በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አቶ ኦባንግ ሜቶ ”የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ” (http://www.solidaritymovement.org) ሊቀመንበርን ንግግር እንዲያደርጉ ጋብዘው ነበር።”ኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማህበር በእስራኤል” በሚል ማኅበር ስር የተሰባሰቡት ወጣት ኢትዮጵያውያንን በከበረ ሰላምታ በማቅረብ ንግግራቸውን የጀመሩት ኦባንግ ”አቶ መለስ የሚነዳው ባቡር የጥላቻ ባቡር ነው…..አሁን ባቡሩ እየቆመ ነው” ብለዋል።አቶ ኦባንግ ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ ምክርቤት የውጭ ፖሊስ ንዑስ ኮሚቴ ቀርበው በተናገሩት ንግግር የብዙ ኢትዮጵያውያንን ልብ አኩርተዋል። አቶ ኦባንግ በአሜሪካ ምክርቤት ቀርበው ”እኛ አሜሪካኖችንን ነፃነት እንዲሰጡን አንለምንም ይህንን እኛ ማድረግ እንችላለን” ነበር ያሉት።
አቶ ኦባንግ በእስራኤል ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያደረጉት ንግግር ቪድዮ ይመልከቱ።
No comments:
Post a Comment