መቀመጫውን በኒዮርክ ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ቡድኑ /CPJ/ ባለፈው ረቡዕ ይፋ ባደረገው ሪፖርት፤ ጋዜጠኞችን በማሰር ከአለም አስር አገሮች መካከል ኢትዮጵያን በሁለተኛ ደረጃ ያስቀመጠ ሲሆን ኤርትራ ቀዳሚ ሆና፣ ግብፅ በሶስተኝነት ተቀምጣለች፡፡
Saturday, December 21, 2013
Wednesday, December 18, 2013
“አና ጐሜዝ አሁንም ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ይቆረቆራሉ” – አቶ አስራት ጣሴ (የአንድነት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ)
ከአቶ አስራት ጣሴ (የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ)
ከአና ጐሜዝ ጋር ከአንድ ሠዓት ተኩል ለማያንስ ጊዜ ነው የቆየነው፡፡ የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላት ከእኛ ጋ የተገናኙት ገለፃ ለማድረግ አስበው ሣይሆን የእኛን አስተያየት ለመስማት ነበር፡፡ ውይይቱ፣ ኢትዮጵያ ያለችበትን ተጨባጭ ሁኔታ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን እና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችን የሚዳስስ ነበር፡፡ በወቅቱ ከሞላ ጐደል ተደጋጋፊ እንጂ የሚቃረኑ ሀሣቦች አልተነሱም፡፡ በእኔ በኩል፣ በኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል በከፍተኛ ችግርና አደጋ ላይ እንደሚገኝ፣ ኢትዮጵያም መስቀለኛ መንገድ ላይ እንደሆነች፣ ከፊታችን አሳዛኝና አስጊ ሁኔታዎች እንዳሉ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ሕዝቡ ሰላማዊ ትግሉን አስመልክቶ ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታዎች እያሣየ መሆኑን ገልጫለሁ፡፡
“ሰላማዊ ትግል” የሚለው “ሰላማዊ እንቅልፍ” የሚል ደረጃ ላይ
“ሰላማዊ ትግል” የሚለው “ሰላማዊ እንቅልፍ” የሚል ደረጃ ላይ
Tuesday, December 17, 2013
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተመሰረተበትን አንደኛ አመት አስመልክቶ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተመሰረተበትን አንደኛ አመት አስመልክቶ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ
ቀን ታህሳስ 7 2006
ታህሳስ 7 2006 ዓም የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከተመሰረተ አንድ አመት ሞላው። አንድ አመት በጭንቅና በአሳር ለተያዘች የዛሬይቱ ኢትዮጵያና ህዝቧ እጅግ ረጅም ግዜ እንደሆነ ህዝባዊ ሃይሉ በሚገባ ይገነዘባል። ባላፈው አንድ አመት ውስጥ የኢትዮጵያን ህዝብ የመከራ፣ የአሳርና የውርደት ህይወት ይበልጥ እየሰፋ፣ የሚፈጸምበት ግፍ ይበልጥ እየገዘፈ መሄዱን አይተነዋል። በሃገርና በህዝብ ላይ እየወረደ ያለውን ወያኔ ወለድ የስቃይና የፍዳ ናዳ በቅጡ ላጤነው ሃገሪቱና ህዝቧ የአዳዲስ የስቆቃና የመከራ አይነቶች መፈተኛ ቤተ ሙከራዎች እየተደረጉ ለመሆኑ ጥርጥር አይኖረውም። ለሚራበው፣ ለሚረገጠው፣ በግፍ ለታጎረው፣ በኑሮ ውድነት ለሚጠበሰው፣ ለተሰደደው ለተፈናቀለው ኢትዮጵያዊ እንድ አመት በሲኦል የቀናትና የወራት መቁጠሪያ እንደሚለካ ዘመን እጅግ የረዘመ የስቃይ ግዜ ነው።
“ሕወሓት ከመለስ ሞት በኋላ እየተዳከመ ያለ ድርጅት ነው፤ ኢህአዴግ ለዘለዓለም መግዛት አለብኝ የሚል ድርጅት ነው” ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ
ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ ከህወሓት ጋር 17 ዓመታት በትግል ያሣለፉ እና ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዷ ነበሩ፡፡ በ1993 ዓ.ም ከፓርቲው ከተሰናበቱ አባላት አንደ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት የ“አረና” ፓርቲ አባል የሆኑት ወ/ሮ አረጋሽ በአጠቃላይ ጉዳዮች ዙሪያ ከ“ሎሚ” አዘጋጅ ቶማስ አያሌው ጋር ያደረጉት ቆይታ የመጀመሪያ ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
ሎሚ፡- የኢህአዴግ ጭቆናና፣ አፈና፣ የተንሰራፈው በመላው ሀገሪቱ ነው የሚል አቋም ካላችሁ፣ ብሔር ተኮር ፓርቲ የመሰረታችሁበት ምክንያት ምንድነው;
አረጋሽ፡- ፓርቲ የሚመሰረተው በአካባቢ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት አድርጐ ነው፡፡ ተጨባጭ ሁኔታ ስል የማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሰብዓዊ መብት፣ የኢኮኖሚ ችግሮችን ለመጥቀስ ፈልጌ ነው፡፡ ማንኛውም ድርጅት በዚህ መልኩ ነው የሚመሰረተው፡፡ አረናም በዚሁ መሠረት የተመሠረተ ፓርቲ ነው፡፡
Monday, December 16, 2013
በደቡብ ሱዳን የተደረገው መፈንቅለ መንግስት መክሸፉን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ተናገሩ
በደቡብ ሱዳን የተደረገው መፈንቅለ መንግስት መክሸፉን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ተናገሩ የአዲሲቷ አገር መሪ የሆኑት ሳልቫኪር የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ታማኝ ወታደሮች መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሌሊቱን ተኩስ መጀመራቸውን ተናግረዋል። ችግሩ በቁጥጥር ስር መዋሉን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ እንዲህ አይነቱን ድርጊት
ሁለገብ ትግል – ከኔልሰን ማንዴላ ጋር የምንጋራው የትግል ስትራቴጂ ግንቦት 7 ለፍትህና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄም በኔልሰን ማንዴላ ዜና እረፍት የተሰማውን ሐዘን በመግለጽ መግለጫ ያወጣ ቢሆንም የትግል ተሞክሯቸው ለአገራችን ስላለው ጠቀሜታ ተጨማሪ ቁም ነገሮችን ማንሳት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል። ኔልሰን ማንዴላንና የትግል ጓዶቻቸው መሣሪያ እስከማንሳት ያደረሳቸው የደቡብ አፍሪቃ አፓርታይድ አገዛዝ ዋነኛው መገለጫው የባንቱስታን ሕግ ነበር። በዚህ ህግ መሠረት ደቡብ አፍሪቃ ዘርን መሠረት ያደረጉ አስር “ባንቱስታ” የተሰኙ “ራስ ገዝ” ግዛቶች ተቋቁመው ነበር። ያኔ በደቡብ አፍሪቃ አገዛዝ ሥር በነበሩ የደቡብ ምዕራብ ግዛቶች ደግሞ ሌላ አስር ባንቱስታዎች ነበሯቸው።
በእያንዳንዱ ደቡብ አፍሪቃዊ መታወቂያ ባንቱስታው እንዲገልጽ ህጉ ያስገድዳል። የአንዱ ባንቱስታ ነዋሪ ያለልዩ ፈቃድ ወደሌላው ባንቱስታ መሄድ አይችልም። ከዚህም ሌላ ለነጮች ብቻ በተከለሉ ቦታዎች ጥቁሮች ለሥራ ካልሆነ በስተቀር ለሌላ ማናቸው ተግባር እንዳይገኙ ህጉ ያዛል። አፓርታይድ የደቡብ አፍሪቃ ዜጎችን በየዘር ክልሎቻው ውስጥ አጉሮ አገራቸውን እስር ቤታቸው እንዲሆን አደረገው። ይህንን ለመቃወም ኔልሰን ማንዴላ እና የወቅቱ ታጋዮች በመጀመሪያ ሰላማዊ ትግልን ሞከሩ፤ ያ አላዋጣ ሲል መሣሪያ አነሱ። በአሁኑ ሰዓት ባንቱስታን መሰል የክልል አስተዳደር ያለው በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው። ልክ በአፓርታይድ ደቡብ አፍሪቃ እንደነበረው ሁሉ የኛም መታወቂያዎች ዘራችንና ክልላችንን ይገልፃል። በአፓርታይድ ደቡብ አፍሪቃ እንደነበረው ሁሉ እኛም ከክልላችን ውጭ ተንቀሳቅሰን መሥራትና መኖር አንችልም።
Saturday, December 14, 2013
የጠላቶቻችን ተግባርና፤የወዳጆቻችን ዝምታ
ደ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዳሉት ‹‹የጠላቶቻችንን ቃሎች ከምናስታውስ ይልቅስ የወዳጆቻችንን ዝምታ እናስበዋለን›› እኔ ደግሞ፤ የጠላቶቻችንን ተግባርና ግፋዊ ድርጊት እያሰብነው ይቅርታንም እንቸራለን የሚያደርጉትን አያውቁትምና፡፡ የሚፈጸመውን ግፍ፤የሕዝብ መብት ገፈፋ፤ የሰብአዊ መብት መጣስን፤የፍትህን እጠትና ሌላውንም ሁሉ እያዩ እነዳላዩ እየሰሙ እንዳልሰሙ በመሆን ጀሯቸውን የጠቀጠቁትን፤ አፋቸውን የለጎሙትን፤ አንደበታቸውን የዘጉትን ወዳጀቻችንን ግን ይቅርታም አልቸር ልረሳውም አልፈቅድም፡፡
በእስር ስር ያሉትን ዘወትር አብረናቸው እንዳለን ከማሳወቅና እንዳልረሳናቸውና እንዳልተውናቸው ከማሳየት የላቀ ምንም ተስፋ የለም፡፡ እስክንድር ነጋ አንዱዓለም አራጌ ርእዮት ዓለሙና ሌሎችም የግፍ ታሳሪወች በጨካኝና ግፈኛ ገዢ ዋሻ ውስጥ ናቸው፡፡ በየእለቱ ነፍሳቸው እንዲሳሳና እንዲንበረከኩ እየተደረጉ ነው፡፡ ይህን ደግሞ አንሰማውም ዋሸው ጥልቅ መዝጊያው ድርብ ነውና፡፡ ድምጻቸው ታፍኗልና ድምጻቸው ልንሆንና ልንጨህላቸው ይገባል፡፡ ያሉበት ቦታ የግፈኛው አገዛዝ የግፍ ዋሻ በትንፋገት የተሞላና ለበሽታ የሚያጋልጥ በመሆኑ ስቃያቸው ሊሰማን ተገቢ ነው፡፡ ስለኢትየጵያ የፐለቲካ እስረኞች ጉረሯችን እስከሰል መጨህ ያለብን ለታይታ
Friday, December 13, 2013
አጋጣሚዎችን ሁሉ ለራሳቸው ጥቅም የሚያውሉ ነውረኞች ! – አበራ ሽፈራው/ከጀርመን
እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጥር ጥቅምት መጨረሽና ህዳር ወር 2006 እጅግ አሳዛኝና በህይወት እስከአለን ድረስ የማንረሳው ክፉ አጋጣሚ በእህቶቻችንና በወንድሞቻችን ላይ ግድያን፣ መድፈርን፣ እስርን፣ መታረድንም፣ በመኪና እየተገጩም ጭምር መሞትንም መጀመሩን ያየንበትና የሰማንበት:: ክፉ ወር:: ብዙዎቻችን በውስጣችን ከራሳችን ጋር የተሟገትንበት፣ ምን እናድርግ? ብለን ከቅርብ ጓደኞቻችን ጋር የተነጋገርንበት:: ሌሎቻችንም ተሰባስበን በውስጣችን ያለውን ሃዘን በግልጽና በአደባባይ ዓለም ሁሉ እየሰማ የተነፈስንበት:: ሳውዲ አረቢያዎች ለዘመናት አብሮአቸው የነበረውን ጭካኔ በአይናችን የተመለከትንበት ምን አልባትም እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ከዚህ በላይ ሲጨቆኑና ሲረገጡ መኖራቸውንም ለማየት የቻልንበት ጊዜ ይህ ይፋ ወጣ እንጂ::
ጄነራል ሳሞራ የኑስ በውጭ ተቃዋሚዎች የመለስን የበላይነት መስክረዋል አሉ
(ዘ-ሐበሻ) ኢሕአዴግ ለይስሙላ ያከብረዋል እየተባለ በሚተቸውና ለ8ኛ ጊዜ የተከበረውን የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሕገ መንግሥት ቀን በዓል ምክንያት በማድረግ መንግስት ባሳተመው ‘ሕብረ ብሔር’ መጽሔት ላይ ቃለ ምልልስ የሰጡት የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጀነራል ሳሞራ የኑስ መለስ ከሞተ በኋላ በውጭ ያሉ ተቃዋሚዎች የሟቹን አቶ መለስ ዜናዊን የበላይነት መስክረዋልና እናመሰግናቸዋለን አሉ። በሰራዊቱ ውስጥ እኩልነት እንዳለ መናገራቸውም ብዙዎችን አስገርሟል።
Thursday, December 12, 2013
Wednesday, December 11, 2013
አንዱዓለም አራጌ ከእስር ቤት “እኔ እስሩ አልከበደኝም፤ በጣም ያሳዘነኝ ግን በኔ መታሰር ልትጠቀሙበት አልቻላችሁም” አለ
(ዘ-ሐበሻ) የ2005 ዓ.ም የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ምርጥ ተብሎ የተሰየመውና በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት የሚገኘው ወጣቱ ታጋይ አንዱዓለም አራጌ እስር ቤት ሊጠይቁት ለሄዱት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች መልዕክት አስተላለፈ። በጣም ማዘኑንም ገለጸ። ዕድሜ ልክ እስራቱን ተቀብሎ እስር ቤት የሚገኘው አንዷለም አራጌ “ይቅርታ አልጠይቅም” በሚል እስካሁን በእስር ቤት እየማቀቀ ሲሆን “በእኔ መታሰር ብዙ ልትጠቀሙበት ስትችሉ አለመጠቀማችሁ ያሳዝነኛል:: እኔ አሁን በእስር ባለሁበት ሰዓት የኢትዮጵያን ሕዝብ የነፃነት ትግሉን ወደ ፊት ለመግፋት አጋጣሚ ሊሆንላችሁ ቢችልም አልተጠቀማችሁበትም ” ሲል የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን መውቀሱን የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።
Monday, December 9, 2013
የመንግስት ወሮበላ ሚልዮነሮች ወይ ቢልዮነሮች እነማን ናቸው?
የኢትዮጵያ ‘ሚልዮነሮች’!አብረሃ ደስታ
ከአንድ መቶ ዘጠኝ ሺ በላይ ዜጎች ወደ አንድ ሀገር የሚሰደዱባት ሀገረ ኢትዮጵያ ባለ ብዙ ሚልዮነሮች ሆነች አሉን። ወጣት ዜጎቻችን ስደት የሚመርጡበት ምክንያት ምንድነው? እውን መንግስት እንደሚለን ‘ቸግሯቸው ሳይሆን ባቋራጭ ለመበልፀግ ፈልገው ነው’? ወይስ የወላጆቻቸው የማዳበርያ ዕዳ ተሰደው ሰርተው ለመክፈል ነው?
Sunday, December 8, 2013
ወያኔ ቁጥርና ቀጠሮ አያውቅም
30ሺ አይሞሉም የተባሉት ስደተኞች ከ150ሺ በላይ ሆነዋል
ወያኔ እንደሚለው በየአመቱ ከ2ሚ. በላይ የስራ እድል ቢፈጠር፣ ከውጭ ሰራተኛ እናስመጣ ነበር፡፡
የአዲስ አበባ አስተዳደር ባለፈው ሳምንት ባሰራጨው ማስታወቂያ፣ በበርካታ አካባቢዎች ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ የውሃ አገልግሎት እንደሚቋረጥ ገልፆ ነበር፡፡ አዲስ መስመር ለማገናኘው ሦስት ቀን ሙሉ ውሃ ማቋረጥ፣ ግራ ያጋባል፡፡ ሁሉም ነገር ከተዘጋጀኮ፣ አዲሱን መስመር በጥቂት ሰዓታት አገናኝቶ ሥራውን ማጠናቀቅ አያቅትም፡፡ ደግነቱ ቅዳሜ በቀጠሮው ውሃ አልጠፋም፡፡ እሁድ ግን ተቋረጠ። ሰኞና ማክሰኞም እንደዚያው፤ ረቡዕ ሀሙስም… ትናንት አርብም አልመጣም፡፡ መንግስት ጋ ቀጠሮ አይሰራም፡፡ “የአገሪቱና የአህጉሪቱ መዲና” በምትባል ከተማ…ውሃ ከጠፋ ስድስት ቀን ተቆጠረ።
Saturday, December 7, 2013
ከሳውዲ ተመላሽ ዜጎች ንብረታቸው በጉምሩክ እንደተወሰደባቸው ተናገሩ
ህገወጥ ናችሁ ተብለው ከሳውዲ አረቢያ ወደ አገራቸው የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን፤ ለበርካታ አመታት ለፍተን ያፈራነውን ንብረት ይዛችሁ መግባት አትችሉም ተብሎ ተነጥቀናል፡፡ የፍተሻ ሰራተኞች ሻንጣዎቻቸውን በመፈተሽ፣ ሞባይል ከአንድ በላይ ከያዙ ትርፉን በማስቀረት፣ አዳዲስ አልባሳት እና ኤሌክትሮኒክስ ቁሰቁሶች የተወሰኑትን ብቻ በመፍቀድ እና ያመጡትን ወርቆች ግራም በመቀነስ ንብረታቸውን እየወሰዱባቸው እንደሆነ ተመላሾቹ ገልፀዋል፡፡ መሃመድ አባመጫ የተባለ የሳኡዲ ተመላሽ፤ ከሳውዲ ስድስት ሻንጣ ይዞ መምጣቱን ገልፆ፤ ቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ ግን ከሁለት ሻንጣ በላይ ይዞ መግባት እንደማይችል፣ ከአምስት ሞባይሎችም ሁለቱ ብቻ እነደተፈቀደለት ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡ የሳውዲ መንግስት ከአንድ ኪሎ በላይ ወርቅ ይዛችሁ መውጣት አትችሉም የሚል መመሪያ ማሳለፉን የጠቆመው ተመላሹ፤ ንብረቱን እዚያው ጥሎ ለመመለስ መገደዱን ገልጿል፡፡ የሳኡዲ መንግስት እንኳን ከወርቅ በስተቀር ሌላ ንብረታቸውን ሁሉ ይዘው እንዲወጡ መፍቀዱን የገለፀው መሃመድ፤ በአገራቸው ንብረታቸውን እንዳያስገቡ መከልከላቸው እንዳሳዘነው ይናገራል፡፡
በመዲናዋ ምስጢራዊ የወሲብ ገበያ ደርቷል
የትላልቅ ድርጅቶች ፀሃፊዎች፣ ሞዴሎችና ተዋናዮች አሉበት
ድንግልናን በ10ሺ ብር የሚያሻሽጡ ደላሎች ሞልተዋል
የከተማዋ ቱባ ባለሃብቶች “የአገልግሎቱ” ተጠቃሚዎች ናቸው
የከተማዋ ቱባ ባለሃብቶች “የአገልግሎቱ” ተጠቃሚዎች ናቸው
ሲኤምሲ ሣሚት ማዞሪያ አካባቢ ካሉት ዘመናዊ ቪላ ቤቶች በአንደኛው 12ሺ ብር ወርሃዊ ኪራይ እየከፈለች ትኖራለች፡፡ የምታሽከረክረው ኤክስኪዩቲቭ ቶዮታ፣ በየዕለቱ የምትቀያይራቸው እጅግ ውድ ዋጋ ያላቸው አልባሳቶቿና በየመዝናኛ ሥፍራው የምትመዘው ረብጣ ብር የተንደላቀቀ ኑሮ እንደምትመራ ይመሰክራሉ፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናትና መዲናችን አለማቀፋዊ ስብሰባዎችን በምናስተናግድበት ጊዜያት እሷን ፈልጐ ማግኘት የማይታሰብ ነው፡፡
ቦሌ ፍሬንድሽፕ ሕንፃ ላይ በከፈተችው ቡቲክ የምታገኘው ገቢ ይሄን ያህል ሊያዝናናት እንደማይችል የታወቀ ነው፡፡ ገቢ ወጪዋን አጥብቃ የማትቆጣጠርበትን ይህንኑ ቡቲኳን ታናሽ እህቷ ትውልበታለች፡፡ እሷም አልፎ አልፎ “ሥራ” በማይኖራት ጊዜ ብቅ እያለች ትጐበኘዋለች፡፡ ታናሽ እህቷ ቤተሰቡን ሁሉ ቀጥ አድርጋ የምታስተዳድረው እህቷ፤ ስለምትሰራው ምስጢራዊ ሥራ አንዳችም የምታውቀው ነገር ያለ አይመስልም፡፡ እሷ የምታውቀው ከተለያዩ የውጪ አገር ሰዎች ጋር የአየር ባየር ንግድ
ቦሌ ፍሬንድሽፕ ሕንፃ ላይ በከፈተችው ቡቲክ የምታገኘው ገቢ ይሄን ያህል ሊያዝናናት እንደማይችል የታወቀ ነው፡፡ ገቢ ወጪዋን አጥብቃ የማትቆጣጠርበትን ይህንኑ ቡቲኳን ታናሽ እህቷ ትውልበታለች፡፡ እሷም አልፎ አልፎ “ሥራ” በማይኖራት ጊዜ ብቅ እያለች ትጐበኘዋለች፡፡ ታናሽ እህቷ ቤተሰቡን ሁሉ ቀጥ አድርጋ የምታስተዳድረው እህቷ፤ ስለምትሰራው ምስጢራዊ ሥራ አንዳችም የምታውቀው ነገር ያለ አይመስልም፡፡ እሷ የምታውቀው ከተለያዩ የውጪ አገር ሰዎች ጋር የአየር ባየር ንግድ
Thursday, December 5, 2013
ሰበር አስዛኝ ዜና !!! ከወደ ደቡብ አፍሪካ !! ታላቁ አፍሪካዊ መሪ ክቡር ኒሰን ማዴላ ከዚህ አለም በሞት ተለዩን
ሰበር አስዛኝ ዜና !!! ከወደ ደቡብ አፍሪካ !! ታላቁ አፍሪካዊ መሪ ክቡር ኒሰን ማዴላ ከዚህ አለም በሞት ተለዩን ! BBC – South Africa’s Nelson Mandela dies
Mr Mandela, 95, led South Africa’s transition from white-minority rule in the 1990s, after 27 years in prison.
He had been receiving intense home-based medical care for a lung infection after three months in hospital.
Wednesday, December 4, 2013
ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወዳገራቸው የመመለስ ግዴታው የህወሃት/ኢህአዴግ ነው!
ኦባንግ ለቴድሮስ መልክት ላኩ
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን)
ኅዳር 23፣ 2006 ዓም
ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወዳገራቸው የመመለስ ግዴታው የህወሃት/ኢህአዴግ ነው!
ግልጽ ደብዳቤ ለሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ገ/የሱስ
Monday, December 2, 2013
የወያኔ አገዛዝ በመልዕክተኞቹ በኩል ላቀረበው የ“እንደራደር” ጥያቄ ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ምላሽ
ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የገነባዉ ሥርዓት በከፍተኛ ችግሮች የተወጠረ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመሪው ሞት በወያኔ መሀል ያስከተለው ቀውስ፤ የሕዝብ ሁለገብ ትግል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበት መሄድ የፈጠረበት ስጋት እና ምርጫ በደረሰ ቁጥር የሚደርስበት ጭንቀት መጨመር ተደማምረው ውጥረቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እያደረሱት መሆኑን የሚያሳዩ በቂ ምልክቶች አሉ። የእስካሁኑ ተሞክሮዓችን እንደሚያሳየው ወያኔ ውጥረት ሲበዛበትና መዉጪያና መግቢያዉ ሲጠፋዉ ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችን “እንወያይ፣ እንደራደር” በማለት ለውጥረት ማስተንፈሻ ጊዜ የሚገዛ መሆኑን ነው። ሰሞኑን በወያኔ አገዛዝ መልዕክተኞች በኩል የደረሰንን “የእንደራደር” ጥያቄ ንቅናቄያችን በዋናነት ያየው ወያኔ እንደለመደው ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻነት ለመጠቀም እየሞከረ መሆኑን ነው።
ሰበር ዜና ኢህአዴግ-ለግንቦት ሰባት የእንደራደር ጥያቄ አቀረበ።
ሰበር ዜና ወያኔ -ለግንቦት ሰባት የእንደራደር ጥያቄ አቀረበ። ኢሳት በምሽት የዜና እወጃው ዝርዝሩን ያቀርባል። ግን እናተ በቀቀኖች የናተን እንደራደር ተቀብሎ የነጻነት ትግሉን የሚያቆም ድርጅት አይደለም ግንቦት 7 ውስጥ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን የናተን ዘረኝነት እና ደደብነት ጠንቅቀው የሚያውቁ ሽንታም ያላቹህትን ህዝብ ያውረዳቹህትን ሀገር ያጠፍቹህትን ነጻነት ደረቴን ለአረር ብሎ ትግሉን የተቀላቀለ ኢትዮጵያዊ ነው የተሰባሰበበት ስለዚህም ሳትቆነጠጡ ላፈሰሳቹህት ደም ላጠፋቹህት ሀገር ቅጣታቹህን ሳትቀበሉ
Sunday, December 1, 2013
‹‹ድኅረ ምርጫ 97 በኢትዮጵያ ያለው ዲሞክራሲያዊ ምህዳር ጠቧል›› አና ጐሜዝ፣ የአውሮፓ ኅብረት የፓርላማ አባል
ምርጫ 97ን ተከትሎ የአውሮፓ ኅብረትን የምርጫ ታዛቢ ቡድንን የመሩት አና ጐሜዝ ምርጫውን ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ በኢትዮጵያ መንግሥትና በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ላይ የሰላ ትችትና ወቀሳ በመሰንዘር ይታወቃሉ፡፡
ከዘጠኝ ዓመታት ቆይታ በኋላ በ26ኛው የአፍሪካ፣ ካሪቢያን፣ ፓስፊክ እና የአውሮፓ ኅብረት የጋራ የፓርላማ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ የመጡትን አና ጐሜዝን በዴሞክራሲ፣ በእስረኞች አያያዝ፣ በሰብአዊ መብት አጠባበቅ እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ነአምን አሸናፊ አነጋግሯቸዋል፡፡
ከ“ፎርጅድ” ፖለቲከኞች፣ባለሥልጣናት፣ ፓርቲዎች፣ … ይጠብቀን!
ሰሞኑን ፖሊስ በቁጥጥር ሥር የዋለውን የፎርጅድ “ስፔሻሊስት” ጉድ ሰምታችሁልኛል? የመቶ ምናምን መስሪያ ቤቶችን ማህተም፣ ቲተር፣ ወዘተ… በመቅረፅ ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ (ሳይማሩ ድግሪ እኮ ነው!)፣ መንጃ ፈቃድ፣ የጋብቻ ሰርተፊኬት፤ ውክልና፣ ሊብሬና ሌሎች ሰነዶችን “ሲያመርት” መክረሙን የሰማሁት ከኢቴቪ የፖሊስ ፕሮግራም ነው፡፡ (ፎርጅድ በፎርጅድ ሆነናላ!) ይሄኛውን የፎርጅድ “ስፔሻሊስት” ከቀድሞዎቹ ልዩ የሚያደርገው ምን መሰላችሁ? ያልደፈረው የመንግስት መስሪያ ቤትና የግል ተቋማት የለም፡፡
(አይዞህ ያለው ማነው?) የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ የፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የግል ክሊኒኮች፣ የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲዎች፣ ወዘተ (የማን ቀረ ታዲያ!) ማህተሞችን … ፎርጅድ እየሰራ የተለያዩ ማስረጃዎችን ያቀርባል ወይም ይቸበችባል፡፡ (ፎርጅድ ፈላጊው “በሽ” ነው ማለት እኮ ነው!)Saturday, November 30, 2013
Friday, November 29, 2013
ከቤሩት የተሰማ አሰቃቂ መረጃ (ይህን ቪድዮ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ እንዲያዩት አይመከርም)
ወደ ዘ-ሐበሻ ዝግጅት ክፍል በፌስቡክ የግል መልዕክት አንድ እህት ብታነጋግሩኝ አሳዛኝና ማንም ያልዘገበው መረጃ ቤሩት ውስጥ የተፈጸመ አቀብላችኋለሁ አለችን። ፈቃዳችንን ገልጸን ስልኳን ተቀብለን ወደ ቤሩት ደወልንላት። አነጋግርናት። ሌሎችንም እንዲሁ አንጋገርን። ከዚያም የሚከተለው አሳዛኝ መረጃ እንዲህ ተቀናበረ።
የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም! (ግንቦት 7)
በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሁንም መከራና ስቃይ ላይ ናቸው። የደረጃ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተንሰራፋ ነው። በመላው አለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ካለማቋረጥ ያደረገው ወገንና ሀገር አኩሪ ጩኸትና አቤቱታ ችግሩ በአለም ዙሪያ ትኩረት እንዲያገኝ ባያደረግ ኖሮ የወገኖቻችን መከራ ከዚህም በከፋ መልክ ይቀጥል እንደነበር ጥርጥር የለውም። አንድ ቀን እንኳን ለሚገዛው ህዝብ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ተሰምቶት የማያውቀው የወያኔ ጉጅሌ መንግስት እግሩን እየጎተተ ቢሆንም ወደ ችግሩ አቅጣጫ እንዲመለከት የተገደደው በዚሁ የወገን ጩኸት መሆኑ ግልጽ ነው።
የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ከተቃዋሚዎችን ጋር ተወያዩ
ለአውሮፓ፣ ኤዥያ፣ ካሪቢያን፣ፓስፊክና አፍሪካ ጉባኤ አዲስ አበባ የተገኙት የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች በቢሮአቸው ከተቃዋሚዎች ጋር ተወያዩ፡፡ ከስፔን፣ ፖርቱጋል፣ ማልታ፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ የተወከሉ ልኡካን በኢትዮጵያ ስላላው አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ ከተቃዋሚዎች በኩል ከመድረክ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ከአንድነት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና አቶ አስራት ጣሴ፣ ከመኢአድ አቶ አበባው መሀሪ፣ ከሰማያዊ ፓርቲ አቶ ይልቃል ጌትነት እንዲሁም ከኢዴፓ አቶ ልደቱ አያሌውና የፓርቲው ፀሀፊ ተገኝተዋል፡፡ ከተወካዮቹ በኩል የተነሱት ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው፡- 1. የፓርቲዎች ቁጥርስ ለምን በዛ? 2. በህግ አግባብ የተመዘገቡ ስንት ናቸው? 3. በፕሮግራምና በርዕዮተ ዓለም ልዩነታቸውና
Thursday, November 28, 2013
በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች በወገኖቻችን ስም በእጅ አዙር ገንዘብ ማሰባሰብ መጀመራቸው እየተነገረ ነው ።
በሪያድ መለዝ አካባቢ የሚገኝ፡አሚራ ኑራ ዩንቨርስቲ ግቢ ሜዳ ላይ ያለዳስ ብርድ እና ጸሃይ የሚፈራረቅባቸው ከ 7 ሺሕ የሚበልጡ ወገኖቻችን በመግብ ወሃ እና የመጸዳጃ ቦታ እጦት እየተሰቃዩ ነው ። የተጠቀሰው መጠለያ ውስጥ ያሉት ወገኖቻችን አብዛኛዎቹ ሴቶች ህጻናት እና አረጋውያን እንደሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ።
‹‹ሰው ለሰው›› የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትእዛዝ ስክሪፕቱን እንዲቀይር ተገደደ፡፡
ኢሳት ዜና :-በኢትዩጵያ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ በረዥምነቱ ቀዳሚውን ቦታ በመያዝ የሚታውቀው ሰው ለ ሰው ተከታታይ ድራማ 109 ክፍሎች ያህል ከተላለፈ በኃላ፣ ሰዎች በማህበራዊ ድህረ ገጾች የድራማው ተዋንያን የሆነውን በትወና ስሙ አስናቀ የተባለውን ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር በማመሳስል ገጸባህሪውና ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለስልጣናትን በገንዘብ ይገዛሉ ፤ ፍትህን ይረግጣሉ ፤ በሰው ህይዎት ይነግዳሉ፡ ፤ ሰው ያስገድላሉ፤ ህዝብን ያስለቅሳሉ ፤ በወንጀል ይነግዳሉ፤ ሰው በላ እና ነፍሰ ገዳይ አምባገነን ናቸው ሲሉ እንደሚተቹዋቸው ይታወቃል፡፡
Wednesday, November 27, 2013
በዜጎች ህይወት የተደራደረው አገዛዝ ማለፉ አይቀርም
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር)
ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡
በኢህአዴግ አባላት ስም ፓርላማውን በመቆጣጠር ኢህአዴግን ሊጎዱት ይችላል ሲሉ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ተናገሩ
የግንቦት7 እና አክራሪ የእስልምና ሀይሎች
ኢሳት ዜና :-ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ይህን የተናገሩት ” በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመንግስት ቀጣዩ የምርጫ ፈተና” በሚል ርእስ ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ባቀረቡት ጽሁፍ ነው።ኢሳት የሚኒስትሩን ሙሉ ንግግር የያዘ ሰነድ የደረሰው ሲሆን፣ በሰነዱ ግርጌ ላይ ” ለመደበኛ አባላት የማይነገር፣ ለከፍተኛ አመራሮች ብቻ” የሚል ተጽፎበት ይታያል። በዚህ ርእስ ስር ደግሞ ” ቀጣዩ የምክር ቤት አባላት ምርጫ የግንቦት ሰባት እና አክራሪ እስልምና ሀይሎችን የሚያስቀጥሉ አባላት ወንበሩ በኢህአዴግ አባላት ስም ሊነጠቅ ይችላል። ” ብሎአል። ሚኒስትሩ ለዚህ አስተሳሰባቸው የምርጫ 97ትን ሁኔታ እንደማጠቃሻ ተጠቅመዋል። ” የ97 የቅንጅት አሸናፊት አካሄድ ስልት ማለትም የተቃዋሚ አባላት ሁነው በህቡእ ተደራጅተው በኢህአዴግ የአባላትን ካርድ ሙሉ በሙሉ ፓርቲውን ሊጎዱት ይችላሉ” ሲሉ ሚኒስትሩ ጽፈዋል።
Tuesday, November 26, 2013
ሰሞኑንን ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ 12 ነፍሰጡሮችን ጨምሮ ወደ 200 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ጉዳያቸው ባሉበት አልቆ ለሃገራቸው መብቃት እየቻሉ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ መጠለያ መወሰዳቸው እያነጋገረ ነው ።
* ትላንት ማምሻውን በ 17 አውቶብስ ከሪያድ ድንበር ግዜያዊ መጠለያ ተጭነው አሚራ ኑራ እይተባለ የሚጠራ ዩንቨርስቲ ግቢ ባዶ ሜዳ ላይ አንተኛም ኤርፖርት ውሰዱን ብለው ከተሳፈሩበት አውቶብስ አንወርድም ብለው ያመጹ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ዛሬ ረፋዱ ላይ ሪያድ ሺሜሲ አካባቢ ወደ ሚገኝ አስርቤት ተወስደው የጣት አሻራ ሰጥተው መጨረሳቸውን እና ሊሴ ፓሴ መቀበላቸውን ማረጋጋጥ ተችሏል።
ጠጉረ ልውጦች ከአራት ኪሎ እንጅ ከሶማሊያ ወይንም ከኢራቅ ይመጡ ይሆን?
ጠጉረ ልውጡ ‹‹መንግስት››
………
ሰሞኑን በኢቲቪና በሬዲዮ፣ እንዲሁም ህዝቡን እየሰበሰቡ ‹‹ጠጉረ ልውጥ ሰው ካያችሁ ጠቁሙን!›› ሲሉ ሰንብተዋል፡፡
ሰሞኑን በኢቲቪና በሬዲዮ፣ እንዲሁም ህዝቡን እየሰበሰቡ ‹‹ጠጉረ ልውጥ ሰው ካያችሁ ጠቁሙን!›› ሲሉ ሰንብተዋል፡፡
ጠጉረ ልውጥ ማለት አገሪቱን አሊያም ህዝቡን የማያውቅ ማለት አይደለም፡፡ እሱማ ፈልጎም ሆነ አፈላልጎ ወደዛው ደርሷል፡፡ ጠጉረ ልውጥ የሚገኝባት አገርም ሆነ ህዝብ በውል የማያውቁት በዕድ ማለት ነው፡
Monday, November 25, 2013
“አንዱዓለም አራጌ በትግራይ ሕዝብ የሚወደድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ነው” አብርሃ ደስታ
ከመቀሌ ኢትዮጵያ በየጊዜው በፌስቡክ እና በተለያዩ ድረገጾች ወቅታዊ መረጃዎችን በማድረስ የሚታወቀው አብርሃ ደስታ አንዷአለም አራጌ በትግራይ ሕዝብ የሚወደድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ነው አለ።
የ ታላቁ ሩጫ ተሳታፊዎች ተቃዉሟቸዉን አሰሙ!!!
ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባል ወገኖች ዛሬ በተካሄደዉ የ ታላቁ ሩጫ ላይ በሳዑዲ ስለሚሞቱና ስለሚንገላቱ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸዉን ሲያሰሙና በመንግስትም ላይ ወቀሳቸዉን በመፈክር እዲዲሁም በዜማ አሰምተዋል፡፡ መንግሰት በዚህ ሩጫ ላይ ህብረተሰቡ የሰማያዊ ፓርቲን ጥሪ እዳይቀበል በአዘጋጀቹ በኩል ቢያሳስብም(ጥቁር ሪቫን እንዳይደረግ) የሀገር ፍቅር ያቃጠላቸዉና የወገኖቻቸዉ ጥቃት ያተሰማቸዉተሳታፊዎች ከፍተኛ የፖሊስና የደህንነት ቁጥጥር ከቁብ ሳይቆጥሩ “በሳዑዲ ነገር እንነጋገር የሳዑዲን ነገር ” ሲሉ አርፍደዋል፡፡ ገና ከመግቢያዉ ጀምሮ ከፍተኛ ፍተሻ ሲደረግ የነበረ ቢሆንም አብዛኞቹ ተሳታፊዎች ሪቫኑን ትተዉ በጥቁር ኮፍያና ሱሪዎች ሩጫዉን መካፈል ችለዋል(በተቃዉሞዉ የተሳተፉቱ)፡፡
Sunday, November 24, 2013
ለዜጎቹ የማይቆረቆርና ጥብቅና የማይቆም መንግስት (ከአስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚኬኤል)
በዚሁ ባለንበት ዘመን ያለፉት ስርአቶች ወደኃላ ተመልሰን ስናስታውስና አሁን ያለውን የህ.ወ.ሓ.ት መንግስት ስንመለከት ኢትዮጵያውያንን ለስድት የሚዳርጓቸዉ ችግሮች ነበሩ።
“እኔ ራሴ ስድስት ያበዱ ሴቶችን ይዤ መጥቻለሁ..” ራውዳ ጀማል – ከሳዑዲ ተመላሽ ኢትዮጵያዊት (ቃለ ምልልስ)
በሃገር ቤት እየታተመ የሚወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ ኢትዮጵያውያን ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። ቃለ ምልልሱ ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም ትዘግባቸው የነበሩ የሳዑዲ ሕይወቶችን የሚያጠናክሩ በመሆናቸው ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው ያደረገችውን ቃለምልልስ ለአንባቢዎቻችን እንደወረደ ይኸው፦
Saturday, November 23, 2013
ከሳኡዲ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ሰቆቃ
ሰሞኑን በህገወጥ መንገድ ሳኡዲ አረቢያ ከገቡ ብዙ ሺ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች መካከል ዓለም አቀፍ የስደተኞ ተቋም ከ350 በላይ የሚሆኑትን ወደ አገራቸው መልሷቸዋል፡፡ ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው በተቋሙ መጠለያ ጣቢያ ያገኘቻቸውን ሦስት ተመላሾች አነጋግራለች፡፡
“ሳኡዲ ወርቅ እየዘነበ ነው ቢሉኝ አልሰማም” አብዱ እንድሪስ
“ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት እየተሰቃዩ ናቸው” እንድሪስ መሃመድ
“አበሻ ለእነሱ ርካሽ እቃ ማለት ነው” እንድሪስ የሱፍ
“ሳኡዲ ወርቅ እየዘነበ ነው ቢሉኝ አልሰማም” አብዱ እንድሪስ
“ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት እየተሰቃዩ ናቸው” እንድሪስ መሃመድ
“አበሻ ለእነሱ ርካሽ እቃ ማለት ነው” እንድሪስ የሱፍ
በሳውዲ ለሚገኙ ወገኖቻችን በአፋጣኝ እንድረስ፤ በወያኔ ላይ በጋራ እንነሳ!!!
በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው መጠን የለሽ የመብት ጥሰት ለመቃወም በተለያዩ የዓለም አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በየአገራቱ የሚገኙ የሳውዲን ኢምባሲዎችን በተቃውሞ እያጨናነቁ ነው። በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ዘግኛኝ በደል የተሰማቸውን ጥልቅ የመጠቃት ስሜት ኢትዮጵያን በተቃውሞ ሰልፎቹ ላይ በሚያሰሟቸው መሪር የሐዘን እንጉሮችና የቁጭት ንግግሮች እየገለፁ ነው። ከሐዘንና ቁጭት ባለፈም ለበደል ለተጋለጡ ወገኖቻችን አስቸኳይ ሰብዓዊ ርዳታ ለማድረስ እና የዲፕሎማሲ ድጋፍን ለማሰባሰብ ዓለም ዓቀፍ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ሥራውን ጀምሯል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ይህንን ዓለም ዓቀፍ ጥረት ለመደገፍ በውጭ አገራት የሚገኙ አባላቱ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ መመሪያ አስተላልፏል።
[የሳዑዲ ጉዳይ]፦ የዮሴፍን ውለታ የማያውቅ ሌላ ፈርኦን ተነሳ
ከመልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ገብረሚካኤል
(በሚኒሶታ የቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክ አስተዳዳሪ)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። አሜን።
ቅዱሱ መጽሐፍ የሃይማኖት ብቻ መጽሐፍ ሳይሆን የታሪክም ምስክር ነው። ዮሴፍ በተሰደደበት በምድረ ግብጽ ኑሮውን ብቻ እያሸነፈ የኖረ አልነበረም። የግብጽ አስተዳደር በመልካምና ፍትሃዊ በሆነ የገንዘብ አከፋፈልና በንብረት አጠባበቅ ያገለገለ ለግብጽ ህዝብና መንግስት ባለውለታ ነበር። ህዝበ እስራኤል በችግር ምክንያት ተሰደው በመልካም ጸባይ ኑሯቸውን እያሸነፉ ምድረ ግብጽን እያለሙ፤ እግዚአብሔርን እያመለኩ፤ ሀገራቸውንም እያሰቡ፤ የሚመለሱበትንም ቀን በተስፋ እየጠበቁ ይኖሩ ነበር። በሁዋላ ግን የዮሴፍን ውለታ የማያውቅ ሌላ ፈርኦን ተነሳ። በህዝበ እስራኤል ላይ ግፍና መከራ ፤ ሰቆቃና ሞት አጸናባቸው። እግዚአብርሔርም ካህኑን አሮንንና መስፍኑን ሙሴን አስነሳ፤ ህዝቡንም ይዘው ወጡ ይላይ ቅዱሱ መጽሐፍ። ቅድስቲቷ ሀገር ኢትዮጵያ ለዜጎቿና ለሌላው ዓለም ባለውለታ ናት።
ቅዱሱ መጽሐፍ የሃይማኖት ብቻ መጽሐፍ ሳይሆን የታሪክም ምስክር ነው። ዮሴፍ በተሰደደበት በምድረ ግብጽ ኑሮውን ብቻ እያሸነፈ የኖረ አልነበረም። የግብጽ አስተዳደር በመልካምና ፍትሃዊ በሆነ የገንዘብ አከፋፈልና በንብረት አጠባበቅ ያገለገለ ለግብጽ ህዝብና መንግስት ባለውለታ ነበር። ህዝበ እስራኤል በችግር ምክንያት ተሰደው በመልካም ጸባይ ኑሯቸውን እያሸነፉ ምድረ ግብጽን እያለሙ፤ እግዚአብሔርን እያመለኩ፤ ሀገራቸውንም እያሰቡ፤ የሚመለሱበትንም ቀን በተስፋ እየጠበቁ ይኖሩ ነበር። በሁዋላ ግን የዮሴፍን ውለታ የማያውቅ ሌላ ፈርኦን ተነሳ። በህዝበ እስራኤል ላይ ግፍና መከራ ፤ ሰቆቃና ሞት አጸናባቸው። እግዚአብርሔርም ካህኑን አሮንንና መስፍኑን ሙሴን አስነሳ፤ ህዝቡንም ይዘው ወጡ ይላይ ቅዱሱ መጽሐፍ። ቅድስቲቷ ሀገር ኢትዮጵያ ለዜጎቿና ለሌላው ዓለም ባለውለታ ናት።
ሰበር ዜና፡- በአሜሪካ፣ ሜሪላንድ ክፍለ ግዛት፣ በዛሬው እለት ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ቢኒያም አሰፋ እና ባለቤቱ፣ የ3 ወር ህፃን ልጃቸውም በጥይት መሞታቸው ተዘገበ፤
ሰበር ዜና፡- በአሜሪካ፣ ሜሪላንድ ክፍለ ግዛት፣ በዛሬው እለት ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ቢኒያም አሰፋ እና ባለቤቱ፣ የ3 ወር ህፃን ልጃቸውም በጥይት መሞታቸው ተዘገበ፤ ባልና ሚስቱ ራሳቸውን ያጥፉ ወይም ይገዳደሉ አልታወቀም። ይሄ ሁሉ ሲካሄድ የ5 አመት ልጃቸው ወደ ጎረቤት አምልጣ ተርፋለች። ሙሉ ዜናው እነሆ!
NEW MARKET, Md. (WUSA9) — The Frederick County Sheriff’s Office have identified the three people, including an infant, who died after a shooting Wednesday night.
Friday, November 22, 2013
ኦባንግ – ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር እየሠራሁ ነው አሉ. የሳዑዲ ልዑል አንጋቾቻቸውን አወደሱ
በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ፈር የለቀቀ አስነዋሪ ግፍ ዓለምአቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡ የሳዑዲ ልዑል ሰብዓዊነት የረገፈበትንና በግፍ የተሞላ የወሮበላ ተግባር የሚፈጸምበትን አሰቃቂ ተግባር የሚከናውኑትን አንጋቾች አሞካሹ፡፡
ያለ አንዳች ልዩነት ኢትዮጵያውያን በኅብረት ድምጻቸውን በማሰማት እየተቃወሙት ያለውን ኢሰብዓዊ ተግባር አስመልክቶ በተለያዩ መንገዶች ይፋ ከሆኑት በተጨማሪ ድብቅ መረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ የጋራ ንቅናቄው ከዓለምአቀፍ የመብት ተቋማት ጋር በቅርበት እየተሰራ ስላለው ዝርዝር ጉዳይ ግን ከሁኔታው ምስጢራዊነት አኳያ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
የህወሓት እኩይ ተግባር እያደረ ይገለጣል!! (ኢንጂኔር አብደልውሀብ ቡሽራ – መቀሌ)
ከሁለት ሳምንታት በፊት ወደ ሽሬ ለመሄድ ወደ መቀሌ አውቶብስ ተራ ሄድኩና በሰላም ባስ አውቶብስ ተሳፍሬ ጉዞየን ጀመርኩ:: እየተጓዝን እያለን በተቀመጥኩበት ወንበር አጠገብ ሁለት ሰዎች ነበሩ:: ሰዎቹ ከዛ በፊት አይቻቸው አላውቅም:: ሁለቱም አካል ጉዳተኞች ናቸው:: በመንገዳችን እየተጓዝን እያለን ሁለቱ ሰዎች የድሮ ትዝታቸው እያነሱ እያወሩ ነበሩና እኔም የነሱ ወሬ አዳምጥ ነበርኩ:: እንደዛ ቆየሁና ወሬያቸው
Thursday, November 21, 2013
በመልሶ ማልማት ፕሮግራም 16 ሔክታር ላይ ያረፈው «አሜሪካ ግቢ» ሊፈርስ ነው
•በዚህ ዓመት 200 ሔክታር መሬት ላይ ያረፉ ቤቶች ለመልሶ ልማት ይፈርሳሉ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመልሶ ማልማት ፕሮግራሙ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከታላቁ አንዋር መስጊድ ፊት ለፊት በሚገኘውና «አሜሪካ ግቢ» ተብሎ በሚጠራው መንደር የሚገኙ መኖሪያ ቤቶችንና ንግድ ቤቶችን ሊያፈርስ ነው፡፡
የስዊድን የጦር ፍርድ-ቤት አቃቢ-ህግ በኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ወሰነ፡፡
ኢሳት ዜና :-የጦር ፍርድ ቤቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በቅርቡ በኦጋዴን የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በተመለከተ፣ የክልሉ የወጣቶች ሊቀመንበርና የፕሬዚዳንቱ የግል ዌብሳት ማኔጀር እና አማካሪ የነበረው ወጣት አብዱላሂ ሁሴን በኦጋዴን የጦር ወንጀልና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸሙን የሚያሳይ ማስረጃ ለፍርድ ቤቱ አቃቢ ህግ ማቅረቡን ተከትሎ ነው።
Monday, November 18, 2013
በገዛ ሀገራችን መንግስታዊ ሽፍቶችም ሆነ በተሰደዱበት ሀገር ሰዎች መደፈሩ ፣ መዋረዱ መቼ ይሆን የሚቆመው ?
“… በየምሽቱ ሁላችንንም ወደ ምርመራ ክፍል ይወስዱናል ፡፡ ከዚያም እያንዳችንን ለያይተው ይገርፉናል ፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ስጠራ ሶስት ወንዶች በክፍል ውስጥ ይጠብቁኝ ነበር ፡፡ ወዲያዉኑ ሶስቱም በየተራ እየተፈራረቁ ደፈሩኝ ፡፡ ወደነበርንበት ጉድጓድ ስመለስ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃየሁ ነበር ፡፡ አሁን ድረስ ህክምና ማግኘት አልቻልኩም ፡፡
Sunday, November 17, 2013
ይድረስ ለኢትዮጵያ ፖሊሶችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት
በየቦታው ተበትናችሁ ለአገር የሚበጅ ስራ እየሰራን ነው ለምትሉ የፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሙሉ። እንዴት ከርማችሁልኛል? እንደ አገር ልጅ ብናፍቃችሁም እንኳ የናንተ እንጀራና የኔ ኑሮ አልገጥም ብሎ ካጠገባችሁ ከራቅሁ አመታት አልፈዋል። ብዙ ሰዎች የሰው ልብ ያላችሁ፣ አዛኝ አንጀት ያላችሁ መሆናችሁን ይጠራጠሩ ይሆናል። እኔ ግን እንደሱ አላስብም ብዙዎቻችሁ ድህነት በግዱ ገፍትሮ እዚህ ውስጥ እንደ ጨመራችሁ አውቃለሁ። ምክንያቱም ብዙ ጓደኞቼ የሚላስ የሚቀመስ ሲያጡ፣ እንደኔ ለመሰደድ መድፈር ሲያቅታችውና ቢፈልጉም እንኳን ሱዳንና ኬንያ የምታደርስ ገንዘብ በማጣታቸው እንጀራ ብለው የገቡ ብዙ እንዳሉ አውቃለሁ። እነዚህ በሙሉ የድሀ ልጆች ቤት ተቀምጦ በረሀብ ከመሞት የምችለውን አድርጌ እኖራለሁ ብለው እንደሚኖሩ አውቃለሁና በተለይ እናንተ ከዚህ የመከራ ማጥ እንድትወጡልኝ አምላኬን መለመን አልተውኩም። ግምገማ ፈርታችሁ የራሳችሁን ወገን በዱላ መጨፍጨፍ እንዴት እንደሚሰማ አውቀዋለሁ። ባዶ እጁን ያለን ሰውማ በጥይት መግደል የባሰ ነው። በተለይ ያልበላን ሆድ ተርቦ የሚያውቅ ሆድ እንዲህ ያለውን ግፍ በደንብ ያውቃል። ዞሮ ዞር የሚመታውም ሆነ የሚገደለው የናንተ ዘመድ እንኳን ባይሆን አንዱ ቦታ ተመድቦ የሚሰራ የባልደረባችሁ ዘመድ መሆኑ መች ይቀራል።
Friday, November 15, 2013
ህወሃት ፈቀደ እኛም ተዋረድን ,መንግሥት አልባ አገር!
የብዙ ሺህ ዘመናት የመንግሥትነት ታሪክ የነበራት አገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ መንግሥት አልባ አገር ናት ብሎ ደፍሮ መናገር የሚቻልበት ወቅት ላይ ደርሰናል።
ኢትዮጵያ የፀረ ቅኝ አገዛዝ ትግል ፋና ወጊና የበርካታ ጥቁር ሕዝብ የነፃነት ትግል ማነቃቂያ ምሳሌ ሆና ቆይታለች፤ ህዝቧም ክብር ያለው ነበር። አሁን ባለንበት ዘመን ግን ኢትዮጵያዊነት የሚያሳፍር የኢትዮጵያውያንም ዋጋ ከእንስሳት ይልቅ የወረደበት ወቅት ላይ እንገኛለን።
መቋጫ ያጠው የወገኖቻችን ስቃይ እና ሞት በሳውዲ አረቢያ ፡አሁንም ቀጥሏል !
ትላንት አመሻሹ ላይ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፍሃ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገርሽቶ በዋለው ተቃውሞ የተጓዳ የሞተ ባይኖርም ኢትዮጵያውያኑ ድምጻቸውን ከፍ አድረገው አንድነን አንድነን … መብታችን ይከበር ….እኛም ሃገር አለን ወዘተ… በሚል መፈክር ታጅበው ብሷታቸውን ሲያሰሙ መዋላቸውን የሚገልጹ የአይን እማኞች የሳውዲ የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞውን ለመብተን በከፈቱት ቶክስ ይሰማ በነብረው የጥይት ድምጽ አካባቢውን ወደ ጦርነት አውድማ ለውጦት ማምሸቱን የገልጻሉ።
ይህንንም ተከትሎ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ተጨማሪ ልዩ ፈጥኖ ደራሽ፡ ኮማንዶዎች ቦታው በመድረስ ተቃውሞውን መግታት ተችሎል ብለዋል ። እንዚህ ምንጮች ትላንት ተቀስቅሷ በነበረው ሁከት ጥቂት ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መደሱን ገልጸዋል። ሰምኑን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በውጭ፡ሃገር ነዋሪዎች ላይ ያወጣው ህግ የግዜ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች በኢትዮጵያውያኑ ላይ እየወስዱ ባሉት የተናጥል እርምጃ አያሌ ወገኖቻችን ወደ ሃገሩ ለመምለስ ከየመኖሪያ ቤቱ ነቅሎ አደባባይ ቢወጣም ወደ ሃገር መግባት የሚያስችሉት ነግሮች በመንግስ በኩል ባለመኖሩ ከእልቂት ተርፈው ወደ እስርቤት የተጓጓዙ ከ 20 ሺህ የሚበልጡ ወገኖቻችን በምግብ ወሃ እና የመጸዳጃ ቦታ እጦት እይተሰቃዩ እንደሚገኙ ተግልጾል።
ይህንንም ተከትሎ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ተጨማሪ ልዩ ፈጥኖ ደራሽ፡ ኮማንዶዎች ቦታው በመድረስ ተቃውሞውን መግታት ተችሎል ብለዋል ። እንዚህ ምንጮች ትላንት ተቀስቅሷ በነበረው ሁከት ጥቂት ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መደሱን ገልጸዋል። ሰምኑን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በውጭ፡ሃገር ነዋሪዎች ላይ ያወጣው ህግ የግዜ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች በኢትዮጵያውያኑ ላይ እየወስዱ ባሉት የተናጥል እርምጃ አያሌ ወገኖቻችን ወደ ሃገሩ ለመምለስ ከየመኖሪያ ቤቱ ነቅሎ አደባባይ ቢወጣም ወደ ሃገር መግባት የሚያስችሉት ነግሮች በመንግስ በኩል ባለመኖሩ ከእልቂት ተርፈው ወደ እስርቤት የተጓጓዙ ከ 20 ሺህ የሚበልጡ ወገኖቻችን በምግብ ወሃ እና የመጸዳጃ ቦታ እጦት እይተሰቃዩ እንደሚገኙ ተግልጾል።
Thursday, November 14, 2013
ዳግማዊ ሆሎኮስት በኢትዮጵያውያን ላይ? ከዲያቆን ዓባይነህ ካሤ
ኢትዮጵያውያን ደማቸው የዐረብን አስፋልት አቀለመው፡፡ ባንዲራውን በራሱ ላይ ሸብ ያደረገው የእማማዬ ልጅ የእኔ ጀግና ማንነቱን እየተናገረ በአናቱ ላይ የወረደውን የድንጋዩን ናዳ በሀገሩ ፍቅር ተቋቁሞ በክብር አሸለበ፡፡ ለእርሱ ከዚህ በላይ ሌላ ድል አልነበረምና፡፡ ድንጋዩስ እርሱን አሳርፎታል፡፡ ነፍሱን ይማርልን እንጂ! ባንዲራችን ግን እንደተመታች እንደታመመች ናት፡፡ እውን ይኽ የሆነው በእኛ ላይ ነው?
ይህቺ ባንዲራ እኮ ጨርቅ አይደለችም፡፡ ያ በሳኡዲ መሬት ተወግሮ የሞተው ወንድሜ የኮራባት በሞቱ ጊዜ የለበሳት የክብሩ፣ የማንነቱ መገለጫ እንጂ፡፡ ማንም ባይደርስለት ባንዲራው ነበረችለት፡፡ በእርሷ ተጽናና፡፡ ሞተ አልለውም መሰከረ እንጂ፡፡ ባንዲራ ለብሶ መከራን መጋፈጥ የሰማእታት ወግ ነው፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)