ኢሳት ዜና:-ተቃውሞው ከአመት በላይ የዘለቀው የድምጻችን ይሰማ ተቃውሞ አንዱ አካል ቢሆንም ፣ የዛሬው የተቃውሞ መነሻ ግን የፌደራል ፖሊሶች ሐሙስ ጧት ከ35 አመታት በላይ ሲያገለግል የነበረውን የወልድያ እርዳታ ማህበር ቢሮ ማሸጋቸውን ተከትሎ የመጣ መሆኑን የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት ገልጸዋል።
ሰላም መስጊድ በሚባለው በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ድምጻችን ይሰማ ፣ መሐይም አይመራንም” የሚሉና ሌሎች መፈክሮችም ተደምጠዋል።
ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ አንዳንድ ከተሞችም ተመሳሳይ ተቃውሞዎች መካሄዳቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል
No comments:
Post a Comment