መቀመጫውን በኒዮርክ ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ቡድኑ /CPJ/ ባለፈው ረቡዕ ይፋ ባደረገው ሪፖርት፤ ጋዜጠኞችን በማሰር ከአለም አስር አገሮች መካከል ኢትዮጵያን በሁለተኛ ደረጃ ያስቀመጠ ሲሆን ኤርትራ ቀዳሚ ሆና፣ ግብፅ በሶስተኝነት ተቀምጣለች፡፡
Saturday, December 21, 2013
Wednesday, December 18, 2013
“አና ጐሜዝ አሁንም ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ይቆረቆራሉ” – አቶ አስራት ጣሴ (የአንድነት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ)
ከአቶ አስራት ጣሴ (የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ)
ከአና ጐሜዝ ጋር ከአንድ ሠዓት ተኩል ለማያንስ ጊዜ ነው የቆየነው፡፡ የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላት ከእኛ ጋ የተገናኙት ገለፃ ለማድረግ አስበው ሣይሆን የእኛን አስተያየት ለመስማት ነበር፡፡ ውይይቱ፣ ኢትዮጵያ ያለችበትን ተጨባጭ ሁኔታ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን እና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችን የሚዳስስ ነበር፡፡ በወቅቱ ከሞላ ጐደል ተደጋጋፊ እንጂ የሚቃረኑ ሀሣቦች አልተነሱም፡፡ በእኔ በኩል፣ በኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል በከፍተኛ ችግርና አደጋ ላይ እንደሚገኝ፣ ኢትዮጵያም መስቀለኛ መንገድ ላይ እንደሆነች፣ ከፊታችን አሳዛኝና አስጊ ሁኔታዎች እንዳሉ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ሕዝቡ ሰላማዊ ትግሉን አስመልክቶ ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታዎች እያሣየ መሆኑን ገልጫለሁ፡፡“ሰላማዊ ትግል” የሚለው “ሰላማዊ እንቅልፍ” የሚል ደረጃ ላይ
Tuesday, December 17, 2013
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተመሰረተበትን አንደኛ አመት አስመልክቶ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተመሰረተበትን አንደኛ አመት አስመልክቶ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ
ቀን ታህሳስ 7 2006
ታህሳስ 7 2006 ዓም የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከተመሰረተ አንድ አመት ሞላው። አንድ አመት በጭንቅና በአሳር ለተያዘች የዛሬይቱ ኢትዮጵያና ህዝቧ እጅግ ረጅም ግዜ እንደሆነ ህዝባዊ ሃይሉ በሚገባ ይገነዘባል። ባላፈው አንድ አመት ውስጥ የኢትዮጵያን ህዝብ የመከራ፣ የአሳርና የውርደት ህይወት ይበልጥ እየሰፋ፣ የሚፈጸምበት ግፍ ይበልጥ እየገዘፈ መሄዱን አይተነዋል። በሃገርና በህዝብ ላይ እየወረደ ያለውን ወያኔ ወለድ የስቃይና የፍዳ ናዳ በቅጡ ላጤነው ሃገሪቱና ህዝቧ የአዳዲስ የስቆቃና የመከራ አይነቶች መፈተኛ ቤተ ሙከራዎች እየተደረጉ ለመሆኑ ጥርጥር አይኖረውም። ለሚራበው፣ ለሚረገጠው፣ በግፍ ለታጎረው፣ በኑሮ ውድነት ለሚጠበሰው፣ ለተሰደደው ለተፈናቀለው ኢትዮጵያዊ እንድ አመት በሲኦል የቀናትና የወራት መቁጠሪያ እንደሚለካ ዘመን እጅግ የረዘመ የስቃይ ግዜ ነው።
“ሕወሓት ከመለስ ሞት በኋላ እየተዳከመ ያለ ድርጅት ነው፤ ኢህአዴግ ለዘለዓለም መግዛት አለብኝ የሚል ድርጅት ነው” ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ
ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ ከህወሓት ጋር 17 ዓመታት በትግል ያሣለፉ እና ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዷ ነበሩ፡፡ በ1993 ዓ.ም ከፓርቲው ከተሰናበቱ አባላት አንደ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት የ“አረና” ፓርቲ አባል የሆኑት ወ/ሮ አረጋሽ በአጠቃላይ ጉዳዮች ዙሪያ ከ“ሎሚ” አዘጋጅ ቶማስ አያሌው ጋር ያደረጉት ቆይታ የመጀመሪያ ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
ሎሚ፡- የኢህአዴግ ጭቆናና፣ አፈና፣ የተንሰራፈው በመላው ሀገሪቱ ነው የሚል አቋም ካላችሁ፣ ብሔር ተኮር ፓርቲ የመሰረታችሁበት ምክንያት ምንድነው;
አረጋሽ፡- ፓርቲ የሚመሰረተው በአካባቢ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት አድርጐ ነው፡፡ ተጨባጭ ሁኔታ ስል የማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሰብዓዊ መብት፣ የኢኮኖሚ ችግሮችን ለመጥቀስ ፈልጌ ነው፡፡ ማንኛውም ድርጅት በዚህ መልኩ ነው የሚመሰረተው፡፡ አረናም በዚሁ መሠረት የተመሠረተ ፓርቲ ነው፡፡
Monday, December 16, 2013
በደቡብ ሱዳን የተደረገው መፈንቅለ መንግስት መክሸፉን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ተናገሩ
በደቡብ ሱዳን የተደረገው መፈንቅለ መንግስት መክሸፉን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ተናገሩ የአዲሲቷ አገር መሪ የሆኑት ሳልቫኪር የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ታማኝ ወታደሮች መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሌሊቱን ተኩስ መጀመራቸውን ተናግረዋል። ችግሩ በቁጥጥር ስር መዋሉን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ እንዲህ አይነቱን ድርጊት
ሁለገብ ትግል – ከኔልሰን ማንዴላ ጋር የምንጋራው የትግል ስትራቴጂ ግንቦት 7 ለፍትህና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄም በኔልሰን ማንዴላ ዜና እረፍት የተሰማውን ሐዘን በመግለጽ መግለጫ ያወጣ ቢሆንም የትግል ተሞክሯቸው ለአገራችን ስላለው ጠቀሜታ ተጨማሪ ቁም ነገሮችን ማንሳት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል። ኔልሰን ማንዴላንና የትግል ጓዶቻቸው መሣሪያ እስከማንሳት ያደረሳቸው የደቡብ አፍሪቃ አፓርታይድ አገዛዝ ዋነኛው መገለጫው የባንቱስታን ሕግ ነበር። በዚህ ህግ መሠረት ደቡብ አፍሪቃ ዘርን መሠረት ያደረጉ አስር “ባንቱስታ” የተሰኙ “ራስ ገዝ” ግዛቶች ተቋቁመው ነበር። ያኔ በደቡብ አፍሪቃ አገዛዝ ሥር በነበሩ የደቡብ ምዕራብ ግዛቶች ደግሞ ሌላ አስር ባንቱስታዎች ነበሯቸው።
በእያንዳንዱ ደቡብ አፍሪቃዊ መታወቂያ ባንቱስታው እንዲገልጽ ህጉ ያስገድዳል። የአንዱ ባንቱስታ ነዋሪ ያለልዩ ፈቃድ ወደሌላው ባንቱስታ መሄድ አይችልም። ከዚህም ሌላ ለነጮች ብቻ በተከለሉ ቦታዎች ጥቁሮች ለሥራ ካልሆነ በስተቀር ለሌላ ማናቸው ተግባር እንዳይገኙ ህጉ ያዛል። አፓርታይድ የደቡብ አፍሪቃ ዜጎችን በየዘር ክልሎቻው ውስጥ አጉሮ አገራቸውን እስር ቤታቸው እንዲሆን አደረገው። ይህንን ለመቃወም ኔልሰን ማንዴላ እና የወቅቱ ታጋዮች በመጀመሪያ ሰላማዊ ትግልን ሞከሩ፤ ያ አላዋጣ ሲል መሣሪያ አነሱ። በአሁኑ ሰዓት ባንቱስታን መሰል የክልል አስተዳደር ያለው በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው። ልክ በአፓርታይድ ደቡብ አፍሪቃ እንደነበረው ሁሉ የኛም መታወቂያዎች ዘራችንና ክልላችንን ይገልፃል። በአፓርታይድ ደቡብ አፍሪቃ እንደነበረው ሁሉ እኛም ከክልላችን ውጭ ተንቀሳቅሰን መሥራትና መኖር አንችልም።
Subscribe to:
Posts (Atom)
