September 24, 2013
ኢህአዴግ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ (በውስጥም በውጪም ተግዳሮቶች) መገፋቱን በሚያመላክቱ የፖለቲካ አጀንዳዎች ላይ የሚያጠነጥን አንድ ፅሁፍ (‹የአብዮቱ የምፅዓት ቀን ምልክቶች›› በሚል ርዕስ) አቅርቤ እንደነበር ይታወሳል፤ ይዘቱም በመጪዎቹ ወራት ወይም ዓመት ስርዓቱ ‹ምርጫ› አሊያም ‹ህዝባዊ› እምቢተኝነት ከሚያመጣው ‹ማዕበል› (እንደበረከት ስምዖን አገላለፅ ‹ናዳን በሚገታ ሩጫ›) የማምለጥ ዕድሉ የጠበበ መሆኑን የሚያመላክት ነው፤ ይሁንና አንድ አብዮት ታላቅ (ውጤታማ) ሊባል የሚችለው አምባገነን ስርዓትን በመቀየሩ ብቻ ስላልሆነ (ሥር-ነቀል ለውጥ የሚፈጥር አብዮት ዋጋ የሚኖረው የዲሞክራሲ ተቋማትን መሰረት መጣል ሲችል ነውና) በቀጣይ መፃኢ ዕድሉ ላይ መነጋገሩ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
በዚህ ፅሁፍህ ተጠየቅም ‹ከስርዓቱ ለውጥ በኋላ፣ ማን ነው አማራጩ?› የሚለው ጥያቄ ትኩረት ይደረግበት ዘንድ አመላክታለሁ፡፡
ምክንያቱም በጠለፉ መንገድ ከቀሩ አብዮቶች ታሪክ ተምረን፣ ‹መጥነን ካልደቆስን› የሚከፈለውን ዋጋ በብላሽ የሚያስቀር አሳዛኝ ሁናቴ ሊፈጠር ይችላልና (ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን ‹‹አብዮት፣ ለአብዮት ብቻ ሲባል መካሄድ የለበትም›› እንዲል፣ ከኢህአዴግ መገላገሉ መልካም ቢሆንም፣ የአገላጋዩን ማቀፊያ ከወዲሁ መምረጡ ወይም የምንጠይቀውን ማወቁ ብልህነት ነው)

አማራጩ ተወልዷልን?
ከኢህአዴግ በኋላ የሚተካው አማራጭ ተዘጋጅቷል? …ይህንን ቀዳዳ አስቀድሞ መድፈኑን አስቸኳይ ያደረገው፣ ለውጡ የሚመጣበት መንገድ ‹ከህዝባዊ እምቢተኝነት› ይሆናል የሚለው ቅደመ-ግምት ነው፡፡ ከታዓማኒና በዕኩል አሳታፊ ምርጫ የሚነሳ ሽግግር (‹ሕዝብ የሚፈልገውን ያውቃልና ውሳኔው መከበር አለበት› ከሚለው የዲሞክራሲ ፅንሰ-ሃሳብ በመነሳት) አሳሳቢነቱ ከአደባባይ ተቃውሞ የሚመነጨውን ያህል አይደለም፤ ስለዚህም ከስጋት ነፃ መሆን የሚቻለው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መሰረታቸውን ሀገር ቤት አድርገው በህግ የተመዘገቡ የፖለቲካ ድርጅቶች የቤት ስራቸውን ሰርተው ዝግጁ ሆነው ሲጠብቁ ብቻ ነው፡፡ ይህ ግን የድርጅቶቹን ቁጥር ከሰማኒያ በላይ ከማሻቀብ ያለፈ አስተዋፅኦ የሌላቸውን አሰስ-ገሰስ ‹ፓርቲ›ዎች በሙሉ እንደሚመለከት ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡
ነፍስ ይማርና በ‹‹ልዕልና ጋዜጣ›› እልፍ አእላፍ ችግሮቹን ማረም ከቻለ መድረክ ተስፋ ሊጣልበት ይችላል ብዬ እንደማስብ መፃፌን አስታውሳለሁ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመድረክ አሰላለፍ ሊቀየር በማጋደሉ (ከአንድነት ጋ አብሮ መቀጠሉ ማጠራጠሩ) እና ሰማያዊ ፓርቲ አዎንታዊ እንቅስቃሴ ከማድረጉ አኳያ ተፎካካሪ ሊሆን የሚችልበት ዕድል በመፍጠሩ፣ በአጀንዳው ላይ ማካትቱን ተገቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ይሁንና ሌሎች ፓርቲዎችን እዚህ ጋ ያላነሳሁበት፣ ከላይ ከጠቀስኩት በተጨማሪ ሶስት ምክንያቶች አሉኝ፤ ቅቡልነትን ማጣት፣ እንቅስቃሴ አልባ መሆን እና በገዥው ፓርቲ ስፖንሰርነት መተንፈስ የሚሉ፡፡

መድረክ
የስድስት ፓርቲዎች ስብስብ ነው፤ በምርጫ ሁለት ሺህ ሁለት (ምንም እንኳ ከአንድ የምክር ቤት ወንበር በላይ ባይሳካለትም) ከሁሉም
ተቀናቃኞች በላይ ጐልቶ መውጣት ችሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የአምስተኛውን ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫም ተስፋ አድርጎ ለመጠበቁ
ማሳያዎቹ፡- አንድም ስብስቡ ዛሬም ህላዊ መሆኑ፣ ሁለትም ለበርካታ አባላቱና ደጋፊዎቹ ወደ ‹ግንባር ተሻጋገሩ› ግፊት ምላሽ መስጠት
መቻሉ ነው፡፡

በምስረታው ዋዜማና ማግስት ብዙ የተነገረለት መድረክ እርስ በእርሱ (በአንድ ጠርዝ-የአንድነት አመራሮች፤ በሌላኛው-ኦፌኮ እና
ኢሶዴፓ) የፈጠረው ውዝግብ በዙሪያው ለተሰለፉ አባላትና ደጋፊዎች ተስፋ አስቆራጭ ነው፡፡ ለግንባሩ ቅርብ የሆነ ወዳጄ የችግሩን
መጦዝ የገለፀው ‹‹ሁለቱ ጎራዎች በስብሰባ ወቅት ‹በውሃ ቀጠነ› ለፀብ ሲገባበዙ የሚያይ እና ለስድብ የሚጠቀሙባቸውን ቃላት የሚሰማ በአንድ ግንባር የተሰለፉ ናቸው ብሎ ከሚያምን ‹ግመል በመርፌ ቀዳዳ መሽሎኩን› ቢቀበል ይቀለዋል›› በሚል ምፀት ነው፡፡ አደጋውን የከፋ የሚያደርገው ደግሞ ኩነቶቹ ከመለዘብ ይልቅ መባባሳቸው ይመስለኛል፡፡

በመሬት ያለው እውነታ ይህ ቢሆንም፣ ፓርቲው በ2005 ዓ.ም ወርሃ መጋቢት ወደ ‹ግንባር› መሻገሩን ከማብሰሩም በላይ፣
‹‹የኢትዮጵያን ወቅታዊና መሰረታዊ ችግሮች የመፍቻ አጋጣሚዎች›› በሚል ርዕስ ይፋ ባደረገው ባለአራት ገፅ ‹ማኔፌስቶ›፣ የሀገሪቱን
ችግር በሙሉ በአራት ክፍል ቀንብቦ ካስቀመጠ በኋላ፣ ጉዳዩን ፈረንጅኛው ‹የሲኒ ማዕበል› እንደሚለው አድርጎ በማለፍ የ‹ደግፉኝ›
ጥሪውን እንዲህ ሲል አስተላልፏል፡-‹‹ይህንን ፀረ-ህዝብና ፀረ-ሀገር የሆነውን ኢህአዴጋዊ ስርዓት በሰላማዊ አግባብ በምታደርገው ብርቱ ትግልህ መለወጥ እንደምትችል ካለፈው የትግል ተሞክሮህ ሆነ የአለም ህዝቦች ለነፃነት፣ ለዕኩልነትና ለፍትህ ብሎም ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን መሆን ከሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎችና ከሚያስመዘግቧቸውም ድሎች ትገነዘባለህ፡፡ ስለሆነም መድረክ ይህንን ክቡር ትግልህን በመምራት ባለቤትነት እንድትበቃ በፅናትህ ከጎንህ ሆኖ ለመታገለ መወሰኑን ተገንዝበህ ከምንጊዜም በላይ ሁለንተናዊ ድጋፍህን እንድትሰጥ ጥሪያችንን በከፍተኛ አክብሮትና በአንተም ላይ ባለን ሙሉ እምነት እናስተላልፋለን፡፡››በግሌ መድረክ ራሱ በሁለት ምክንያቶች እምነት ሊጣልበት የሚችል አልመስለኝም፡፡

የመጀመሪያው ከአንድነት ጋር የገባበት ድምፅ የለሽ ውዝግብ ከዕለት ወደ እለት እያደገ መሄዱ ነው፤ አዲሱ የዶክተር መረራ ጉዲና መጽሐፍም ቅራኔውን ቢያሳፋው አይገርምም፤ ዶ/ሩ ስለ2002ቱ ምርጫ ባወሳበት ምዕራፍ ‹‹የ1997ቱ የቅንጅት ወራሽ ነው ብለን የተማመንበት አንድነት እውነተኛ ወራሽ ለመሆን በጣም ብዙ እንደሚቀረው ተረዳው›› ያለበት ግምገማ እና ‹‹ያልገባኝና የሚከነክነኝ አንድነት ኦሮሚያ ላይ በብዛት ያወዳደራቸው ኦህዴድ ያሰማራቸው ወሮበሎች ነበሩ›› ፍረጃው ‹ትችት›ን በቅንነት ለመቀበል ልምድ ከሌለው የሀገሪቱ ፖለቲካ አንጻር አቧራ ማስነሳቱ አይቀሬ ለመሆኑ መገመቱ አይከብድም፡፡ ይህ እንግዲህ አንድነትን የአማራ (የከተማ ልሂቃን) ተወካይ የሚያደረገውን ወቀሳ ሳይጨመር ነው (እዚህ ጋ የሚነሳው አስቂኙ ጉዳይ ወቀሳውን የሚሰነዝሩት አባል ፓርቲዎች አንድነት የብሔር ድርጅት ቢሆን ይበልጥ ተጠቃሚ ከመሆናቸው በተጨማሪ ለአብዛኛው ችግሮቻቸው በቀላሉ መፍትሄ የመስጠቱ ጉዳይ ሲታሰብ ነው) ሁለተኛው መድረኩ ከለውጡ በኋላ ሀገር ለመምራት የሚያስችል የጠራ የፖለቲካ አመለካከት አለመከተሉ ነው፤ በውስጡ ያሉ ፓርቲዎች ቢያንስ ሁለት የተለያዩ ፕሮግራም የሚያራምዱ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
የአንድነትን እና የኦፌኮን ፕሮግራም ብንወስድ
የችግሩን ግዝፈት ያሳየናል፤ አንድነት መልካ ምድር ላይ ስለተመሰረተ ፌደራሊዝም አስተዳደር ጠቀሜታ ሲያብራራ፤ የኦፌኮ ባለስድስት ገፅ
ፕሮግራም ደግሞ በማንነት ላይ ስለተመሰረተ ፌደራሊዝም ይሰብካል፡፡ በግልባጩ ውድሀት ይፈፅሙ እንዳይባል ደግሞ የእነ ዶ/ር መረራ
‹ከተዋህድን ኦሮሞ ተውጦ ይጠፋል› ስጋት ጋሬጣ ነው፡፡ አንዳንድ የአመራር አባላቱ ‹‹ዓላማችን ቅድሚያ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን
መገንባት ነው›› የሚል መከራከሪያ ሲያቀርቡ ቢደመጡም፣ ከዚህ በኩል ከሚነሳው ተግዳሮት በቀላሉ የሚመለጥ አይመስለኝም
(በነገራችን ላይ መድረኩ በወቅታዊው ቁመና ‹ግንባር› ለመመስረት የሚያስችለውን መስፈርት ሟሟላቱ ራሱ አጠራጣሪ ነው)

አንድነት
የአንድነት ተግዳሮት ወደ መድረክ ከመግባት ጋ ተያይዞ የመጣ ነው (ከጠዋቱ ሰማያዊ ፓርቲን የመሰረቱት ወጣቶች ከድርጅቱ
ለመውጣት አንዱ ምክንያታቸው ይህ እንደሆነ ይታወሳል)፤ ትብብሩን ‹ያልተባረከ ጋብቻ› የሚያስብለው ደግሞ የዛሬ አራት ዓመት ‹ወደ
መድረክ ካልገባን ትግሉን እናደናቅፋለን› ሲሉ የነበሩ አንዳንድ የአንድነት አመራሮች የውዝግቡ ተሳፊ መሆናቸውን ስንመለከት ነው፤
መተነኳኮሱ በ2002ቱ ምርጫ ማግስት የተጀመረ ቢሆንም፣ ባለፈው ዓመት ወደ መጦዝ ተሸጋግሯል፡፡ በተለይም አንድነት ‹‹የሚሊዮኖች
ድምፅ ንቅናቄ›› በሚል መርህ ያካሄደው የሶስት ወር ዘመቻ መድረክን አለማካተቱ የሚያስተላልፈው መልዕክት ግልፅ ነው፡፡ በ‹‹ፀረ-
ሽብር›› አዋጁ ላይ (ኢህአዴግንና ኢዴፓን ጨምሮ) በተደረገው ክርክርም አንድነት እና መድረክ በተለያዩ ሰዎች ተወክለው መቅረባቸው
ግንኙነቱን እንደ ቀድሞ ለማየት አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡

ይህም ሆኖ አንድነት በራሱ የተሻለ ፓርቲ ሆኖ ሊወጣ የሚችልበት ዕድል አለው፡፡ ምሁራዊ ስብስቡም ሆነ የኢኮኖሚ አቅሙ
(የዲያስፖራ ድጋፉ) አንፃራዊ ጥንካሬ እንዲያገኝ ረድቶታል፤ ርዕዮተ-ዓለሙንም ከተቀናቃኝ ፓርቲዎች በጠበቀ መልኩ ማዘጋጀቱ
ለቅቡልነቱ አስተዋፅኦ ሊያደርግለት ይችላል፤ ከመኢአድ ጋር የጀመረውን ውህደት (‹የአማራ ተወካይ› የሚለውን ፍረጃ ቢያጠናክረውም)
ከዳር ካደረሰ ደግሞ ከአቻዎቹ ጋ ያለው ልዩነት በእጅጉ መስፋቱ አይቀሬ ነው (መኢአድ የፈራረሰው ከአናት ነውና ግዙፍ መዋቅሩ ‹እረኛ አልባ› በመሆኑ፣ አንድነት በውህደት ስም ቢሰበስበው በከፍተኛ ደረጃ ይጠቅመዋል)

የወል-መንገድ
በቀጣይ የተሻለ አማራጭ ሆኖ ለመገኘት መድረክና አንድነት መቻቻላቸው ወሳኝ ነው፡፡ ይሁንና ኩነቱን በታዛቢነት መመልከት
የመረጡት የአረና ሰዎቸ በግንባሩ ቢሮ ሰላም ለማውረድ የአስታራቂነት ሚና ቢጫወቱ ጠቃሚነቱ ለእነርሱም ነው፡፡ አንድነቶችም፣
በመድረክ ስም እዚህ ድረስ ለመጓዝ የከፈሉት ዋጋ ብላሽ ከሆነ ማንንም አያተርፍም፡፡ በአናቱም ወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ አስገዳጅ
መሆኑ መረሳት የለበትም፡፡ ምክንያቱም አንድነት የሰበሰባቸው ልሂቃኖችም ሆኑ በሀገሪቱ የተለያዩ ከተሞች ያነበረው መዋቅር (ጥንካሬው
ላይ ያለኝ ጥርጣሬ እንደተጠበቀ ሆኖ) ቅድሚያ ለብሔር ፖለቲካ ከሚሰጡ አካባቢዎች በ‹መድረክ ባርኔጣ› በሚገኝ ድጋፍ (ድምፅ)
ካልታገዘ በቀር አየር ላይ ተንጠልጥሎ ከመቅረት አይታደገውም፡፡

የመድረክ ተግዳሮትም ተመሳሳይ ነው፤ በፖለቲካው ላይ ውጤት የሚያዛባ ተፅዕኖ ማሳረፍ የሚቻላቸውንና አንድነት የራሱ
ያደረጋቸውን ከተሜዎች ‹ቡራኬ› ሳይቀበል ወደ ውድድር መግባቱ ‹ውሃ በወንፊት…› አይነት ሊሆንበት ይችላል፡፡ የመድረክንና
የአንድነትን የወል ቀዳዳ መዘርዘሩን እዚሁ ገትቼ፣ የተሻለ ጥንካሬና የመግባባት መንፈስ ለማስረፅ በቅድሚያ የችግሮቻቸውን መንስኤ
ለይተው ማወቅ አለባቸው ብዬ ስለማስብ፣ በግሌ ‹ያለመግባባቱ መነሻ› ከምላቸው ዋና ጉዳዮች ሶስቱን በአዲስ መስመር እጠቅሳለሁ፡፡

፩- የፕሮግራም መጋጨት ያመጣው ጣጣ አንዱ ነው፤ ይኸውም የፀቡ የቡድን አባቶች የ‹ሕብረ ብሔር› እና የ‹ክልል› ፖለቲካ አቀንቃኝነት፣ ሁሉም አባል ፓርቲዎች መድረኩን ሲፈጥሩ የየራሳቸውን ፕሮግራም እንደያዙ መሆኑ፣ ጥቂት የማይባሉ ልዩነታቸውን ሳይፈቱ ‹በይደር› ማስቀመጣቸው… እንደ ማሳያ ይጠቀሳሉ፡፡ ይህ ሁኔታም የእርስ በእርስ መተማማን እንዳይኖራቸው ያደረገ ይመስለኛል(ከዚህ አኳያም ለመፍትሄው ቅድሚያ ከልሰጡ በመድረክ በኩል ‹መጪው ጊዜ ብሩህ ይሆናል› ብሎ መጠበቅ ‹የዋህ› ሊያስብል ይችላል) የጫናው ተፅእኖ ደግሞ በሁለቱም በኩል (በአንድነትና በብሄር ድርጅቶቹ) ከሚከተሉት የፖለቲካ አመለካከት አንፃር ወደ ስልጣን የመምጣቱ አጋጣሚ ቢፈጠር፣ የታገሉለትን ስርዓት ማንበሩ ፍፁም አዳጋች መሆኑን በማስታወስ ነው፤ አንድነቶች ፓርቲያቸው ከመድረክ እንዲወጣ ይጎተጉታሉ፤ ብሔር ተኮሮቹ ደግሞ ‹አንድነት የነፍጠኛውን ስርዓት የሚመለስ በመሆኑ፣ ወይ ወደ ብሄር ድርጅት ራሱን ይቀየር፣ አሊያም ፕሮግራሙን ይከልስ› የሚለው ሙግታቸው በአሳማኝ ሁኔታ መፍትሄ አለማግኘቱ ራሱን የቻለ ሌላ ትግል ከሚፈልግ አጀንዳ ጋ አላትሟቸዋል፡፡
፪-አንድነት በሚያራምደው የሊብራል ዲሞክራሲ እና አብዛኛው የመድረክ አባል ድርጅቶች በሚከተሉት የሶሻል ዲሞክራሲ መካከል ያለውን ልዩነት የማሰታረቅ ስራ አለመሰራቱ ነው፡፡ ‹‹የአንድነት ፓርቲ ስትራቴጂና የአምስት ዓመት ዕቅድ›› በሚል ርዕስ 246 ገፅ ይዞ በታተመው መፅሀፍ ላይ ‹‹አንድነት የሚመሰረትበት ርዕዮተ-ዓለም ሊበራሊዝም ሆኖ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች የሶሻል ዲሞክራሲን ጠቃሚ ገፅታዎች ይወስዳል›› የሚለው አንቀፅ ቢጤን ለመልካም ግንኙነት መደላድል መሆን ይችላል (በነገራችን ላይ‹እንዲህ የችግር ቋት ተሸክመው ስለምን በጋራ ለመስራት ተስማሙ?› የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርምና ግምቴን ላስቀምጥ፤ የብሔር ድርጅቶቹን እስትንፋስ የሚቆጣጠሩት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ እና ዶ/ር መረራ ጉዲና ምርጫ 97ን ከሁለት አቅጣጫ ገምግመው ከደረሱበት ድምዳሜ ጋ የሚያያዝ ይመስለኛል፤ ይኸውም ‹አንድነት፣ የቅንጅት ወራሽ ነው› የሚለው የተሳሳተው ትንተና አንዱ ሲሆን፣ ሁለተኛው በዛው ምርጫ ተቀማጭነታቸው አውሮፓና አሜሪካ ከሆኑ አስራ ሁለት ፓርቲዎች ጋር መስርተውት የነበረው ‹‹ህብረት››፣ ፓርላማ በመግባታቸው፣ ከውግዘት ጋር እንዲባረሩ በማድረጉ ያሳደረባቸው መገለል ሊሆን ይችላል፤ በአንድነት በኩል ደግሞ ‹የመድረኩ መሀንዲስ› ተደርገው የተወሰዱት ዶ/ር ነጋሶና አቶ ስዬ አብርሃ አንድነትን ለመቀላቀል ወደ መድረክ መግባትን እንደ መደራደሪያ በማቅረባቸው ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ ዛሬም ያልተሸነፈው የ‹ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ› ግልብ ግፊት ነው ብዬ አስባለሁ፤ የዚህ ድምር ውጤትም ከነርዕዮተ-ዓለም እና የፕሮግራም ልዩነት ወደ መድረኩ አምጥቷቸው አይን የሚገባ ሥራ እንዳይሰሩ አግዷቸዋል)
፫-የመድረክ አባል ድርጅቶች መተዳደሪያ ደንብን አለማክበር ‹የፖለቲካ ብልጠት› በማድረጋቸው፣ ለራሳቸው ተጨማሪ የመናተረኪያአጀንዳ ፈጥረዋል፡፡ ይህ አይነቱ ስርዓት አልበኝነት በጋራም በተናጥልም ተፈፅሟል፡፡ አንድነትን ጨምሮ የመድረኩ ስራ አስፈፃሚ ደጋግሞከመርሁ ሲያፈነግጥ ታይቷል፤ ለምሳሌ በደንቡ ላይ መሻሻል ያለበትን አንቀፅ የሚወስነውም ሆነ ከፍተኛው ስልጣን የጠቅላላ ጉባዔውመሆኑ በግልፅ ተቀምጦ ሳለ፣ ጉባዔው ከተሰበሰበባቸው በአንዱ ዕለት ‹የመድረኩ ሊቀ-መንበረ በዙር ከሚሆን፣ በብቃት ይሁን›፤እንዲሁም ‹አዲስ ፓርቲ በአባልነት የምንቀበልበት መንገድ መሻሻል አለበት› የሚሉ አቋሞች ላይ ቢደርስም፣ ስራ አስፈፃሚው ቃል በቃል‹ይህንን አሰራር ጉባኤው ሊቀይረው አይችልም› ሲል ውድቅ ያደረገበትን አጋጣሚ መጥቀስ ይቻላል፡፡
በተናጥል አንድነት፣ ኦፌኮ እና ኢሶዴፓ በአንቀፅ 21 ‹የአባል ድርጅቶች ግዴታ› በሚል ርዕስ ስር የተቀመጡትን፡- ‹ከአፍራሽና
ተቃራኒ ከሆኑ እንቅስቃሴዎች መቆጠብ›፣ ‹በአባላት መካከል አለመተማመን ከሚፈጥሩ ማናቸውም ተግባር መቆጠብ›፣ ‹የግንባሩን አቋም
የሚፃረር አቋም ያለማራመድ› እና መሰል ደንቦችን ደጋግመው በአደባባይ ሲጥሱ ታይተዋል፤ ይህ አይነቱ ስርዓተ-አልበኝነት መፍትሄ
ሳያገኝ የተሻለና ጠንካራ ሆኖ መውጣቱ አዳጋች ይመስለኛል፡፡

ሰማያዊ
ሰማያዊ ፓርቲ አዲስ በመሆኑ ለወቀሳ መቸኮሉ አግባብ እንዳልሆነ ቢሰማኝም፣ ፓርቲው እያሳየ ካለው ፈጣን እንቅስቃሴ አኳያ፣
በፍጥነቶቹ መካከል የሚፈጥራቸውን ድክመቶቹን ቢያሻሽል ጠቀሜታው ለሀገር ስለሆነ የግል አስታየየት መስጠቱን አስፈላጊ ሆኖ
አግኝቸዋለሁ፡፡የሰማያዊ ዋናው ድክመት ከ‹ግንፍሌ ፓርቲ›ነት አልፎ የመሄድ ፍላጎት ያለው አለመምሰሉ ነው (ጽ/ቤቱ አራት ኪሎ /ግንፍሌ/ አካባቢ ይገኛል)፡፡

ከአዲስ አበባ ውጪ ለመንቀሳቀስ ሲሞክር አይታይም፤ በሌሎቸ የሀገሪቱ ከተሞች የተከፈተ ተጨማሪ ቢሮ ካለ፣ ከምስረታው
በኋላ የአባላቱ ቁጥር ምን ያህል እንደደረሰ፣ እና መሰል መረጃዎችን ለማግኘት ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት ሄዶ የነበረው የመፅሄቱ ሪፖርተር
‹እንዴት እንደምትጠቀሙበት ስለማናውቅ አንናገርም› በሚል ክልከላ በመመለሱ ስለወቅታዊው ቁመና እዚህ ጋ መጥቀስ አልተቻለም
(ከዚህ ውጪ ሊቀ-መንበሩ ይልቃል ጌትነት ከ‹ሰንደቅ› ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ-መጠይቅ ‹‹ባለፉት 40 ዓመታት ከመጣው የፓርቲዎች ጥንካሬ ይልቅ፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ሰማያዊ ፓርቲ ብቻውን አምጥጦታል›› ያለው ሀረግ ስህተት ቢሆንም፣ አንድም በሂደት የሚታረም፣ሁለትም የአፍ ወለምታ፣ ሶስትም ከልምድ ማነስ የሚያጋጥም በመሆኑ ‹ፀጉር መንጨቱ› ፓርቲው ፍርሃትን ለመስበር ከሚያደርገው እንቅስቃሴ አኳያ ገንቢ አይደለምና አልፈዋለሁ፡፡)

‹እምነት ጨምሩልን›
‹ለውጥ! ለውጥ!› የሚል ድምፅ በመላ ሀገሪቱ የበረከተው የ‹ቡርዣ› ወይም ‹አድሀሪ› አብዮትን በመናፈቅ አይደለም፤ እንዲህ አይነት
አብዮት፣ ከሰው ለውጥ በቀር ሕዝባዊ ጠቀሜታ የለውማና፡፡ የደርግም ሆነ የኢህአዴግ ‹አብዮት› የዚህ አምሳያ በመሆኑ ነው፣ ዛሬም
ዘመን ተጋሪዎቼ ‹ፋኖ ተሰማራ!› ከማለት ነፃ ያልወጡት፡፡ ‹ሶስተኛው አብዮት› የማይሸነፍ እና የማይንበረከክ እንዲሆንልን ከምንመኘው
በላይ ወደ ‹መፈንቅለ-መንግስት›ነት እንዳይቀየር መጠንቀቁንም ግዴታ ያደረገው ጠንካራ ፓርቲና የነቃ ማህበረሰብ ያለመኖሩ ስጋት ነው፡
፡ ይህ ደግሞ ከወዲሁ ከአማራጩ ኃይል ጎን መቆም ይቻል ዘንድ ‹እምነት ጨምሩልን!› (ሀገር የመረከብ አቅማቸውን አሳዩን?) እንድንል አስገድዷል (‹ጀግናው› ኢህአዴግ ወደ ማይቀረው ሽንፈት መንገዱን ከጀመረ ጥቂት ክረምቶች በማለፋቸው፣ ከለውጡ በኋላ የሚመጣው ኃይል ሁለንታው የተቃና መሆኑን ማስመስከር አለበት)መድረክ፣ አንድነት እና ሰማያዊ ወደራሳቸው ይመለከቱ ዘንድ ከሞላ ጎደል የወል ‹ክፍተቶች› ወይም ‹ድክመቶች› የምላቸውን ሶስት ጉዳዮች ከዚህ ቀጥሎ እጠቅሳለሁ፡፡

ሃሳብ-አልባ
ፓርቲዎቹ በምስረታቸው ዘመን ቅድሚያ የሚሰጡት ለምርጫ ቦርድ የእውቅና ሰርተፍኬት እና ‹ተቃዋሚ ድርጅት› ተብለው
ለመጠራት በመሆኑ አንድም የሀገሪቱን አንኳር ችግሮች አጥንተው መፍትሄ በመያዝ አልተዘጋጁም፤ ሁለትም ከነባር ድርጅቶች ድክመትና
ጥንካሬ ተምረው አልመጡም፤ በዚህም የሚፈልጉትን ሳያወቁ እና የተለየ አማራጭ ሳይይዙ ወደ ፖለቲካው ገብተዋል ወደሚል ጠርዝ
እየገፋን ነው፤ ጠንካራና የተፍታታ የፖለቲካ ፕሮግራም የላቸውም፤ በንፅፅር ‹‹አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ›› የተሻለ ፕሮግራም
ለመቅረፅ ከመሞከሩ ውጪ፣ የመንግስቱ ስልጣን ‹ገጭ-ቋ› ቢል ‹አማራጭ ሊሆኑ ይችላሉ› የሚባሉት ፓርቲዎች ‹እያሾፉ ነው› በሚል
ችላ ካልተባሉ በቀር ‹ፕሮግራሜ› ብለው ያቀረቡትን ለተመለከተ ምን ያህል ሃሳብ አልባ እንደሆኑ ለመረዳት አይቸገርም፡፡

የሆነው ሆኖ ይህንን ፅሁፍ ሳዘጋጅ የነበረኝ አመለካከት ስለመድረክና አንድነት የፖለቲካ ፕሮግራም ደካማነት ከዚህ ቀደም ስለጠቀስኩ፣
ዛሬ ሰማያዊ ፓርቲን ብቻ አንስተን ብንነጋገር ይሻላል የሚል ነበር፤ ይሁንና የድርጅቱን ፕሮግራም ካነበብኩ በኋላ ግን ምንም ማውራት
እንደማይቻል ተረዳው (ያውም ያየሁት ወረቀት ‹ፕሮግራም› ተብሎ ሊጠራ ከቻለ ማለት ነው)፡፡ ፓርቲው ለስልጣን የመብቃት ዕድል
ካገኘ፣ ለዘመናት ሲንከባለልና ሲደራረብ የመጣውን ዘርፈ ብዙ የሀገሪቷን ችግር የሚፈታው ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ፕሮግራም›› በማለት ርዕስ
ባዘጋጀው ባለአስራ አምስት ገፅ ወረቀት ነው፡፡ መቼም በዚህ ፕሮግራም ‹ከሌሎች የተሻልኩ ነኝ-ምረጡኝ› የማለቱ ድፍረት ግራ አጋቢ
ይመስለኛል፤ ምናልባት ‹የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ዶ/ር መረራ ጉዲና ካዘጋጀው አራት ገፅ ፕሮግራም፣ የእኛ የበለጠ ነው› የሚል
መከራከሪያ ካልቀረበ፡፡

ስለርዕዮተ-ዓለሙም ቢሆን ‹ለዘብተኛ ሌብራሊዝም› ከማለት ያለፈ ያብራራልን ጉዳይ የለም (በዚህ በኩል ኢዴፓ ከሁሉም በተሻለ የተብራራና የጠበቀ ፕሮግራም አለው፤ ግና! ለአንድ ፓርቲ ከምንም በላይ አስፈላጊ የሆነውን ‹ታአማኒነት› አፍርሷልና ፕሮግራሙ ጠቀመ አልጠቀመ ፋይዳ አለው ማለት አይቻልም) በተቀረ ያለ ርዕዮተ-ዓለም ፓርቲ መስርቶ፣ ‹ሀገሬን፣ ሀገሬን…› ማለቱን
ከቀረርቶ ለይቶ መረዳት ይቸግራል፡፡ መድረክ፣ አንድነት እና ሰማያዊ አሁንም ጊዜውም ዕድሉም አላቸውና ስልጣን ቢይዙ በዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች፣ በፖሊሲዎች፣ በማህበራዊ ፍትህ እና መሰል ጉዳዮች ላይ ያላችውን የመፍትሄ ሃሳብ እና የተሻለ አማራጭ በትክክል ተንትነው ማዘጋጀቱን ቢያስቀድሙ መልካም ይመስለኛል፡፡

ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ በ1997 ዓ.ም ‹‹የምርጫ ማኒፌስቶ›› ብሎ ያዘጋጀው ሰነድ እንኳ ከ130 ገፅ በላይ የፈጀ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ እናም ፓርቲዎቹ ‹ፕሮግራሜ› የሚሉትንም ሆነ፣ ከተራራ የገዘፈ ችግሮቻችንን በደቃቃ ግምገማ ለማብራራት መዳከሩን አርቀው በመስቀል ወደ ቁም-ነገሩ ቢያዘንብሉ ጠቀሜታው ለራሳቸው ነው፤ ‹የትም ፍጪው…› መረሳት አለበት፤ ለፖለቲካ ፓርቲ ሃሳብ ከምንም በላይ ወሳኝ ነው፡፡ ዳሩስ! በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የተዘጋጀ ፓርቲ፣ የሚሸጥ ርዕዮተ-ዓለም ካላዘጋጀ በቀር ወታደራዊ ድርጅት አይደለምና ‹በኃይል ተጠቅሜ ፍላጎቴን አሳካለሁ› ሊል አይችልም፡፡ እውነት እውነት እላችኋለውም በዚህ በኩል ቀድሞ የነቃ፣ እርሱ አትራፊ ነው፤ ረቢው እንዳለውም ‹ላለው ይጨመርለታል›ና፡፡
ምሁር አልባ
የተፎካካሪ ድርጅቶች ሌላኛው ክፍተት ምሁራንን /ሙያተኞችን/ አለማቀፍ እንደሆነ ተደጋግሞ ቢነገርም፣ ዛሬም በዚህ በኩል የተሰራ
ሥራ የለም፡፡ ይህንን ቀዳዳ ለመድፈን አመራሩና አባለቱ ከጽ/ቤት በመውጣት መቀስቀስ፣ ማሳመን፣ ማግባባት… አለባቸው ብዬ
አስባለሁ፤ መቼም በሁሉም ዘርፍ ‹እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው› ግብዝነትን የወረሱት ነፍሱን ይማረውና ከአቶ መለስ ይመስለኛል፤ ይህ
አይነቱ አመለካከት ግን ወንዝ አያሻግርም፡፡ በርግጥ ‹ፖለቲካና ኮረንቲ…› በሚባልበት አገር፣ በደፍረት፣ ድርጅት እስከመመስረት መድረስ
ትልቅ ታሪክ ቢሆንም፣ ጠንካራ መሆን ካልተቻለ ዞሮ ዞሮ ያው ክሽፈት ነው፡፡ አደባባዩም እንደቀድሞ ‹ድንጋይ ዳቦ ነው› ብለው
ለሚከራከሩ አፈ-ጮማ ፖለቲከኞች ቦታ የሌለው መሆኑ ግልፅ ይመስለኛል፡፡ በተለያየ ሙያ የሰለጠኑ ምሁራኖችን ወደ ፓርቲያችሁ
ለመሳብ መደላደሉን አመቻቹ፤ ፍርሃት መሰበር እንዳለበት አሳምኗቸው፤ አንኳኩ፤ ከልከፈቱም ደጋግሙት፡፡

የሴራ ፖለቲካ
ሌላው ድርጅቶቹ የሚጠነክሩት፡- ከሴራ፣ ከስርቻ ስር ፖለቲካ፣ ከጠልፎ መጣል ጨዋታ፣ ከአፍቅሮተ-ስልጣን አና ከመሳሰሉት ነፃ
ሲሆኑ ነው፡፡ በአናቱም የጥናትና ምርምር ዘርፍ መሰል እያቋቋሙ እውቀትና መረጃን ወደላይም ወደታችም በማሰራጨት አመራሩንና
አባላትን ማብቃት፣ እንዲሁም ግልፅነትን በመተግበር፣ የ‹ጀርባ ፖለቲካ›ን ማዳካም ይቻላል፡፡ ይህ ሲሆን ነው ኩነቶችን ከመበለጥና
ያለመበለጥ፤ ከመሸነፍና ያለመሸነፍ አኳያ ብቻ የማየቱ አባዜ የሚለወጠው፡፡ ከእዚህ ሁሉ ስንክሳር በላይ ደግሞ በምሬቷ ብዛት
በአማራጩ ኃይል ላይ ተስፋ የጣለች ሀገር መኖሯም ከእያንዳንዷ እንቅስቃሴ ጋ መታወስ ይኖርበታል፡፡

በመጨረሻም-የአልባራዲ መንገድ
ሀገሪቱ ካለችበት ወሳኝና ታሪካው ወቅት አኳያ ቢያንስ በመንግስት ጥቁር መዝገብ ስማቸው ያልሰፈረ፣ እውቀትና አቅም ያላቸው፣
በየትኛውም ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው መንገድ ወደ ሀገራቸው ገብተው ትግሉን ማገዝ የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁናቴ
የሚያስገድደው ነው፡፡ በተለይም በእንዲህ አይነት ጉዳዮች ከትምህርትም ሆነ ከመስክ ልምድ ያካበቱ ወንድምና እህቶች የግብፃዊውን
መሀመድ አልባራዲ መንገድ ቢከተሉ፣ አንድም ሁኔታዎች ከቁጥጥር እንዳይወጡ ማገዝ ይችላሉ፤ ሁለትም አብዮቱን ከሽንፈትና ቅልበሳ
ይታደጋሉ፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ
No comments:
Post a Comment