Monday, September 30, 2013

“ፕሬዚዳንት እንድሆን ብጠየቅ በቅድሚያ ምን ያህል ላገለግል እችላለሁ እላለሁ – ወ/ሮ ሰሎሜ ታደሰ


የቀድሞዋ የመንግስት ቃል አቀባይ ወ/ሮ ሰሎሜ ታደሰ ሃገር ቤት ከሚታተመው ሎሚ መጽሔት ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች። የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ግንዛቤ ይረዳቸው ዘንድ ቃለ ምልልሱን እንደወረደ አስተናገድነው…

ሁሉ ነገር ራዕይ ሆኖ ይቀጥላል እንዲባል አልፈልግም
በሥልጣን የሚመጣ ክብር ደግሞ ከሥልጣን ጋር አብሮ ይቀራል

ሎሚ፡- አምባሣደር ዮዲት እምሩ በሕይወትሽ ከፍተኛ መነቃቃት እንደፈጠሩብሽ ይሰማል፤ እንዴትና ለምን?
ወ/ሮ ሰሎሜ፡- እሳቸው ከፈጠሩብኝ መነሣሣትና መነሳሳት ይልቅ አባቴ እሳቸውን ምሣሌ በማድረግ ውስጤ የፈጠረው መነሣሣት ነው የሚበልጠው፡፡ ልጅ እያለሁ እሣቸው አምባሣደር ነበሩና በቴሌቪዥን በተደጋጋሚ ይታዩ ነበር፡፡ የዛን ጊዜ እኔ አራተኛ ክፍል ነበርኩ፡፡ ሁልጊዜም በቴሌቪዥን ሲመጡ አባቴ ይጠራኝና “…በቃ አንቺ ስታድጊ እሣቸው ስራ የላቸውም” ይለኝ ነበር፡፡ የእሱ አባባል ስታድጊ ስራቸውን ትወስጅባቺዋለሽ ዓይነት ነበር፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ይህንን የማፊያ ቡድን በማፍረስ ታሪክ ይስሩ! በግርማ ሠይፉ ማሩ



ግርማ ሠይፉ ማሩ
በ2005 ዓ.ም የምክር ቤት ዘመን መጨረሻ ላይ የደህንነት መስሪያ ቤቱን በሚኒስትር ደረጃ ለማዋቀር የሚረዳ አንድ አዋጅ ለምክር ቤት ቀርቦ ፀድቆዋል፡፡ ይህ አዋጅ ሲፀድቅ ከነቅሬታዬ ያለኝ ድጋፍ መስጠቴ ይታወቃል፣ ለዚህ አዋጅ ድጋፍ መስጠት የፈለኩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከበረሃ ይዘውት የመጡት ልዩ ልዩ አፋኝ ቡድን ስለማይኖራቸው እንዲሁም ቀደም ሲል የነበሩትን አፋኝ ቡድንች ወደ አንድ መዋቅር በማጠቃለል ተጠሪነቱ ከተለያዩ መዋቅሮችና ግለሰቦች ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ (ወደ ተገቢው ማለት ነው) ቁጥጥር በማስገባት ለዜጎች ስጋት ሳይሆን ለዜጎች እና ለሀገር ደህንነት የሚስራ ተቋም ይሆናል በሚል ተስፋ ነው፡፡ ይህ ተስፋዬም ዝም ብሎ ሳይሆን በአዋጁ አንቀፅ 3 “ይህ አዋጅ በመላው ሀገሪቱ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ በፌዴራልም ሆነ በክልል መንግስታት ደረጃ ሌላ የመረጃና ደህንነት ተቋም  ማቋቋም አይቻልም” የሚል ድንጋጌ በመያዙ ነው፡፡ በመስከረም 19 እሁድ ዕለት አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ “በሰላም” ከተጠናቀቀ በኋላ እጅግ አሰገራሚ የሆነ ተግባር አጋጥሞናል፡፡

Sunday, September 29, 2013

ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ለኢትዮጵያውያን፣ ለአባሎቹ እና ለደጋፊዎቹ ያስተላለፈው የምስጋና መልእክት















ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን እንደ ወያኔ ዘመን የተዋረዱበት የተናቁበትና የተበደሉበት ጊዜ የለም። በአሁኑ ወቅት አገሪቱና ህዝቧ ከፊታቸው የተጋረጠው ችግር የመሰረታዊ የዲሞክራሲና የሰብኣዊ መብቶች አለመከበር ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የሕልውና ጥያቄና ኢትዮጵያ እንደ አገር የመቀጠልና ያለመቀጠል ጉዳይ ሆኖዋል። በመሆኑም ዛሬ የነጻነት ታጋዮች ህይወታቸውን በመሰዋት አገራችንን እንደ አገር ለማስቀጠል እና ህዝቧን ነጻ ለማውጣት ቆርጠው ተነስተዋል። 

ሰላማዊ ሰልፉ ቢታገትም ፣ የተሳካ ሕዝባዊ ንቅናቄ ነበር! – ከአንድነት ፓርቲና ከ 33ቱ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ


603944_622133674503606_213601633_n አንድነት ፓርቲ ከ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብ ጋር በመሆን ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ ያቀዱት ሰላማዊ ሰልፍ በገዢው ፓርቲ (መንግስት) ክልከላ ሠልፉ ሊደረግበት ወደነበረው መስቀል አደባባይም ሆነ በአማራጭ ነት ያቀረቡት 9 አደባባዮች እንዳይንቀሳቀስ ተደርጎ ከአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት እስከ ቀበና አደባባይ ባለው አስፋልት ላይ ቁጥሩ ከ80 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት ደማቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ተደርጓል፡፡ 

Saturday, September 28, 2013

የሞት “ድግስ”


የሞት “ድግስ”
 መስከረም 4 ቀን 1996ዓ.ም ለኢትኦጵ ጋዜጠኛ የስልክ ጥሪ ይደርሰዋል። “ በነገው እለት ከቀኑ 6ሰአት መስቀል አደባባይ በሚገኘው የትግራይ ልማት ዋና ቢሮ 4ኛፎቅ እንድትገኝ” የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል ጥሪ ነበር የደረሰው። ከዛ በፊት ለስድስት ወር የአየር መንገድ የደህንነት ሃላፊ ሃይሌ ጋዜጠኛውን ሲያስጨንቀው፣ የተለያዩ የማግባቢያ ወይም መደለያ ሃሳቦችን ሲያቀርብለት ቆይቷል። መስከረም 2 ቀን ደግሞ በቀበሌ 06/07 መ/ር ቢሮ እንዲገኝ የሚገልፅ መጥሪያ ቢደርሰውም በአጋጣሚ ጋዜጠኛው ስላልተመቸው አልሄደም። በማግስቱ የቀበሌውን ሊ/መ አቶ ቢሻው አበጋዝን ያገኘውና « ትላንት ፈልጋችሁኝ ነበር፤ ለምን ነበር?» ሲል ይጠይቀዋል፤ ቢሻውም « እኛ አይደለንም የፈለግንህ፤ ከደህንነት ቢሮ የመጡ ሰዎች ናቸው የፈለጉህ፤ ባለመምጣትህ ተናደው ነው የሄዱት፤ ለምን እንደፈለጉህ አልነገሩንም፤» በማለት መለሰ። …ከዛ በኋላ ነው - የመስከረም 4 ጥሪ የደረሰው፤ በማግስቱ በተባለው ቢሮ ተገኘ። ከ30 ደቂቃ ቆይታ በኋላ የማህበሩ ዳይሬክተር « ከሚፈልጉህ የበላይ አካላት ጋር አገናኝሃለሁ» በማለት ለጋዜጠኛው ተናግሮ በሚያሽከረክራት ኒሳን መኪና ተያይዘው ቦሌ በሚገኘው የደህንነት ቢሮ አመሩ።..ከአንድ ግዙፍና አስፈሪ ገፅታ ካለው ሰው ጋር ጋዜጠኛውን አገኛኝቶት ወጥቶ ሄደ። ..« እሺ ኢየሩሳሌም አርአያ..» አለ ንቀት በተሞላበት ሁኔታ፤ አስከተለና፥ « ወ/ስላሴ እባላለሁ፤ ....ከእኛ ባልደረባ ጋር ስትገኛኝ ነበር፤ መንግስት ብዙ አማራጮችን አቅርቦልህ..አንተ ግን አሻፈረኝ ብለሃል። ለመሆኑ የምታወጣቸው መረጃዎች ተፅፈው ነው የሚሰጡህ?...ለምንድነው መረጃ የሚሰጡህን የሕወሐት ሰዎች የማትነግረን?..የምናስራቸው፣ የምንጠይቃቸው መስሎህ ነው?...» ሲል ሹሙ ሲናገር፣ ጋዜጠኛው ግን የቀረቡትን መደራደሪያዎች እንደማይቀበል ተናገረ። ለሁለት ሰአት ተኩል ከደህንነት ሃላፊው ጋር ውዝግብ የተቀላቀለበት ቃላት ተለዋወጡ። በተለይ የደህንነት ሹሙ « ..የትግራይ ተወላጅ ያውም ቤተሰብህ አድዋ ሆነው..እንዴት ፀረ-ሕወሐት ትሆናለህ?..ከጠላቶቻችን አንዱ ከሆነው ኢትኦጵ ጋዜጣ ጋር እንዴት ትሰራለህ?..» እያለ ከመናገሩ በተጨማሪ « እንዳንተ የተለማመጥነውና የታገስነው የለም። ብንገድልህስ?..» ሲል በንቀት ሲጠይቅ፣ ጋዜጠኛውም « ምንም ጥያቄና መልስ አያስፈልገውም፤ አሁኑኑ ሽጉጥህን መዘህ ልታደርገው ትችላለህ። እኔ ብእር እንጂ የያዝኩት - ከጀርባዬ ያሰለፍኩት ሰራዊትና መሳሪያ የለም። ..ደግሞም ለስልጣን ያበቋችሁን 36ሺህ ታጋዮች ላይ ምን እንደፈፀማችሁ ስለማውቅ..» አላስጨረሰውም፤ ..« እሱ አይመለከትህም፤ ከማን ጋር ምን እያወራህ እንዳለህ እወቅ!?..ከዚህ በኋላ እንድታስብበት የ15 ቀን ጊዜ ብቻ ሰጥተንሃል። በነዚህ ቀናት አቋምህን አስተካክለህ፣ የተባልከውን ካልፈፀምክ ግን…እንገድልሃለን!! ማንም አያድንህም!! ጨርሻለሁ።» በማለት አምባረቀበትና አሰናበተው። ..ከአስራ አምስት ቀን በኋላ ረቡዕ መስከረም 20 ቀን 1996ዓ.ም ከምሽቱ 3፡30 ሰአት ገደማ በመኖሪያ ቤቱ አቅራቢያ ወ/ስላሴ ያሰማራቸው ሰባት የፌደራል ፖሊስ አባላት “አቦ ድልድይ” አቅራቢያ ጋዜጠኛውን ጥብቀው በያዙት ዱላ የቻሉትን ያክል ቀጥቅጠውና ከፍተኛ ጉዳት አድርሰው ወደ ድልድዩ ወረወሩት። ሶስት ጥርሱ ተሰበረ፣ ጭንቅላቱ 5 ቦታ ተፈነካከተ፤ ሁለቱ እጆቹ፣ ግራ እግሩ፣ ወገቡ፣..አጠቃላይ አካሉ ተጎዳ። ...እነ ወ/ስላሴ ከድርጊቱ በኋላ ለጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና 5 ጊዜ ስልክ ደውለው « የኢየሩሳሌምን ሬሳ ሂድና ከምኒሊክ ሆስፒታል ውሰድ..» ሲሉ ተሳለቁ።…ከጨካኞች፣ ገዳዮችና አምባገነኖች ..የሚጠብቅ ፈጣሪ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባትን የጋዜጠኛውን ነፍስ በኪነ-ጥበቡ ታደጋት። እነሆ ከአስር አመት በኋላ የቀድሞ የደህንነት ሹም ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል እስር ቤት ሲወረወር፥ በእርሱ “ሞት የተደገሰላት” የጋዜጠኛው ነፍስ በህይወት ቆይታ ለማየት በቃች። ሁሉም የዘራውን ሊያጭድ ግድ ነው!! …ይህ ታሪክ የእኔ ነው። 
(በምስሉ የሚታየው ለስድስት ወር ያልጋ ቁራኛ የዳረገኝ የግድያ ሙከራ ከተፈፀመብኝ በኋላ፣ )


መስከረም 4 ቀን 1996ዓ.ም ለኢትኦጵ ጋዜጠኛ የስልክ ጥሪ ይደርሰዋል። “ በነገው እለት ከቀኑ 6ሰአት መስቀል አደባባይ በሚገኘው የትግራይ ልማት ዋና ቢሮ 4ኛፎቅ እንድትገኝ” የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል ጥሪ ነበር የደረሰው። ከዛ በፊት ለስድስት ወር የአየር መንገድ የደህንነት ሃላፊ ሃይሌ ጋዜጠኛውን ሲያስጨንቀው፣ የተለያዩ የማግባቢያ ወይም መደለያ ሃሳቦችን ሲያቀርብለት ቆይቷል።

Thursday, September 26, 2013

ወታደራዊ መኮንኖች የደሞዝ ይጨመርልን ጥያቄ አቀረቡ


ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ካለፉት 8 ቀናት ጀምሮ ስብሰባ ላይ ሲሆኑ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ዋነኛው የመነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑ ታውቋል።
ከመቶ አለቃ በላይ ማእረግ ያላቸው ወታደራዊ መኮንኖች ስብሰባዎችን እያካሄዱ ያሉት የጄኔራሎች ስብሰባ ከወር በፊት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። በጄኔራሎቹ ስብሰባ ላይ ለሰራዊቱ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ተነስቶ የነበረ ቢሆንም፣ “ሰራዊቱ አሁን የሚያገኘው ደሞዝ ለኑሮው በቂ ነው” የሚል መልስ ከሰራዊቱ ዋና አዛዦች ተሰጥቷል።  በተሰጠው መልስ የተበሳጩት  ጄኔራል ሰአረ መኮንን ስብሰባ ረግጠው ወጥተው እንደነበር ታውቋል። ጄኔራሉን ለማረጋጋት ከፍተኛ ጥረት ተደርጎ እንደነበርም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ጄኔራል ሰአረ ለሰራዊቱ ደሞዝ እንዲጨመር አቋም ከያዙት ከፍተኛ መኮንኖች መካከል አንዱ ናቸው።

Wednesday, September 25, 2013

15 የሚሆኑ የአንድነት ፖርቲ አባላት ዛሬ ህገወጥ እስር ተፈጸመባቸው


September 24th, 2013   
 
አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ መስከረም 19 ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ የመኪና ላይ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ 15 አባላቱ ህገወጥ እስር ተፈፀመባቸው፡፡ አባላቱ ከስድስት ኪሎ ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው ጎዳና በመኪና ላይ እየቀሰቀሱ ባለበት ወቅት ሚኒሊክ ት/ቤት ፊትለፊት የፖሊስና የደህንነት ኃይሎች የሚተላለፈውን መኪና መንገድ በመዝጋት ቅስቀሳውን አደናቅፈዋል፡፡

ከለውጡ በኋላስ? (ጋዜጠኛ ተመሰገን ደሳለኝ )


September 24, 2013

ኢህአዴግ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ (በውስጥም በውጪም ተግዳሮቶች) መገፋቱን በሚያመላክቱ የፖለቲካ አጀንዳዎች ላይ የሚያጠነጥን አንድ ፅሁፍ (‹የአብዮቱ የምፅዓት ቀን ምልክቶች›› በሚል ርዕስ) አቅርቤ እንደነበር ይታወሳል፤ ይዘቱም በመጪዎቹ ወራት ወይም ዓመት ስርዓቱ ‹ምርጫ› አሊያም ‹ህዝባዊ› እምቢተኝነት ከሚያመጣው ‹ማዕበል› (እንደበረከት ስምዖን አገላለፅ ‹ናዳን በሚገታ ሩጫ›) የማምለጥ ዕድሉ የጠበበ መሆኑን የሚያመላክት ነው፤ ይሁንና አንድ አብዮት ታላቅ (ውጤታማ) ሊባል የሚችለው አምባገነን ስርዓትን በመቀየሩ ብቻ ስላልሆነ (ሥር-ነቀል ለውጥ የሚፈጥር አብዮት ዋጋ የሚኖረው የዲሞክራሲ ተቋማትን መሰረት መጣል ሲችል ነውና) በቀጣይ መፃኢ ዕድሉ ላይ መነጋገሩ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
Journalist Temasegan Dasaleg
በዚህ ፅሁፍህ ተጠየቅም ‹ከስርዓቱ ለውጥ በኋላ፣ ማን ነው አማራጩ?› የሚለው ጥያቄ ትኩረት ይደረግበት ዘንድ አመላክታለሁ፡፡
ምክንያቱም በጠለፉ መንገድ ከቀሩ አብዮቶች ታሪክ ተምረን፣ ‹መጥነን ካልደቆስን› የሚከፈለውን ዋጋ በብላሽ የሚያስቀር አሳዛኝ ሁናቴ ሊፈጠር ይችላልና (ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን ‹‹አብዮት፣ ለአብዮት ብቻ ሲባል መካሄድ የለበትም›› እንዲል፣ ከኢህአዴግ መገላገሉ መልካም ቢሆንም፣ የአገላጋዩን ማቀፊያ ከወዲሁ መምረጡ ወይም የምንጠይቀውን ማወቁ ብልህነት ነው)

Sunday, September 22, 2013

በኢህአዴግ ቀይ መስመር ላይ የተደረገ ታሪካዊና ውጤታማ ሰለፍ


የሰልፊ አጀማመር ልክ እንደባለፈው ነበር ልዩነቱ የሰአቱ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ የዛሬው 3፡45 ሲሆንየጀመረው የባለፈው ከሶስት ሰአት በፊት ለጉዞ ተነስቶ ነበር፡፡የባለፈው ሰልፍ ላይ መጀመሪያ ላይ የአካባቢው ህብረተሰብ የለሁበትም አይነት የሞላበት የፍርሀት ስሜት የተንጸባረቀበት የነበረ ሲሆን የዛሬው ግን የዛ ፍጹም ተቃራኒ ነበር፡፡በአካባቢው የነበሩ ጥቂት የማይባሉ ፖሊሶች ላይ ሳይቀር ይነበብ የነበረው ስሜት ደግ አደረጋችሁ ፈጣሪ ከእናንተ ጋር ይሁን አይነት ነበር፡፡

Wednesday, September 18, 2013

ርዕዮትና እስክንድር የአውሮፓ ህብረት በሚያዘጋጀው “ሻካሮቭ የነጻነት ሽልማት” የ2013 ተሸላሚ ለመሆን ከሰባቱ እጩዎች ውስጥ ገቡ፡፡



ርዕዮትና እስክንድር የአውሮፓ ህብረት በሚጋጀው  “ሻካሮቭ የነጻነት ሽልማት” የ2013 ተሸላሚ ለመሆን ከሰባቱ እጩዎች ውስጥ ገቡ፡፡ ከ15 ቀን በኋላ መስከረም 20 ለመጨረሻ ውድድር ሚቀሩት 3 እጩዎች የሚታወቁ ሲሆን መስከረም 30 በሚደረገው የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ስብሰባ የአመቱ ተሸላሚ እንደሚለይ ከህብ
ረቱ መግለጫ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ህዳር 11 ቀን በምስራቅ ፈረንሳይ በምትገኘው ስትራስበርግ ከተማ የሽልማት ስነስርዓቱ ይከናወናል፡፡
መልካም ዕድል ለርዕዮትና ለእስክንድር!
ሙሉ መግለጫው የሚከተለው ነው

BREAKING NEWS


September 18, 2013
The Ethiopian Satellite Television has just reported in its breaking news that four senior pilots of the Ethiopian Air Force have defected and joined the opposition Ginbot 7 Movement. The Station stated that some of the defecting capitains have served the Country in the recent Ethiopian Air Force’s involvement in Somalia. ESAT said it will make the names of these pilots, which include Majors, public in its Prime Time News tonight.

የቤተመንግስት ደህንነት ሃላፊ ተነሱ


(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

የቤተ-መንግስት የደህንነት ጥበቃ ዋና ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት የሕወሐት አባል አቶ ጌታቸው ተፈሪ ከስልጣናቸው መነሳታቸውን ምንጮች አስታወቁ። አቶ ጌታቸው ቀደም ሲል በክልል 14 ፖሊስ ኮሚሽን የደሕንነት ልዩ ተወርዋሪ ሃይል ሃላፊ ተደርገው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን የጠቆሙት ምንጮች፣ ከዚያም ወደ ቤተ መንግስት ተዛውረው መመደባቸውንና በተጨማሪ የአገር ውስጥ ደህንነት ምክትል ሃላፊ በመሆን ከአቶ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል ጋር ሲሰሩ መቆየታቸውን አስረድተዋል። የአቶ መለስና ወ/ሮ አዜብ የቅርብ ሰው የሆኑት አቶ ጌታቸው ተፈሪ በነበራቸው ታማኝነት የቤተመንግስት የደህንነት ሃላፊ ተደርገው በአቶ መለስ ተመርጠው እንደተሾሙ ያስታወሱት ምንጮች፣ በማያያዝም እስከ 1994ዓ.ም የቤተመንግስት የደህንነት ጥበቃ በሃላፊነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ዘርኡ መለስ በወቅቱ ከአቶ መለስ ጋር በፈጠሩት የፖለቲካ ልይነት ምክንያት ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ “ኮከብ ሬስቶራንት” የአሁኑ “ሚልክ ሃውስ” መኖሪያ ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ቤታቸው ውስጥ አንገታቸው በስለት ታርዶና በድናቸው ተበላሽቶ መገኘቱን አመልክተዋል። ይህን አሰቃቂ ግድያ ያከናወነው አሁን በእስር ቤት የሚገኘው የቀድሞ አገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊና የአቶ መለስ ቀኝ እጅ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል መሆኑን ምንጮቹ አጋልጠዋል።

Tuesday, September 17, 2013

በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ ተጠየቀ።


ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ሌሎች በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ ተጠየቀ።
መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ ከዓመት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ለ14 ወራት በቃሊቲ እስርቤት ከታሰሩ በኋላ ተፈተው የወጡት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ማርቲን ሺቢ እና ዩዋን ፐርሹን እንዲሁም ዓለምዓቀፍ የሰብዓዊና የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተወካዮች፡ ጋዜጠኞችና በስዊድን የሚኖሩ በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ስዊድናውያን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባዘጋጀው ደብዳቤ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የታሰሩ ጋዜጠኞችን እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

Friday, September 13, 2013

የርዕዮት ደህንነት አደጋ ላይ ነው!

(ሰርካለም አለሙ)
” እኔ ባልፍም እንኩዋን ሺህ ርዕዮቶች ስላሉ በርቱ አትደናገጡ “
* የርዕዮት ደህንነት አደጋ ላይ መሆኑን እንድታዉቁት ስል ነዉ ይህንን በብዙ ሀዘን ዉስጥ ሆኜ የጻፍኩላችሁ ትላንትና እንደሁል ጊዜዉ ስንቅ ይዤላት ወደ ቃሊቲ ሔድኩ በር ላይ ያለዉ ፖሊስ “የርዕዮት እህት ነሽ አይደል እሱዋን መጠየቅ አትችይም በአስተዳደር በኩል ሔደሽ ጠይቂ” አለኝ፡፡ እንዳዘዘኝ በአስተዳደር በር በኩል ሔድኩ ወደ ዉስጥ በስንት ትግል ከስለሺ (የርዕዮት እጮኛ) ጋር ገባን፡፡
Reeyot Alemu
Reeyot Alemu
ከብዙ ጥበቃ በሁዋላ በብዙ ፖሊሶች ታጅባ መጣች ፊትዋ ተለዋዉጦ ስለነበር ምን እንደሆነች ስጠይቃት ከእናት፡ አባት እና ንስሃ አባት ዉጪ ማንም ሊጠይቃት እንደማይችል እና የእነሱን ስም እንድትሰጥ እንደተጠየቀች እና አሚናዘር የሚትባል የሴቶች ክፍል ሀላፊ አልጋዋ ድረስ በመምጣት እንደሰደበቻትና እንደዛተችባት እየነገረችኝ እያለ አሚናዘር የተባለችዉ ሃላፊ ወደኛ በመምጣት ርዕዮትን በማመናጨቅና በመስደብ ከኛ ልትወስዳት ስትሞክር ለምን እንደሆነ ስጠይቃት “ከዛሬ ወዲህ ዐይኑዋን አታዩትም ማንም እኔን ሊያዝ አይችልም የእናንተ ጋዜጣና ሚዲያ ምን እንደሚያመጣ እናያለን ” በማለት ርዕዮትን በማዋከብ እና በመጎተት እየሰደቡ ወሰዱዋት፡፡ ምድር ላይያሉ ሰቅጣጭ እና ለህሊና የሚከብዱ ስድቦችን አወረዱብን በዚህ መሀል ርዕዮት ድምጹዋን ከፍ አርጋ “የማልጨርሰዉን ነገር አልጀምርም እኔን ለማንበርከክ እና ለማሸማቀቅ ክሆነ መቼም አላረገዉም ትገይኝም ከሆነ ነይ ተኩሺ ” ስትል ጎትተዉ ወሰዱዋት፡፡

Friday, September 6, 2013

የጋራ ንቅናቄው ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን ይቆማል!

September 6, 2013

የወጣት አመራሮቹን ሰላማዊ የትግል መስመር ይደግፋል!
ያለፈው እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጠርቶ በነበረው የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ላይ በህወሃት/ኢህአዴግ የተወሰደውን ጽንፈኛ፣ አክራሪና አጸያፊ የውንብድና ተግባር የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ይኮንናል፤ ያወግዛል፡፡ ፓርቲው ሰልፉን ለማካሄድ ከሁለት ወራት በፊት ፈቃድ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ቅዳሜ ነሐሴ 25፤2013 የፌዴራል ፖሊስና የደኅንነት አባላት የፓርቲውን ጽ/ቤት ጥሰው በመግባት የፈጸሙት ተራ የውብንድና ተግባር ብቻ ሳይሆን የህወሃት/ኢህዴግን ማንነት በግልጽ ያሳየ ለመሆኑ ከማንም በላይ ተግባሩ ራሱ ምስክር ነው፡፡Ethiopian news
በዕለቱ እንደሆነው የህወሃት/ኢህአዴግ አሸባሪ ፖሊሶች የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤትን ከመውረራቸው በፊት ኤሌክትሪክ መስመሩን ቆርጠዋል፡፡ በቀጣዩም ለእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ዝግጅት እያደረጉ የነበሩትን አመራሮችና ፈቃደኛ ሠራተኞችን ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ ከደበደቡና ካሰቃዩ በኋላ ለሰዓታት አስረዋቸዋል፡፡ ወጣቶቹ ከተፈቱ በኋላ ለእሁዱ ስብሰባ ተመልሰው ዝግጅት እንዳያደርጉ የህወሃት/ኢህአዴግ አሸባሪዎች የፓርቲዉን ጽ/ቤት እስከ እሁድ ድረስ በመቆጣጠር ኮምፒውተሮችን፣ የጽህፈት መሣሪያዎችን፣ ሠንደቅዓላማዎችን፣ መፈክሮችን፣ … በማውደም፤ የሚፈልጉት በመውሰድ ሰልፉ እንዳይካሄድ አድርገዋል፡፡ ይህንን ተግባር የሚመሰክር ከበቂ በላይ የፎቶግራፍ፣ የሰው፣ … ማስረጃ ቢኖርም ህወሃት/ኢህአዴግ ሁሉንም በመካድ ለዓለምአቀፍ ሚዲያ አንዳች ነገር እንዳልተደረገ በመናገር የተለመደውን ዓይን ያወጣ ቅጥፈት ደግሟል፡፡

ከሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ (ለውጥ ፈላጊዎች በሙሉ ሊሰሙት የሚገባ)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጂነር ይልቃል፤ ከአትላንታው ማህደረ አንድነት ሬዲዮ ጋር ከ30 ደቂቃ በላይ የፈጀ ቃለ ምልልስ አድርገዋል። በዚህ ቃለ ምልልስ በኢህአዴግ አንጋቾች እና ደህንነቶች የደረሰባቸውን ወከባ በዝርዝር ይገልጻሉ። ከዚህ ሁሉ ወከባ እና እንግልት በኋላም ቢሆን፤ ሰላማዊ ትግሉን ለመቀጠል ጽኑ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። በለውጥ የሚያምኑ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ሊሰሙት የሚገባ ቃለ ምልልስ ነው። እርስዎ ይስሙት፤ ላልሰሙትም ያሰሙ።

Monday, September 2, 2013

በመንግስታዊ ውንብድና ትግላችን አይገታም! ሰማያዊ ፓርቲ

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ባካሄደው ታላቅ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለመንግሥት ያቀረባቸው ጥያቄዎች አስፈላጊው ምላሽ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ይህ ካልሆነ ግን ከሦስት ወር በኋላ ተቃዉሞውን ከፍ ባለ ደረጃ እንደሚያቀርብ በመጋለፅ ሰልፉን አጠናቋል፡፡ ለተነሱት ጥያቄዎች የተገኘ ምላሽ ባለመኖሩ ፓርቲው ለሕዝብ በገባዉ ቃል መሠረት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ታላቅ የተቃዉም ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሔድ በመወሰን በሕግም ሆነ በሥራ የሚያስፈልጉ ነገሮችን በማጠናቀቅ እለቱን በመጠበቅ ላይ እያለ ምንም አይነት መለዮ ባልለበሱ ግለሰቦች የሚመራ የፖሊስ መለዮ ለባሽ ታጣቂዎች ከሕግ ውጭ ነሐሴ 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ከምሽቱ 12 ሰዓት አካባቢ የፓርቲውን ቢሮ ጥሰው በመግባት ፓርቲው ይጠቀምባቸው የነበሩ የቅስቀሳ ቁሳቁሶችና ሌሎች የፓርቲውን ንብረቶች ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወርሰዋል፡፡ በፓርቲው ፅ/ቤት የነበሩ አባላትን እና መሪዎችን በጠመንጃ በማስገደድ ወደተለያዩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያዎች ከፋፍሎ በመውሰድ አስረዋል፣ ዘልፈዋል፣ አስፈራርተዋል እንዲሁም አረመኔያዊ በሆነ መንገድ ደብድበዋል፡፡ አንዳንዶችን በጭቃ ላይ ጭምር አንከባለዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሕገ ወጥና አረመኔያዊ ድርጊት ሕገ መንግስታዊ የሆነውን መብታቸውን በሚጠቀሙ ዜጎች ላይ ሲፈፀምና በሕግ ማስከበር ስም በቁጥጥር ሥር በዋሉ ዜጎች ላይ የግል ጥላቻን መወጣጫ እስኪመስል ድረስ ማንኛዉንም የማንአለብኝነት ድርጊት ሲፈፅሙ ማየት ያልታጠቁ ዜጎችን አቅመ ቢስነትና የሕግ ከለላ ማጣትን ገሃድ አድርጎታል፡፡ ይሕ አይነቱ የጡንቻ ሥራ በአንድ በኩል ልብን በሐዘን የሚሰብር ድርጊት ሲሆን በሌላ በኩል ለነፃነትና ለፍትህ የሚደረገው ትግል እጅግ ትክክለኛና ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡