Tensay Abera (Co-pilot Hailemedhin’s sister)
ቦይንግ 767-300 ጄኔቭ አርፎ፣ መንገደኞቹ ወደየመድረሻቸው ተጉዘው አውሮፕላኑም ወደ ሀገሩ ተመልሷል። ነገር ግን የወሬው በረራ ማረፊያ ቦታ እንዳጣ ነው። የኃይለመድን ጉዳይ በየቦታው የመወያያ ርዕስ እንደሆነ ነው፣ ይቀጥላልም። የግምት ወሬዎች እዚህም-እዚያም እየተረጩ ነው። በተለይ የመንግስት ካድሬዎችን “ቢዚ” አድርጓቸዋል። በምን መልኩ የድራማውን ድርሰት እንደሚጽፉ ግራ ግብት ብሏቸዋል የአዕምሮ ሕመምተኛ ሊሉት ፈለጉ …ከዚያ ትዝ ሲላቸው አዕምሮ ታማሚ ሆኖ አየር መንገዱ መንግስት እንዴት እንዲያበር ፈቀደ፣ ለአብራሪዎቹ ምርመራ አያደርግም ወይ የሚሉት ጥያቄዎች ሊከተሉ ሆነ። ቀጥለው አባትዬው እቁብ ሰብሳቢ፣ አራጣ አበዳሪ… ተደርገው ተሳሉ። እእ..ደራሲዎቹ የቤተሰብ ጣጣ መሪ ተዋናዩ ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ አልታይ አላቸው። የኃይለመድን እህት ሆነው የተዋቀረ እና የተዋቃ ጽሑፍ በፌስቡክ ላይ አከታተለው ጻፉ…በርግጥ ይሄኛው የወጭ የዜና አውታሮች ዘንድ ደርሶላቸው ተራግቦላቸዋል። ተአማኒነት ባያገኝም።