Wednesday, July 31, 2013
መረጃ በጨዋታ፤ በዱባይ ኤንባሲያችን ሆኗል አሉ “ገዳይ”
መረጃ በጨዋታ፤ በዱባይ ኤንባሲያችን ሆኗል አሉ “ገዳይ”
ዱባይ ሆይ የእህቶቻችን ሀገር እንደምን ነሽ… ለመሆኑስ እህቶቻችንን እንዴት ናቸው…በሻርጃ እና አቡዳቢ ጉያዎችሽ የደበቅሻቸው ጎረምሶችሽ በዚህ ሰዓት ምን እያሏቸው ይሆን… “ማዳሞችሽስ” ስንቷን የሀገሬ ሴት እየገላመጡ ስነቷንስ እያመናጨቁ ይሆን…
በፌስ ቡክ የመልዕክት ሳጥኔ አንድ መልዕክት መጣ፡፡ እንዲህ ይላል “በዱባይ ኤንባሲያችን እየሆነ ስላለው ነገር ልነግርህ ነበር” እኔስ ማነኝ፤ እስቲ አምጪው አልኳታ፤
በዩናይትድ አረብ ኢምሬት ዱባይ ኢትዮጵያ ኤንባሲ አሰራሩ ከይሲ ቢባል ይቀላል፡፡ እህቶቻችን ፓስፖርት ለማሳደስ ወይም ለአንድ ጉዳይ ወደ ኤንባሲ ደጃፍ ልክ ሲደርሱ የድሮ ቀበሌ አቀባበል ይደረግላቸዋል፡፡ ቀበሌ ትዝ ይልዎታል ወዳጄ… ዘበኛውም ሊቀመንበሩም እኩል ሰው የማመናጨቅ ስልጣን የተሰጣቸው ቦታ እኮ ቀበሌ ነው፡፡ (በነገራችን ላይ አሁን ግን ቀበሌ ተሸሽሏል፡፡ እኔ ሽሮሜዳን ትቼ “ልነካው” የነበረ ሰሞን ቀበሌ የሄደ ሰው የሚደረግለት እንክብካቤ… እንደው ያ ደህንነት ወዳጄ “ወግሞ” ባይዘኝ ኖሮ ለቀበሌያችን ፀባይ መሻሻል ስልስ እዛው ብኖር እመርጥ ነበር፡፡)
Tuesday, July 30, 2013
“ጴጥሮስ ያቺን” ቃል!
“ፋሺስቶች ያገራችንን አርበኞች ሽፍታ ቢሏቸው እውነት እንዳይመስላችሁ፡፡ ሸፍታ ማለት ያለ አገሩ መጥቶ የሰውን አገር የሚወር ይህ በመካከላችሁ መጥቶ የቆመ አረመኔው የኢጣሊያ ፋሺስት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለእርሱ እንዳይገዛ ውጉዝ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መሬት እንዳትቀበለው የተገዘተች ትሁን፡፡” አቡነ ጴጥሮስ፡፡
ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን ጀግናው ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስ በግፍ የተገደሉበት ቀን ነው፡፡ እኒህ ታላቅ አባት ለሰማዕትነት ያበቃቸው ዋናው ምክንያት በወቅቱ ለተጠየቁት ቀላል ለሚመስል ጥያቄ “ቃሌን አልክድም” ብለው በመቆማቸው ነበር፡፡
በወልድያ ከተማ 3 ሰዎች ተገድለው ተገኙ
ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ወኪል ከስፍራው እንደዘገበው ሁለቱ ሰዎች በአንድ ቦታ ላይ ተገድለው ተጥለው ሲገኑ፣ አንደኛው የተገኘው በተለየ ስፍራ ነው።
የሀዘን መግለጫ፣ አንድነት ፓርቲ በቁርጥ ሰዓት ጀግናውን ኢትዮጵያ ልጅን በማጣቱ ታላቅ ሐዘን ተሰምቶታል
ፍኖተ ነፃነት
አቶ ግርማ ወ/ሰንበት በ1984 ዓ.ም. መዐህድን በመመስረት፣ ህይወታቸው እስካለፈበት ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ ደግሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) የብሄራዊ ም/ቤት አመራር አባል በመሆን ታግለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በፓርቲያችን አንድነት ከፍተኛ አመራር ሰጭ በመሆን ሌት ተቀን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የኢትዮጵያን ህዝብ የነፃነትና የዴሞክራሲ ጥያቄን ለማሳካት ግንባር ቀደም አርበኛ በመሆን ሲታገሉ የቆዩ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጅ ናቸው፡፡
Monday, July 29, 2013
የዘመኑ መንፈስ (በእውቀቱ ስዩም)
በእውቀቱ ስዩም
ባገራችን ባሁኑ ጊዜ ብዙ ተከታይ ያለው ሃይማኖት ብሄርተኝነት ይባላል፡፡የብሄርተኝነት ምእመን ከሆንክ የነፍስ አባት ይኖርሀል፣በጭፍን የምትቀበለው ቀኖና ይኖርሀል፣ነገ የምትገባባት የተስፋ ምድር ይኖርሀል፣ከሁሉ በላይ ደግሞ ብርቱ ችግርህን የምትደፈድፍበት የመስዋእት በግ ይኖርሀል፡፡
ሃይማኖቶች ምእመናንን ብቻ ሳይሆን መናፍቃንንም ያፈራሉ፡፡ብሄርተኞች በስሜት የሚነድደውን ምእመን ብቻ ሳይሆን የኔ ቢጤውን መነፍቅም እንደሚያፈሩ አንርሳ፡፡በነገራችን ላይ ሃይማኖትን መካድ ማለት ሃይማኖት የሚያነሳቸውን አብይ ጥያቄዎች መካድ ማለት አይደለም፡፡እንዲሁም፣ ብሄርተኝነትን መካድ ማለት የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች ህልውና መካድ ማለት አይደለም፡፡በዚህ ጉዳይ ፣መናፍቅ መሆን ማለት፣ የብሄርተኛ ነቢያት ሰለ ጭቆና ስለ ነጻነት ብሎም ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚያቀርቡትን አጉል እምነት መጠራጠር ማለት ነው፡፡
ከኢትዮጵያዊነት እንጀምር፡፡
ከዘመናችን የብሔርተኝነት ነቢያት አንዱ ጃዋር መሐመድ በቅርቡ ከእንቁ መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለመጠይቅ ላይ ስለኢትዮጵያዊነት የሚከተለውን ይላል፡፡
Sunday, July 28, 2013
! …. የህወሓት የድሮ ታጋይ ‘አሸባሪ’ ተባለ
….! Abraha Desta
ስዒድ አሕመድ ይባላል። የድሮ የህወሓት ታጋይ ነው። በትጥቅ ትግሉ ወቅት የትግራይ ህዝብ ለትግሉ በማነሳሳትና ትግሉ በመምራት ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ግንባር ቀደም ሚና ተጫውቷል።
የደርግ ስርዓት ከተገረሰሰ በኋላ እንደሌሎች ታጋዮች ከውትድርና ተቀንሶ በግል ስራ ተሰማርቶ ህይወቱ ሲመራ ቆየ። ባለፈው ሓሙስ (ሓምሌ 18) የፌደራል ፖሊሶች የትጥቅ መሳርያው እንዲያስረክብ ይጠይቁታል። ስዒድ ደግሞ አሁን ምንም ዓይነት መሳርያ እንደሌለውና የድሮ ትጥቁ ደግሞ ከዓስር ዓመት በፊት በሕጋዊ መንገድ ለመንግስት አካላት ማስረከቡ በማስረጃ ያስረዳል። ፖሊሶቹም ‘በሽብር ተጠርጥረሃል’ በሚል ሰበብ ዓፍነው ይወስዱታል።
Subscribe to:
Posts (Atom)