Thursday, August 8, 2013

በባንዲራ ያሸበረቀው አገር አቀፉ የዒድ ክብረ በዓል እና ተቃውሞ እጅግ አስራሚ ድባብ ፈጥሯል




ድምፃችን ይሰማ
የዛሬው ተቃውሞ በፅሁፍና በፎቶ በከፊል!
ከማለዳው 1፡20
በአዲስ አበባ ስታዲየም በሁሉም አቅጣጫ ያለን ሙስሊሞች ከፍተኛ ጥንቃቄ እናድረግ፡፡ በአካባቢያችንን ያሉ ኹኔታዎችን በደምብ እየቃኘን፡፡
ከማለዳው 1፡27
በባንዲራ ያሸበረቀው አገር አቀፉ የዒድ ክብረ በዓል እና ተቃውሞ እጅግ አስገራሚ ድባብ ፈጥሯል፡፡ ግና ምኑም አልተነካም፡፡ አልሀምዱሊላህ!
Ethiopian Muslims
ከማለዳው 1፡30
አዲስ አበባ ስታዲየም እየሞላ ነው፡፡ በጣም ጥቂት ቀርቶታል፡፡
ከማለዳው 1፡34
በጣም በርካታ ሙስሊሞች በመንገድ ላይ ተይዘዋል፡፡ መንግስት ሕገ መንግስታዊ መብታችንን በዚህ በበዓል ቀን እንኳ ለማክበር ፈቃደኛ አይደለም፡፡
ከማለዳው 1፡38

በጣም በርካታ ሙስሊሞች በመንገድ ላይ ተይዘዋል፡፡ መንግስት ሕገ መንግስታዊ መብታችንን በዚህ በበዓል ቀን እንኳ ለማክበር ፈቃደኛ አይደለም፡፡ከዒዱ ሰላት መጠናቀቅ በኋላ በመላው አገሪቱ ተቃውሞን ለመግለጽ በመስከረም 27 የተደረገው የመጅሊስ የሹመት ሂደት ተምሳሌታዊ የቀብር ስነ ስርአት ይፈጸምለታል፡፡ ኢንሻ-አላህ!
ከማለዳው 1፡42
በደቡብ ሐላባ ከተማ የአገሬው ሙስሊም ነቅሎ ሐላባ ስታዲየም ደርሷል፡፡ ዙሪያ ገባው ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› በሚል መፈክር ተሸፍኗል፡፡ የክልሉ ልዩ ኃይል ዙሪያውን አድፍጧል፡፡ አላሁ አክበር!
ከማለዳው 1፡52
የአጋሮ ሕዝብ በተንጣለለ ሜዳ አንድ ላይ ለመስገድ ቢከለከልም አብዛኛው ሕዝብ አዝሐር መስጂድ ከትሟል፡፡ ልዩ ተቃውሞ ከሰላት በኋላ ይፈጸማል፡፡
ከማለዳው 1፡54
ኢቴቪ የቀጥታ ስርጭቱን አሁን ጀምሯል፡፡
ከማለዳው 1፡56
በአዲስ አበባ ስታዲየም ፖሊሶች ሕዝቡን ምንም አላላውስ ብለውታል፡፡
ከማለዳው 1፡58
በአዲስ አበባ ስታዲየም ፖሊሶች ባንዲራ ወደ ውስጥ ይዞ መግባትን ከልክለዋል፡፡ ለባንዲራ ክብር ያለውን ሕዝብ በጸረ አገርነት ሲፈርጅ የከረመው መንግስት አሁን ግን ባንዲራ መያዝን ከልክለውናል፡፡
ከማለዳው 1፡59
በደቡብ ክልል ወልቂጤዎች ተቃውሞ ማሰማታቸውን ጀምረዋል፡፡ አላሁ አክበር!
ከማለዳው 2፡02
በአማራ ክልል በወረባቡ ከተማ ፖሊሶች እና የአካባቢው ሚኒሻዎች ከተማዋን ወረዋታል፡፡ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል፡፡ በከተማዋ ላይ ተክቢራ ማሰማት ከልክለዋል፡፡
ከማለዳው 2፡04
በአፋር ክልል ጎሊና ወረዳ ላይ ሲካሄድ የነበረው ሰላት እና ተቃውሞ በሰላም መጠናቀቁን ምንጮች ገለጹ፡፡፡
ከማለዳው 2፡05
ኢቴቪ የቀጥታ ስርጭቱን አሁን አቋርጧል፡፡ ከጀርባ የንግግር ማቆሚያ ተክቢራ መደረግ ሲጀምር ነው ስርጭት የተቋረጠው፡፡ አላሁ አክበር!
ከማለዳው 2፡06
መንግስት እና መጅሊስ ያዘጋጀውን ካርድ የያዙ ሰዎች በትሪቡን በኩል ሲገቡ ታይተው አሁን ሞላ ተብለዋል፡፡
ከማለዳው 2፡08
እንደተለመደው የመንገድ ትራንስፖርት ህንፃ እና ሌሎች ባካባቢው ያሉ የመንግስት እና የግል ተቋማት የጦርነት ካምፕ መስለዋል፡፡ እኛ ሰላማዊ ነን፡፡
ከማለዳው 2፡09
ሐረር ከተማ በፈደራል ፖሊሶች እና ልዩ ሃይል ፖሊሶች እንዲሁም በጭምብል ለባሾች ተከባለች። በየቦታው ያለው ፍተሻ ግዜ እየገደለ ነው። ህዝበ ሙስሊሙ ከየአቅጣጫው በተክቢራ ወደ እስታዲዬም እየተመመ ይገኛል።
ከማለዳው 2፡12
በአዲስ አበባ የህዝቡን ቁጥር ለማሳነስና የተቃውሞውን ጥንካሬ ለማቀዝቀዝ በሚል መንገዶች በሁሉመ አቅጣጫ በተለይ በልደታ ፍርድ ቤት፣ ቡልጋሪያ ማዞሪያ፣ ሳር ቤት፣ ጎፋ… አቅጣጫዎች መንገድ ቢዘጋም ሰዉ በእግሩ እየተመመ ነው፡፡ አላሁ አክበር!
ከማለዳው 2፡15
በአዲስ አበባ ስታዲየም ውስጡ ሕዝቡ ከመድረኩ በጣም ርቆ እንዲቀመጥ ተገዷል፡፡ የህዝቡ ድምጽ ወደ መድረኩ እና ሚዲያ እንዳይደርስ ታስቦ ይመስላል፡፡
ከማለዳው 2፡18
በአዲስ አበባ የፖሊስ ፒክ አፕ መኪና የዒድ ተክቢራ እያለ በሚመጣው ህዝብ አካባቢ በጣም እየተመላለሰ ነው፡፡ ሰላማዊውን ህዝብ ለምን ያሸብሩታል?
ከማለዳው 2፡20
የመጅሊስ ተወካይ ንግግር ተጀምሯል፡፡ ሕዝቡ ተክቢራውን በተቃውሞ ድምጹ እያሰማ ነው፡፡ አላሁ አክበር!
ከማለዳው 2፡23
የበደሌ ሙሥሊም የጦር ቀጠና በመሰለው ከባቢ ውስጥ በቁርተኝነት ወደ ኢድ ሰላት በመትመም ላይ ይገኛል፡፡
ከማለዳው 2፡24
የመጅሊስ ተወካይ ንግግርን በተቃውሞ ለማስቆም የሚደረገው የተክቢራ ድምጽ ጎልቶ እየወጣ ነው፡፡ ኢቴቪ የቀጥታ ስርጭቱ እንዳይታወክ የጀርባውን ድምጽ ለማስወገድ እየሞከረ ነው፡፡
ከማለዳው 2፡25
መጅሊሶች ንግግር ሲያደርጉ በተክቢራ ለማስቆም ተክቢራ እየተባለ ነው፡፡ ንግግሩም ተክቢራውም ቀጥሏል፡፡
ከማለዳው 2፡29
መንግስት ድራማ እየሰራ ነው፡፡ በስታዲየም ውስጥ የመጅሊሱ ሹመኛ የሚያደርገው ንግግር ወደ ሕዝቡ እየደረሰ አይደለም፡፡ የመጅሊስ ሹመኞች ንግግር በቀጥታ ወደ ካሜራ ብቻ ነው የሚገባው፡፡ የመድረክ ግለሰቦች ንግግር እያደጉ ያሉት ለኢቴቪ ስርጭት ብቻ ነው፡፡
ከማለዳው 2፡32
በሕዝቡና በመድረኩ መካከል ያለው ርቀት ይህን ይመስላል፡፡ ሕዝቡ እንዲህ እንዲርቅ የተደረገው የተቃውሞ ድምጹ ወደ ኢቴቪ ካሜራ ማይክራፎን እንዳይገባ ለማድረግ ነው፡፡ ሕዝቡ ንግግሩን ለማስቆም ተክቢራ በማለት ላይ ይገኛል፡፡ ንግግሩ ለሕዝብ አይሰማም፡፡
ከማለዳው 2፡34
ወደ ስታዲየም እየተመመ የሚገኘውን የባሌ ሮቤ ጀግና ሙስሊም ህዝብ ፖሊስ ‹‹ስታዲየሙ ጭቃ ነው›› በሚል የሀሰት ምክንያት ከመንገድ እየመለሱት ይገኛሉ፡፡
ከማለዳው 2፡38
የኢድ ሰላት አሁን ተጀምሯል፡፡ ሕዝቡ መድረክ ላይ ምን እየተደረገ እንደሆነ መረጃ የለውም፡፡
ከማለዳው 2፡41
ሰላት ሲጀመር የሕዝቡ ድምጽ መሰማት ተጀመረ፡፡ የመድረክ መሪው ተክቢራ ሲያስብል የሕዝቡ ድምጽ አይሰማም ነበር፡፡ አሁን ሰላት ሲጀመር ግን ከጀርባ ያለው የሕዝብ ድምጽ መሰማት ጀምሯል፡፡ ድራማውን ለሰላት ገታ አድርገውታል፡፡
ከማለዳው 2፡42
የአዳማ ከተማ ሙስሊም ያለአንዳች የፕሮፓጋንዳ ዲስኩር ተቃውሞውን አሰምቶ ተበትኗል፡፡ ተቃውሞው በጣም የደመቀ ነበር፡፡ አላሁ አክበር!
ከማለዳው 2፡46
ሰላት ተጠናቆ ኹጥባ ተጀምሯል፡፡ ከስታዲየሙ ውጪ ተቃውሞ ተጀምሯል፡፡ ከመድረክ የሚመጣው ድምጽ ለካሜራ ብቻ ነው እየገባ ያለው፤ ለሕዝቡ አይሰማውም፡፡
ከማለዳው 2፡48
ተቃውሞው በከፍተኛ ወኔ እና ኃይል ተጀምሯል፡፡
ከማለዳው 2፡53
ኢቴቪ ወደ ሕዝቡ ካሜራውን ለማዞር አልፈቀደም በድምጽ ማጥለያ በመጠቀም የመድረኩን ድምጽ ብቻ እያሰራጨ ነው፡፡ ሕዝቡ ከፍተኛ ተቃውሞ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ከማለዳው 2፡57
ኢቴቪ አሁን እያሳያ ያለው ምስል ከሰላት በፊት የነበረውን ምስል የቀጥታ በማስመሰል ነው፡፡ መንግስት በቀጥታ ስርጭቱ ላይ ድራማ እየሰራ ነው፡፡
ከማለዳው 2፡59
በአዲስ አበባ ስታዲየምና ዙሪያው ኔትወርክ እየሰራ አይደለም፡፡
ከማለዳው 3፡09
በቻግኒ የኢድ በኣሉን ማክበር አልተቻለም፡፡ የሚሰገድበትን መስጊድ ፌደራሎች ሰፍረውበት የመንግስታዊ ሃይማኖት ጥቂት ተከታዮች ብቻ እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ በአገሪቱ ምን እየተሰራ ነው?
ከማለዳው 3፡09
አላሁ አክበር! ስታዲየም በተቃውሞ እየተናጠች ነው፡፡ አላሁ አክበር!
ከማለዳው 3፡12
በወልቂጤ ከፍተኛ ግርግር ተነስቷል፡፡ ባለንበት እንረጋጋ፡፡
ከማለዳው 3፡14
በአዲስ አበባ አድማ በታኝ ፖሊሶች መንገድ ትራንስፖርት አካባቢ በሕዝብ መሀል ገብተው ለማሸበር እየሞከሩ ነው፡፡
ከማለዳው 3፡16
አድማ በታኝ ፖሊሶች በአምባሳደር አቅጣጫ በኩል መተላለፊያ ከልክለዋል፡፡
Ethiopian Muslims
ከማለዳው 1፡52
የአጋሮ ሕዝብ በተንጣለለ ሜዳ አንድ ላይ ለመስገድ ቢከለከልም አብዛኛው ሕዝብ አዝሐር መስጂድ ከትሟል፡፡ ልዩ ተቃውሞ ከሰላት በኋላ ይፈጸማል፡፡
Ethiopian Muslims
ከማለዳው 2፡32
በሕዝቡና በመድረኩ መካከል ያለው ርቀት ይህን ይመስላል፡፡ ሕዝቡ እንዲህ እንዲርቅ የተደረገው የተቃውሞ ድምጹ ወደ ኢቴቪ ካሜራ ማይክራፎን እንዳይገባ ለማድረግ ነው፡፡ ሕዝቡ ንግግሩን ለማስቆም ተክቢራ በማለት ላይ ይገኛል፡፡ ንግግሩ ለሕዝብ አይሰማም፡፡
Ethiopian Muslims
ብሔራዊ ቲያትር አካባቢ
Ethiopian Muslims
Ethiopian Muslims
በመስከረም 27 የተደረገው የመጅሊስ የሹመት ሂደት ተምሳሌታዊ የቀብር ስነ ስርአት እየተደረገለት ነው፡፡ አላሁ አክበር!
Ethiopian Muslims
Ethiopian Muslims
ከማለዳው 3፡16
አድማ በታኝ ፖሊሶች በአምባሳደር አቅጣጫ በኩል መተላለፊያ ከልክለዋል፡፡
Ethiopian Muslims
ድሬደዋ
Ethiopian Muslims

No comments:

Post a Comment