Monday, August 19, 2013

ታሎው ኦይል የተባለው ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመሪያውን የነዳጅ ክምችት ማውጣት እንደሚችል ገለጸ


http://api.ning.com/files/uHRAM*dGlS-LmWsm337OZ6BEglttsbvpfPbxSHGm9FJDkyr-usatxf1PiO0iM-XNfEPd*2amUqb2oyvjr4yhddifHjfSxocZ/sabisa.jpg
የኬንያን የነዳጅ ክምችት ያገኘው የእንግሊዙ ታሎው ኦይል እንደገለጸው የነዳጅ ክምችቱ ወደ ጎረቤት ሀገር አትዮጵያ ሊቀጥል ይችላል የሚል እሳቤ ላይ እንዳለ ዋሰሽንግተን ፖስት ዘገበ፡፡ በዚህም መሰረት ታሎው ኦይል ፣ አፍሪካ ኦይል ኮርፖሬሽንና ማራቶን ኦይል ኮርፖሬሽን በደቡብ ኦሞ አካባቢ የሳቢሳ ፕሮጄክት ጉድጓዶችን እንደሚያጠናቅቁ ተገለጸ፡፡
ማርቲን ሙቦጎ የተባለ በኬንያ የታሎው ኦይል ማኔጀር እንዳለው “ የመጀመሪያው የነዳጅ ግኝት በኢትዮጵያ ትልቅ ይሆናል ለሀገሪቱም ትልቅ ታሪክ ነው ፡፡’’ ብሏል
ታሎው ኦይል ባሁኑ ሰዓት የምስራቅ አፍሪካን ተራራማ ቦታዎች በመቃኘት ላይ ሲሆን እይታው በኡጋንዳና በኬንያ የነዳጅ በረከት አስገኝቶለታል፡፡ ለድርጅቱ አዲስ የነዳጅ ክምችት በኢትዮጵያ ተገኘ ማለት አዲስ የነዳጅ ግዛት ሲሆን ለሀገሪቱ መንግስት ደግሞ ከውጭ የሚገዛው የሀይል ምንጭ ቀርቶ እንዲሁም አብዛኛው ኢኮኖሚ ከቡና ሽያጭ ቀረጥ ከማግኘት ይልቅ በነዳጅ ዘይት የተደገፈ ኢኮኖሚ እንዲኖረው ያደርጋል፡፡

የኢትዮጵያ መአድን ሚኒስትር ወ/ሮ ስንቅነሽ እጅጉ እንዳሉት እያንዳንዷን የነዳጅ ዘይት ጠብታ ከውጭ እንደሚያስመጡና ይህ አሰራር መቀየር እነዳለበት ተናግረዋል፡፡
ይህ በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር የሚገኘው የነዳጅ ቦታ በእንግሊዝና በአውሮፓ መሀል የሚገኘውን የሰሜን ባህር(north sea) የተባለውን ባህር የሚያህል ቢሆንም 2400 የነዳጅ ጉድጓድ ካለው የሰሜን ባህር ጋር ሲወዳደር ግን እስካሁን 11 የነዳጅ ጉድጓዶች ብቻ ተቆፍረዋል፡፡ የተፈጥሮ ጋዝ በምስራቃዊ ኢትዮጵያ ቢገኝም ታሎው ኦይልና አፍሪካ ኦይል ትኩረታቸውን በኦሞ አካባቢ ያደረጉበት ምክንያት በኬንያ የሚገኘው የነዳጅ ክምችት በቀጣይነት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ሊሻገር ይችላል በሚል ተስፋ ነው፡፡
የአፍሪካ ኦይል የንግድ እድገት ፕሬዝደንት የሆኑት ጀምስ ፊሊፕስ እንዳሉት ቦታው ናግሚያ ከሚባለው የኬንያ የነዳጅ ክምችት ቦታ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለውና ለኢትዮጵያም ቁልፍ የሆነ የነዳጅ ጉድጓድ እንዳለ ተናግረዋል፡፡
እንደ ሲ.አይ.ኤ. መረጃ በምስራቅ አፍሪካ የሚገኙ ሀገሮች የነፍስወከፍ ገቢ በደረጃ 211ኛ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም ደረጃ ከቶጎ ብፊትና ከዚምቡዋቤ በኋላ ያደርጋቸዋል፡፡
ብራየን ጋላገር የተባለው የለንደኑ ኢንቭሰቴክ ባንክ አናሊስት በሪፖረቱ እንደገለጸው “ናግሚያ የተገኘው ነዳጅ በቀጣይነት ወደ ሳቢሳ እንደሚሄድ ግለጽ ነው፡፡ ሳቢሳ የታመቀና የወደፊት የነዳጅ ማግኛ ሸለቆ ነው፡፡” ብሏል፡፡
ቀጥሎም ጋላገር የኢትዮጵያ መንግስት 10 ፕርሰንት ድርሻ እንደሚኖረው ገልጾ የሳቢሳ ፕሮጄክት 140 ሚሊዮን ባረል ነዳጅ እንደሚኖረው ተናግሯል፡፡ የአፍርካ ኦይሉ ፊሊፕ ደግሞ እሰከ ሴፐቴምበር 9 ድረስ ስለነዳጅ ጉድጓዱ ቁፋሮ ሂደት ምንም ገላጻ እንደማያደጉ አስታውቋል፡፡
የፕሮጄክቱ ባለቤቶች የቻይናው ኩባንያ ቢ.ፒ.ሲ. የከርሰምድራዊ ጥናት በኦሞ ወንዝ ማለትም በኬንያና ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ እንዲደረግ ከኬንያና ኢትዮጵያ መንግስት ጋር ውይይት ላይ ሲሆኑ ድንበሩም ባሁኑ ሰዓት እንደተዘጋ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም መንገዱ ጭቃማ በመሆኑ ለመኪኖች መጓጓዣ አስቸጋሪ ስለሆነ አስፈላጊ ቁሶችን ወደ ድንበሩ ማንቀሳቀስ አስቸጋሪ እንደሆነ ተወርቷል፡፡
ፊሊፕ እንዳሉት የኦሞ ወንዝ አካባቢ የተለየ ቦታ እንደሆነና ከሉዚያናው ሚሲሲፒ ወንዝ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ታናግረዋል፡፡
ነሙራ ሆልዲንግስ የተባለው የጃፓን የፋይናስ ኩባንያ ባሁኑ ወር ባወጣው ዘገባ መሰረት በኬንያና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ድንበር 10 ቢሊዮን ባረል የሚሆን የነዳጅ ዘይትና የተፈጥር ጋዝ ክምችት ይኖረዋል፡፡ ታሎው ኦይልና አፍሪካ ኦይል በዚህ አመት 10 ጉድጓዶችን እንደሚቆፍሩና ከነዚህም ውስጥ ሶስቱ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚሆኑ ተነግሯል፡፡ በተጨማሪም ነሙራ ሆልዲንግስ እንደገለጸው ይህ የነዳጅ ሸለቆ ታሎው ኦይል ኡጋንዳ ውስጥ ካገኘው አስር እጅ እንደሚበልጥ ተናግሯል፡፡

No comments:

Post a Comment