(ዘ-ሐበሻ) በቅርቡ ወደ ሰሜን አሜሪካ የመጣው እና ከስራ ባልደረባው ከኮሜዲያን ተመስገን ባትሪ ጋር በመሆን የኮሜዲ ሥራውን እየተዟዟረ በማቅረብ ላይ የሚገኘው ኮሜዲያን ዶክሌ (ወንደሰን ብርሃኑ) በቨርጂኒያ አሌክዛንደሪያ ሆስፒታል ኢመርጀንሲ ሩም ገባ በሚል የተሰራጨው መረጃን ተከትሎ ዘ-ሐበሻ ባደረገችው ማጣራት ኮሜዲያኑ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ አረጋግጣለች።
ይህ ወሬ እንደተሰማ ዘ-ሐበሻ ኮሜዲያኑን ወደ አሜሪካ ወዳስመጣው ያቆብ ፕሮሞተር ደውላ የፕሮሞተሩ ስልክ ባይነሳም ከአዲስ አበባ አብሮት ወደመጣውና በቨርጂኒያ አንድ ቤት ውስጥ አብሮት ወደሚኖረው የሥራ ባልደረባው ኮሜዲያን ተመስገን ባትሪ ጋር በመደወል እንዳረጋገጠችው ኮሜዲያን ዶክሌ ትናንት ምሽት ከገባበት የኢመርጀንሲ ሩም በመውጣት አሁን እቤቱ ይገኛል። እንደ ኮሜዲያን ተመስገን ባትሪ ገለጻ በዶክሌ ላይ በ እግሩ ላይ በወጣች እባጭ የተነሳ አላራምድ ብላው ወደ ኢመርጀንሲ ሩም ሄዷል። ሆኖም ግን በተደረገለት ህክምና አርቲስቱ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛል።
ለኮሜዲያን ተመስገን ዘ-ሐበሻ ‘እንደሚታወቀው በሰሜን አሜሪካ እየተዟዟራችሁ ከዶክሌ ጋር ሥራችሁን እያቀረባችሁ ነው፤ ይህ አደጋ ከሥራችሁ ያቆማችሁ ይሆን?” በሚል ላቀረበችው ጥያቄ “አሁን ዶክሌ በመልካም ሁኔታ ላይ ስለሚገኝከሥራችን የሚያግደን ነገር የለም” ብሏል።
ከኮሜዲያን ተመስገን ጋር በስልክ ያደረግነው ምልልስ የሚከተለው ነው፦http://www.zehabesha.com/amharic/archives/10957
(ዘ-ሐበሻ)
No comments:
Post a Comment