፖሊስ ጋር ባደረጉት ግጭት አንድ የፖሊስ መኪና እንደተሰበረ የአይን እማኞች ገልጸውልኛል። ይህንን ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን አደጋ በመፍራት አብዛኛው ተቃውሞ አቅራቢ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት መበተናችው ታውቋል።

ሕወሓት አለማቀፍ አሸባሪ መዝገብ ላይ በአሸባሪነት የሚታወቅበት ፕሮፋይል::


ምንጭ :- START – UNIVERSITY OF MARYLAND – የአሸባሪዎች አጥኚ ቡድን
የአሸባሪ ድርጅቶች መዝገብ
በሃገሩ ቋንቛ መጠሪያው .. አልተገለጸም
የድርጅቱ ስም …..የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (TPLF)
የሚንቀሳቀስበት አከባቢ … ኢትዮጵያ
የተቋቋመበት ጊዜ ….. አልተገለጸም
የአባላቶቹ ቁጥር/ጥንካሬው … አይታወቅም
መለያው ….. ኮሚኒስት/ሶሻሊስት/ብሄርተኛ/ተገንጣይ
የገንዘብ ምንጩ …. አይታወቅም
የተነሳበት የፖለቲካ ፍልስፍና
ራሱን የትግራይ ንቅናቄ ወይንም ወያኔ በማለት በ1970ዎቹ መጀመሪያ በመንግስቱ ሃይለማርያም አገዛዝ ላይ የተጀመረ

“አንድነት” በአባላቶቹ ላይ የሚደርሰው ጥቃት መባባሱን ገለፀ


 
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በአባላቱና በደጋፊዎቹ ላይ የሚደርስባቸው ጥቃትና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ መባባሳቸውን ገለፀ፡፡

Friday, November 8, 2013

Breaking news የግንቦት 7 መሪዎችን ለመግደል የተጠነሰሰው ሴራ ከሸፈ


በኢትዮጵያ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ሃለፊ በአቶ ጌታቸው አሰፋ እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የብራዊ ደህንነት አማካሪ በአቶ ጸጋየ በርሄ ቁጥጥር የተመራና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል መሪዎች ላይ የተቀነባበረው የግድያ ሙከራ ከሸፈ።

ከግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ለግድያ የተላከው ሙሉቀን መስፍን የተባለው ግለሰብ በትናንትናው እለት በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፣ በእየደረጃው ከሚገኙ የደህንነት ሀላፊዎች ጋር በስልክ ሲያደርግ የነበረው የስልክ ለውውጥ በህዝባዊ ሀይሉ የመረጃ ክፍል ሲቀዳ ቆይቷል።

አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን ኢትዮጵያውያኑን ሰደተኛ ሳንጃ እና ቋጨራ ታጠቀዋል ብለው መናገራቸው ተቃውሞ ገጠመው።





ዕለቱ ኖቬበር 4 2013 የሳውዲ አረቢያ መንግስት የምህረት አዋጅ የግዜ ገደብ መጠናቀቅ አስመልክቶ ለተለያዩ የልማት ማህበር አባላት ኤንባሲው አርብ ኖቬብር 1 2013 በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ ስብሰባ ጠርቶ እንደነበር የሚገልጹ ምንጮች ስብሰባው በኢትዮጵያውያን ቆጨራ እና ሳንጃ መታጠቅ ዙሪያ ኤንባሲው ማህብረሰቡን ለመነጋጋር አጀንዳ ኢዞ መቅረቡ ስብሰባው በጣም አሳፋሪ እና ኢትዮጵያውያንን በጅምላ ለመወንጀል ሆን ተብሎ የታቀደ ከስም ማጥፋት ዘመቻ ተለይቶ የማይታይ መሆኑንን ገልጸዋል ። 

ሀገራዊ ውርደት እንዲያበቃ ወያኔን ከሥልጣን ማስወገድ!!!


የወያኔ ገዢ ጉጅሌ በባህርዩ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት አጋጥሟት የማያውቅ ፍጹም ኢሰብዓዊና ነውረኛ ስብስብ እንደሆነ ለመረዳት ኢትዮጵያዊያንን ለማዋረድ የሚጠቀሟቸውን ተግባራትና ቃላትን ማጤን ይበቃል።
በሶማሌ ክልል የኦብነግን ታጣቂዎች ቅስም ለመስበር ልጃገረዶችንና እናቶችን ብቻ ሳይሆን ወንዶችንም ጭምር በቤተሰብ ፊት በደቦ የሚደፍሩ፤ ለዚህ ተግባር የሠለጠኑ የልዩ ጦር አባላት መኖራቸው በስፋት የሚታወቅና በተደጋጋሚም የተዘገበ ጉዳይ ነው። ወያኔ፣ የኦጋዴን ወገኖቻችን በዚህ ጥቃት ተሸማቀው ያነገቡትን መሣሪያ ጥለው ፀጥ-ለጥ ብለው ይገዛሉ ብሎ ተስፋ ያደረገ ቢሆንም እየሆነ ያለው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው። ዛሬ የሶማሌ ክልል ወንዱም ሴቱም፤ ወጣቱም አዛውንቱም በፀረ-ወያኔ አቋም የጋራ መግባባት ላይ ደርሷል። በኦጋዴን የወያኔ አስነዋሪ ጥቃት የፈጠረው ምሬት በውጭ አገራትም በሚደረጉ የፀረ ወያኔ ትግሎች የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች ተሳትፎ እንዲጎለብት አድርጎታል። በሶማሌ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት በሁላችንም ላይ የደረሰ ነውና ቁጭታቸውን እንጋራለን። በሶማሌ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት ሀገራዊ ውርደት ነው።

Wednesday, November 6, 2013

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ከማስረጃ አልባ ፍረጃ እንዲላቀቁ አንድነት አሳሰበ



አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ካለፈው ስህተታቸው በመማር ከአጉልና ማስረጃ አልባ ፍረጃ እንዲላቀቁ አሳሰበ። ፓርቲው ከትናንት በስትያ ባወጣው መግለጫ እንደገለፀው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ባለፈው ሳምንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በመሪ ደረጃ በማይጠበቅ መልኩ የአንድነትን እንቅስቃሴ ስም ለማጥፋት በመሞከራቸው ከዚህ ድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የራሳቸው አጀንዳ የላቸውም፣የሻዕቢያ መልእክት አድራሾች ናቸው ያሉት የራሳችን አጀንዳ እንዳለን

ህወሀት በእነ አቶ ስየ ላይ የጀመረውን ዘመቻ ቀጥሎበታል


 ኢሳት ዜና :-ህወሀት በውስጡ የተነሳበትን መከፋፈል ለማስቀረት በእነ አቶ ስብሀት ነጋ የሚመራው ቡድን የቀድሞ ታጋዮችን በማሰባሰብ ህወሀትን ለማዳን በሚረባረብበት ጊዜ፣ በአቶ ስየ አብርሀ እና ቤተሰቦቻቸው ላይ የተጀመረው ዘመቻ ግን እንደቀጠለ መሆኑ ታውቋል። አቶ ስየ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴያቸው በእጅጉ የተገታ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ( ኢቲቪ) ” የነቀዙ ሀይሎች” በሚል በእርሳቸውና በአቶ ታምራት ላይኔ ላይ የዶክመንታሪ ፊልም ሰርቶ ማዘጋጀቱ ታውቋል። ፊልሙን ለምን አሁን ለመስራት እንደተፈለገ የታወቀ ነገር የለም። ይሁን እንጅ በህወሀት እና በመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀሳብ አመንጭነት ፊልሙ መዘጋጀቱን ለማወቅ ተችሎአል።

አይ አበሻ! አበሻና ሆድ፤ አንድ (ፕ/መስፍን ወልደ ማርያም)



ወያኔና የነፖሊቲካ አጋሮቹ የሚያደርጉትን ለእነሱ የሚመች አከፋፈል ትተን አበሻን ለሁለት እንክፈለው፤ ሆድ ያለውና ሆድ የሌለው፤ ወይም የሚበላና የማይበላ፤ ዛሬ የምናገረው ሆድ ስላለው ወይም ስለሚበላው አበሻ ነው፤ አታውቁት እንደሆነ ተዋወቁት፤ በአጠቃላይ ስንመለከተው ግን የአበሻ ፍቅርም ሆነ ጠብ ለሆድ ነው፤ አበሻን የሚያጣላው፣ የሚያነታርከው፣ የሚያቧጭቀው የሆድ ነገር ነው፤ ለመብላት ነው፤ አንዳንዴም ሎሌውን ለማብላት ነው፤ ግብር ለማግባት ነው።
አዳም አበሻ ሳይሆን አይቀርም፤ ሁሉንም ነገር ብላ ከተከለከለው በቀር ብሎ ያስቀመጠው ይመስላል፤በላባችሁ ወዝ ብሉ ተብለው አዳምና ሔዋን መረገማቸውን አበሻ ገና አልሰማም፤ አበሻ የተፈጠረው ገነት ውስጥ ቁጭ ብለህ ያለውን ሁሉ ብላ በተባለበት ጊዜ ነው፤ እግዚአብሔር አበሻን ሁሉንም ብላ ሲለው ምናልባትም በጆሮው ጭራሽ አታስብ ብሎት ይሆናል፤ እስቲ በመጀመሪያ ስለምግብ እንነጋገር።

Tuesday, November 5, 2013

አንድነት ፓርቲ የመጀመሪያውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርት ይፋ አደረገ


አንድነት ፓርቲ የመጀመሪያውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርት ይፋ አደረገ

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ሕግና ሰብዓዊ መብት ቋሚ ኮሚቴ ያዘጋጀውን በአገሪቷ ውስጥ ተከሰቱ የሚላቸውን የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን

የፖለቲካው ስር ቁማርተኞች! (ተመስገን ደሳለኝ)


Journalist Temasegan Dasalegበሀገራችን መንግስታዊ አስተዳደር የ‹‹ቁማር ህግ››ን ችግር መፍቻ አድርጎ መጠቀም የጀመረበትን ጊዜ ለማስላት ንጉሰ ነገስት ዳግማዊ ምንሊክ እንደ”ተበሉበት” ከሚነግረን የሽኩሹክታ ታሪካችን አንስቶ አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት… እያልን ለመቁጠር እንገደዳለን፡፡ ይሁንና ባለሙያ (በንባብ የደረጀ) ቁማርተኛ ፖለቲከኛ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛበት ድንገቴ ክስተት የ1966ቱ አብዮት ዋዜማ ነው ቢባል ወደ እውነታው ይጠጋል፡፡ ከመንግስቱ ኃ/ማሪያም ‹‹ለምሳ ያሰቡንን፣ ቁርስ አደረግናቸው›› እና የአጥናፉ አባተ ፍፃሜን ጨምሮ የእነተስፋዬ ደበሳይና ብርሃነ መስቀል ረዳ፤ የእነኃይሌ ፊዳና አለሙ አበበ፤ የእነሌንጮ ለታና ባሮ ቱምሳ፤ የእነ አባይ ፀሀዬና አረጋዊ በርሄ፤ የእነታምራት ላይኔና ያሬድ ጥበቡ… ከትግል መድረክ መገለል ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ፌስቡክን ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ሊዘጋ ነው


(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ መንግስት ፌስቡክን ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ሊዘጋ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች ገለጹ። ከአዲስ አበባ የመጡ መረጃዎች እንደጠቆሙት ሕዝቡ በተለይ ነፃ ሚዲያ በሌለበት ሃገር መረጃዎችን ከፌስቡክ በቀላሉ ማግኘት በመቻሉና የንቃት ደረጃውም እየጠነከረ በመሄዱ   የሃይለማርያም ደሳለኝ መንግስት “በመንግስት መሥሪያ ቤቶች እና በትምህርት ቤቶች በከፍተኛ ሁኔታ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየበዛ በመምጣቱ የመማር ማስተማሩን ሂደትም ሆነ የሥራ ሁኔታዎችን አስተጓጉሏል” በሚል ሰንካላ ምክንያት የፌስቡክን አገልግሎት ለማገድ ተዘጋጅቷል።
በግብጽም ሆነ በቱኒዚያ የተነሱት የአረቡ ዓለም አብዮቶች

አርቲስትና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ተሾመ ከሞት ተረፈ



Sunday, November 3, 2013

በሙኒክ ጀርመን የተጠራው የቦንድ ሽያጭ ተቃውሞ ገጠመው


ዶላር ለመሰብሰብ ወደ ሙኒክ ያቀናው የህወሀት ቡድን አልቀናውም


በአባይ ግድብ ስም ቦንድ በመሸጥ ጠቀም ያለ ዶላር ለመሰብሰብ አቅዶ ወደ ጀርመን፣ ሙኒክ ከተማ የተንቀሳቀሰው የህወሀት/ኢህአዴግ መልዕክተኛ ቡድን ከኢትዮጵያውያን የደረሰበትን ከፍተኛ ተቃውሞ መቋቋም ሳይችል ቀርቶ ያሰበውን ዶላር ሳይሰበስብ ቀርቷል።

ብሄራዊ ጭቆናን የማስወገድ ትግሉ ለአንድ ብሄር (ወይ ግለሰብ) የሚተው የግል ስራ አይደለም። Abraha Desta


ኢትዮዽያውያን ዘረኞች አይደለንም፤ በዘር አልተለያየንም። ኢትዮዽያ ዉስጥ የተለያየ ዘር የለም። ዘራችን አንድ ነው፤ የሚለያየው ቋንቋችን ነው። የተለያየ ቋንቋ (ና እምነት) አለን። የተለያየ ቋንቋ መኖር ደግሞ ባህሪያዊ ነው። የተለያየ ቋንቋ መኖር በራሱ ችግር አይደለም። 

“ከ6 ሚሊዮን የኢህአዴግ አባል አንዱ ብሆን ምን ችግር አለው;” አቶ ልደቱ አያሌው


CC
አቶ ልደቱ አያሌው
“ከ6 ሚሊዮን የኢህአዴግ አባል አንዱ ብሆን ምን ችግር አለው;”
አቶ ልደቱ አያሌው
“ወ/ት ብርቱካን የተሰጣት ኃላፊነት አግባብ አይደለም”
“እንባ አውጥቼ አልቅሼ ኃላፊነት በቃኝ እያልኩ ነው የተመረጥኩት”
“ከኢንጂነር ኃይሉ እንዲሕ ያለ ውሸት አልጠብቅም ነበር”

ወይዘሮ አዜብ መስፍን የፓርቲ መልቀቂያ አቀረቡ:



ወይዘሮ አዜብ መስፍን የፓርቲ መልቀቂያ አቀረቡ: ተቀባይነት አላገኘም::#Ethiopia
ሕወሓት ለወይዘሮ አዜብ ስልጣን በመስጠት በስልት ልታጠምዳቸው ነው::#TPLF

"ለእኔ ስም የሚያወጡልኝ ተቃዋሚዎች ሳይሆኑ የሕወሓት ሹሞች ናቸው::" የሚሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት የሆኑት እና የሙስናዋ ወይዘሮ በመባል የሚታወቁት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ለፓርቲያቸው ያቀረቡት የፖ
ለቲካ በቃኝ ማመልከቻ ተቀባይነት ማጣቱ ሲገለጽ የሕወሓት ከፍተኛ ሰዎች ወይዘሮ አዜብን ለማጥመድ በሚያስችል ስልጣን ላይ ሊያስቀምቷቸው እንዳሰቡ ምንጮቹ ጠቁመዋል::የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው በወይዘሮ አዜባ ጋር በዋዛ አንላቀቅም በማለት ቂም በቀላቸውን ሊወጡባቸው ይችላሉ የሚል ግምቶች በሕወሓት አከባቢ እየተነገሩ ነው::

Saturday, November 2, 2013

የኢትዮዽያ መከላከያ T- 72 ታንኮችን ተረከበ


 

Ethiopian Military Receiving T-72 Main Battle Tanks
It appears that the Ethiopian military is receiving T-72 main battle tanks from the Ukraine, with a consignment delivered last month.

Friday, November 1, 2013

4 ሺህ ዶላር ይዞ የተገኘው የናሽናል ጂኦግራፊ ፎቶግራፈር በጋምቤላ ታሰረ


(ፍኖተ ነፃነት) የናሽናል ጂኦግራፊ የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ ሮቢን ሃሞንድ በጋምቤላ ክልል በቁጥጥር ስር መዋሉን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ፓሪስ ከሚገኘው የኢትዩጵያ ኢምባሲ ቪዛ ያገኘው ሮቢን በኢትዩጵያ በተለያዩ ክልሎች በመዘዋወር ፎቶ ግራፍ የማንሳት እቅድ እንደነበረው ተነግሯል፡፡የፎቶግራፍ ጋዜጠኛው ከኢትዩጵያዊ ረዳቱ ጋር ለእስር የተዳረገው 4000 የአሜሪካ ዶላር በእጁ ይዞ በመገኘቱ ነው፡፡ወደ አገር የሚገባ ማንኛውም የውጪ አገር ዜጋ በእጁ የሚገኘውን ገንዘብ ማሳወቅ የሚገባው ቢሆንም ሮቢን ወደ አገር ሲገባ ከገለጸው ገንዘብ በላይ ይዞ መገኘቱ ለእስሩ እንደምክንያት ተወስዷል፡፡

ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ሀገር ቤት ከገባ በኋላ የሰጠው ቃለምልልስ


የአውራምባ ታይምሱ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ Dawit Kebede of Awramba Times

ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከስደት ለምን ተመለሰ?
“እኔ ወደ ሀገሬ ለመምጣት ከማንም ጋር አልተደራደርኩም”ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ
የአውራምባ ታይምሱ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወደ ሀገር ቤት መመለሱን ኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ መዘገቧ አይዘነጋም። ዳዊት ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ በሀገር ውስጥ የሚታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ በ8ኛ ዓመት ቁጥር 425 የረቡዕ ጥቅምት 20/2006 ዓ.ም. ዕትሙ ከዳዊት ጋር ያደረገውን ቆይታ እንደወረደ እንደሚከተለው አቅርበነዋል። ቃለምልልሱን ያደረገው ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሙሉጌታ ነው።

አሳዛኝ ዜና- ስደተኞቹ በሙሉ አለቁ!


ከኒጀር ተነስተው ፣ ሰሃራ በረሃን በማቋረጥ አልጄሪያ ለመድረስ፣ ከዚያም ወደ ሌላ አገር ለመሻገር አንድ መቶ የሚሆኑ ስደተኞች በአንድ መኪና ታጭቀው ጉዞ ይጀምራሉ።