Thursday, October 31, 2013

የጉዲፈቻ ልጃቸውን የገደሉ ተፈረደባቸው


ኣንዲት የጉዲፈቻ ልጃቸውን ኣሰቃይተው ለሞት ያበቁ ባልና ሚስት አሜሪካውያን ከ28 እስከ37 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተፈረደባቸው።

gudifecha
የ13 ዓመትዋ ሐና ዊሊያምስ ህይወቷን ያጣችዉ በጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን ቀመር ግንቦት 12 ቀን 2011 ሲሆን ከትናንንት በስተያ ማክሰኞ ዕለት ያስቻለው የሲኣትል ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ ሚስት ወ/ሮ ካሪ ዊሊያምስ 37 ዓመት እና ባል ላሪ ዊሊያምስ ደግሞ 28 ዓመት እንዲታሰሩ ፈርዶባቸዋል።
ካሪ እና ላሪ ዊሊያምስ ኣንድ ሌላ እትዮጵያዊ የጉዲፈቻ ልጅን ጨምሮ ስድስት አብራካቸዉ የተገኙ ልጆችም ኣሏቸው።

አሳዛኝ ዜና -በጀርመን ህክምና እየተከታተለ የሚገኘው ኮሜዲያን አብርሐም አስመላሽ አረፈ።


የዲስክ መንሸራተት አጋጥሞት በጀርመን ህክምና እየተከታተለ የሚገኘው ኮሜዲያን አብርሐም አስመላሽ አረፈ።

ነፍስ ይማር

የኢዴፓ_ገበና_ሲገለጥ (ሊነበብ የሚገባው ደባ)


የልደቱ_አያሌው_ኢዴፓ_በየትኛው_ሞራሉ_ነው_ተቃዋሚውንም_ይሁን_ገዢውን_ፓርቲ_የሚተቸው??

የአቶ ልደቱ አያለውን መጽሃፍ የጻፈው በወያኔ ልዩ ትእዛዝ አቶ
ገነነ አሰፋ ነው።
ዶክተር በየነ ጴጥሮስ እና ሻለቃ አድማሴ መላኩ በአቶ መለስ ትእዛዝ የወር ደምወዝ ነበራቸው።
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በኢዴፓ ህልውና አያምንም። ዘላለም ህዝቡ ኢዴፓን በበጎ መንፈስ አያየውም። በአሁን ሰአት ለተፈጠረው ኢህአዴጋዊ አክራሪነት እና የፖለቲካ ጽንፈኝነት ተጠያቂው ኢዴፓ እና አመራሩ ናቸው። ኢዴፓ ብሎ ራሱን የሚጠራው በኢሕኣዴግ የጎለበተው ድርጅት ባካሄደው ስብሰባ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እና ገዢውን ፓርቲ እንደተቸ እየሰማን ነው። ኢዴፓ የ97 ምርጫ የህዝብን ድምጽ አፈር የከተተ እና ከገዢው ፓርቲ ጋር መሰሪ ተግባራትን በማከናወን የቅንጅት አመራርን ለእስር ቅንጅትን ደግሞ አላማውን በማኮላሸት ድባቅ እንዲመታ ያደረገ ታማኝ ቅጥረኛ በራሱ አጠራር ተቃዋሚ ፓርቲ ነው።

እረፍት የሚነሳው ህምም


የኮንትራት ሰራተኞች ስቃይ፣ የእኛ ፍርሃትና የፖለቲከኞች ጭካኔ

saudi 1


እረፍት አደርግ ብየ ከማህበራዊ መገናኛ መድረኩ ገለል ባልኩባቸው እንደ ብርሃን ፍጥነት በሚወረወሩት ባለፉት ጥቂት ቀናት ከበርካታ ወዳጆቸ በርካታ መልዕክቶች ይደርሱኛል። ብዙው መልዕክት ደግሞ የሚያጠነጥነው በጅዳ እና በአካባቢው በተፈናቃይ የኮንትራት ሰራተኞች አሰቃቂ ስቃይ ላይ ያተኮራል … ለነገሩ የአብዛኞቹ መልዕክቶች ብቻ ሳይሆኑ ከመልዕክቶች ጋር የሚላኩልኝ መረጃዎች እረፍት የሚነሱ ናቸው! …

Wednesday, October 30, 2013

ፉዓድ ኢብራሂም ዳግም ዋሊያዎቹን ተቀላቀለ


የቀድሞው የአሜሪካ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ተጨዋችና ኢትዮጵያዊ የዘር ሀረግ ያለው ፉዓድ ኢብራሂም ዛሬ ዋሊያዎቹን ተቀላቀለ፡፡

“ትግራይ ከአንድ ፋብሪካ እንደወጣ ሳሙና”


 ዛሬ አንድ ታሪክ ያስታወሰኝ አስተያየት አነበብኩ። በ97 ምርጫ ቅስቀሳ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበርኩ። በኢህአዴጎችና ቅንጅቶች መካከል የነበረ ክርክር እከታተል ነበር። የማናቸው ደጋፊ ወይ ተቃዋሚ አልነበርኩም። አንድ ሲኔራችን ነበር። ሁሌ ወደ ዶርማችን እየመጣ ስለነዚህ የቅንጅት መሪዎች መጥፎ ታሪክ ይነግረናል፤ ለትግራይ ህዝብ መጥፎ አመለካከት እንዳላቸው (እንዲህ አደረጉ፣ እንዲህ አሉ እያለ)፣ የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣናት የነበሩና ወንጀለኞች መሆናቸው ወዘተ።

የቦሌ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን የድረሱልኝ ጥሪ አሰማች


 

ኢሳት ዜና :- የቦሌ ለሚ ቅ/ሩፋኤል የጻዲቁ አቡነ ኤዎስጣቲዎስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት መልአከ ብርሀን ተከስተ ካሳሁን “የድረሱልን ጥሪን ይመለከታል” በሚል ርእስ ለለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ረዳትና የጅማ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ለሆኑት ለ ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ በጻፉት ደብዳቤ ላይ፣ የመንግስት ባለስልጣናት ቤተክርስቲያኑዋን በ7 ቀናት እንዲያፈርሱ እንዳዘዙዋቸው ተናግረዋል።