Wednesday, November 13, 2013

ብሄራዊ ውርደት፤ የምንመጻደቅበት ‘ሌጋሲ’


The suffering of Ethiopians in Saudi Arabia
ክንፉ አሰፋ 
ወገናችንን በጥይት ሲደፉት በራሱ ላይ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንድራችንን ጠምጥመውበታል[1]። ጭካኔ በተሞለበት መንገድ የተገደለው ይህ ኢትዮጵያዊ አስከሬኑም በሰላም አላረፈም። በአካሉ ላይ ያረፈውን ጨርቅ በሴንጢ እየቆራረጡ በሰብአዊ ፍጡር ላይ ሊደረግ የማይገባውን ሁሉ አደረጉበት። ድርጊቱ ናዚዎች በኦሽዌትስ ይፈጽሙት የነበረውን አሰቃቂ ግፍ ያስታውሰናል። በ21ኛው ዘመን እንዲህ አይነቱ ክስተት ይደገማል ብሎ የሚያስብ የለም። እነሆ ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመችው ነው። በስውር ሳይሆን በግልጽ። እንደ ኦሽዊትስ በታጠረ የማጎርያ ካምፕ ሳይሆን በአደባባይ።

Tuesday, November 12, 2013

የኢሕአዴግ መንግሥት አሳምሮ ይፈራል! በኃይሉ አርአያ (ዶ/ር)

የኢሕአዴግ መንግሥት አሳምሮ ይፈራል! በኃይሉ አርአያ (ዶ/ር) ሰሞኑን የኢሕአዴግ መንግሥት ይፈራል አይፈራም የሚል ጉዳይ ከፓርላማ ተነስቶ ወደ መገናኛ ብዙኃንም ደርሷል። ጉዳዩ የተነሳው የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ አዲሱ ፕሬዚዳንታችን በፓርላማ ያደረጉትን ንግግር አስመልክቶ ባቀረቧቸው የማማሻሻያ ሐሳቦችና ጠቅላይ ሚኒስትራችን በሰጡት ምላሽ ዙሪያ ነው። ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዝ ሪፖርተር ጋዜጣ ጥቅምት 13 ቀን 2006 ዓም በአወጣው ዕትሙ ‹‹’ፈሪ’ መንግሥት?›› በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ የማነ ናግሽ ጥሩ ትንተና አቅርቧል። የፍርኃት ነገር ከተነሳ ጋዜጠኛው

መከራው ቀጥሏል- ኩዌት ደግሞ ሌላ የኛን ትኩረት የሚሻ ነገር ዛሬ ተፈጽሟል።

መከራው ቀጥሏል – የኛም ጩኸት እንዲሁ ይቀጥላል! ኩዌት ደግሞ ሌላ የኛን ትኩረት የሚሻ ነገር ዛሬ ተፈጽሟል። በኩዌት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መካከል 1ሺ የሚሆኑት የሚሰሩት በአንድ የጽዳት ኩባንያ ውስጥ ነው። ነገር ግን በምን ምክንያት እንደሆነ ባልተገለጸ ሁኔታ ይኸው የጽዳት ኩባንያ 1ሺዎቹንም ኢትዮጵያውያን ከትናንት እሁድ ጀምሮ ከሥራ አባሯል። ኩዌት ታይምስ ዛሬ ህዳር 2 (ኖቬምበር 11) እንደጻፈውና

ወያኔ ማለት ቁምጣ ለብሶ የመጣ ደርግ ነው ፡፡

ጥቁር ሽብር ወያኔ ቁምጣ የለበሰ ደርግ ነው ! እመኑኝ በየትኛውም የታሪክ ገጠመኝ የሳወዲ መንግስት የዚህ አይነት ድፍረት ያውም በአደባባይ በዜጎቻችን ላይ አሳይቶ አያውቅም ፡፡ ነገሮችን ተመልሰን ከተመለከትን ይህ ግፍና በደል የእኛው ባለስልጣናት ሳውዲወችን አደፋፍረው ያስፈፀሙት ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ሁለት ፖለቲካዊ ምክንያቶች አሉት ፡፡ የመጀመሪያው ፡- የወያኔ ባለስልጣናት በሳውዲ የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያንን ቦንድ እንዲገዙ በሰበሰቡበት ወቅት ተደጋጋሚ ተቃውሞ ደርሶባቸው እንደነበር የሚታወቅ ነው ፡፡ ይህም ድምፃችን ይሰማ ባሉ ሙስሊሞች ላይ በሃገር ውስጥ የሚደርሰው በደል ይቁም ለጥያቂያቸውም አጥጋቢ

Monday, November 11, 2013

ሰበር ዜና አርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ በተማሪዎች በተነሳ ተቃውሞ ግቢው በከፍተኛ ውጥረት ላይ ይገኛል፡፡

ሰበር ዜና 

አርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ እየተማሰ ነው፡፡ በውሃ እጥረት ችግር በተማሪዎች በተነሳ ተቃውሞ ግቢው በከፍተኛ ውጥረት ላይ ይገኛል፡፡ የፌድራልና የአጋዚ ወታደሮች ግቢው ውስጥ ገብተዋል፡፡ ተማሪዎችን እየደበደቡ ነው፡፡ ወደ ላይ እየተኮሱ ነው፡፡ በርካታ ተማሪዎች እየተደበደቡ ወደ መኪና እየተጫኑ ነው፡፡ውጥረቱ አይልዋል፡፡ ፖሊሶች ወደ ላይ እየተኮሱ ነው፡፡ ግቢው ውስጥም የተነሳ እሳት መኖሩን ቦታው ድረስ በመደወል ያነጋገርናቸው ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ ዝርዝሩን በዛሬው ፕሮግራም ይጠብቁን

Sunday, November 10, 2013

ለዜጎች ስደት እንዲሁም በስደት ለሚደርስባቸው ሰቆቃ ተጠያቂ ሥርዓቱን የሚመራው መንግሥት ነው!!



ቀደም ባሉት ዘመናት ወደ ውጭ ሀገር በተለያየ ምክንያት የተጓዙ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትን፤ የእናት ሀገራቸውን ምድር የሚረግጡበትን ቀናት ይቆጥሩና ይናፍቁ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን በዋናነት ወደ ውጪ ሀገር የሚሄዱት ለትምህርት ሲሆን የዚያን ዘመን ወጣት ትምህርቱን ጨርሶ በመመለስ የሀገሩን እና የሕዝቡን ውለታ ለመክፈል የነበረው ጉጉት ከፍተኛ ነበር፡፡ ተምሮ በውጪ ሀገር መቅረት ሀገርን እንደመክዳት የሚያስቆጥር በመሆኑ በኢትዮጵያውያን ህሊና ስደት ተቀባይነት አልነበረውም፡፡
ዛሬ ዛሬ ሁኔታዎች ሁሉ ተለዋውጠው የኢትዮጵያ ህዝብ እጣ ፋንታ ፍልሰትና ስደት ሆኗል፡፡ ስደት የማያባራ የኢትዮጵያውን የሕይወት ገጽታ ሆኗል፡፡ የገጠሩም የከተማውም ሰው ወደ ውጭ ሀገር ይሰደዳል፡፡ ወጣቶች ይሰደዳሉ፡፡ እህቶቻችን ይሰደዳሉ፡፡ ሕፃናት ጭምር በጉዲፈቻ ስም ይሰደዳሉ፡፡ ‹ሕጋዊ› በተባለውም ሆነ በሕገ-ወጥ መንግድ ሕዝባችን ወደ ውጭ ሀገር ይነጉዳል፡፡ በዚህ የተነሳም በወሊድ ምጣኔ ሳይሆን በሰደት ምክንያት አምራች የሆነው የህዝብ ቁጥር ሊቀንስባቸው ከሚችሉ ሀገሮች ኢትዮጵያ አንዷ ሆናለች፡፡

ቴዎድሮስ አድሃኖም ህገወጥ ኢትዮጵያውያን እንዲያዙ የተስማማበት ሰነድ አለን"የሳኡዲ ባለስልጣናት,


በሪያድ የዛረው ሰልፍየሚመጣውን አደጋ በመፍራትተበትኗል::
999410_10201428110199302_1866404023_n“ቴዎድሮስ አድሃኖም ህገወጥኢትዮጵያውያን እንዲያዙየተስማማበት ሰነድአለን”የሳኡዲ ባለስልጣናት
አምስተኛ ቀኑን የያዘው የሳኡዲጸረ ኢትዮጵያውያን ዘመቻእንደቀጠለ ሲሆን ሁኔታዎችንለመፍታት የተደረጉ ጥረቶችከዚህ
ቀደም የኢትዮጵያመንግስት እና የቆንስላውዲፕሎማቶች በሰርኡት ስህተትመስመር ሊይዝ አልፈለገም::
እንደ ሳኡዲ ባለስልጣናትአነጋገው የውጪ ጉዳይሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ባደረጉት ጉብኝት ሃገራቸው ህገወጥ ኢትዮጵያውያንን እንዲያስወጣ እና በምትኩ40,000 ህጋዊ ስደተኞችን እንደሚልኩ የፈረሙበትን ማስረጃ ይዘዋል::