Thursday, February 6, 2014

ምሁራኑ ሠልጣኝ፣ ሹመኞች አሰልጣኝ የሆኑበት ዩኒቨርሲቲ ሆኗል – ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ

addis ababa university


መጽሔታችን የአገራችን የትምህርት ሁኔታበከፍተኛ ደረጃ ችግር ላይ የወደቀ መሆኑን በመገንዘብ፣ የችግሩን ጥልቀት ለማወቅና የመፍትሄ ሃሳቦችን ለማስቀመጥ በዘርፉ ጥናትና ምርምር ካደረጉ ምሁራን ጋር ተከታታይ ውይይቶችንስታደርግ ቆይታለች፡፡ በዚህ ዕትማችንም ውይይቱን በመቀጠል ከዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ጋር ስለትምህርት ፍልስፍና፣ ስለዩኒቨርሲቲ ተልዕኮና ስለሌሎቸ ተያያዥ ጉዳዮች ቆይታ አድርገናል፡፡ ዶ/ር ዳኛቸው ለአብዛኛው የመገናኛ ብዙኃን ተከታታይ እንግዳ ስላልሆኑ ማስተዋወቅ ያለብን አይመስለንም፡፡ ውይይቱን እነሆ፡-

Tuesday, February 4, 2014

አቡጊዳ – ከሳኡዲ የተለመሱ ተቃዉሞ ሊኦያሰሙ ሲሉ በፖሊስ ተበተኑ !


በሳዉዲ መንግስት በግፍና ጭካኔ ተባረው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የተደረጉ ኢትዮጵያዊያን በአዲስ አበባ፣ በዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ፣ «መንግስት ትኩረት አልሰጠንም» በሚል ድምጻቸውን ለማሰማት የተሰባሰቡ ወደ 400 መቶ የሚሆኑ ኢትዮጵያዉያን በፖሊሲ እንዲበተኑ መደረጉን የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነው የፍኖት ጋዜጣ ዘገበ።

Monday, February 3, 2014

ልፋ ያለው በሕልሙ ዳውላ ይሸከማል! ጠርናፊና ተጠርናፊ (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም )

መስፍን ወልደ ማርያም

Prof. Mesfin Woldemariam : is an Ethiopian Human Rights activist and philosopherጥር 2006
ሰሞኑን እንደአዲስ ሆኖ የሚወራው ስለጥርነፋ ነው፤ ጥርነፋ ከዲያብሎስ ፋብሪካ የወጣ የክፋትና የጭቆና መሣሪያ ነው፤ ሰዎችን በመጨቆንና በማሰቃየት፣ ምቾትና እንቅልፍ በማሳጣት፣ ፍርሃትንና ስጋትን በማሰራጨት ሕዝብን ለጥ-ጸጥ አድርጎ ለመግዛት የሚፈልጉ ጠርናፊዎች፣ አምባ-ገነኖች፣ ጨቋኞች፣ አፋኞች፣ ዘራፊዎች፣ ወሮበሎች፣ ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ሕግ የማይገዛቸው፣ አምላካቸው አድርገው የሚያገለግሏቸው ሎሌዎችን በሆዳቸው ገዝተው የሚያሰልፉ ናቸው፤ እንኳን የገጠር ልጆችና አኛም የአዲስ አበባዎቹ መሰንከል ምን እንደሆነ እናውቃለን፤ እንስሳትን (በቅሎዎችንና አህዮችን፣ አንዳንዴ በገግና ፍየልም) የፊት እግር ከኋላ እግር ጋር በአጭር ገመድ እያሰሩ እንደልባቸው እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ ነው፤ ሀብት በመሆናቸው ቢጠፉ ባለቤቶቹ ይጎዳሉ፤ ስለዚህ በየአካባቢያቸው ያለውን እየጋጡ ችለው እንዲኖሩ ለማድረግ ቀላሉ ዘዴ መሰንከል ነው፡፡

Thursday, January 30, 2014

“ኢትዮጵያውያን ለምንድን ነው የውጭ ገበሬዎች የሚያስፈልጓቸው? ምንድን ነው ይዘውልን የሚመጡት?” አቶ ግርማ

"አንድም ሰው ከቀዬው እንዲፈናቀል አልተደረገም" ሚኒስትር ዴኤታ

displaced anuaks


  • “ሰፋፊ የእርሻ ኢንቨስትመንቶች እንደታሰቡት ውጤታማ አልሆኑም” መንግሥት
  • መንግሥት የውጭ ባለሀብቶች የመሬት ቅርምት ኢትዮጵያን አይመለከትም አለ
የውጭ ባለሀብቶች በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ ለመሰማራት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ወስደው እያለሙ እንጂ፣ መሬት ለመቀራመት ብለው ወደ ኢትዮጵያ አልገቡም ሲል ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
“መሬት መቀራመት ኢትዮጵያን ጭራሽ አይመለከታትም፤” ሲሉ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስትሩ የመሥሪያ ቤታቸውን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለፓርላማው ማክሰኞ ዕለት ሲያቀርቡ፣ ሰፋፊ መሬቶች ወስደው በግብርና ላይ ኢንቨስት እያደረጉ ስለሚገኙ የውጭ ባለሀብቶች ትክክለኛ ማብራሪያ እንዲሰጡ በተጠየቁበት ወቅት ነው ይህንን ያሉት፡፡

ማንነት (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም )

መስፍን ወልደ ማርያም

ኅዳር 21/2006
በ1996 ዓ.ም. የክህደት ቁልቁለት በሚል ጽሑፌ ውስጥ ‹‹ማንነት ምንድን ነው፤ በሚል ንዑስ ርእስ ስር ከገጽ 98 ጀምሮ በተቻለኝ መጠን አፍታትቻለሁ፤ የሪፖርተር ጋዜጠኛ ይህንን ለማንበብ ጊዜ አላገኘም፤ ወይም የተገለጠለት ዱሽ ቅንጫቢ በቅቶት ይሆናል፤ የምጠቅሰውም ለሱ ሳይሆን ለሌሎች ነው፡፡Prof. Mesfin Woldemariam : is an Ethiopian Human Rights activist and philosopher
በቅርቡ በፌስቡክ ላይ አንድ አውቀቱ ይሁን ጤንነቱ፣ ወይም ኪሱ የተቃወሰበት ሰው በትግርኛ ስለማንነት ጽፎ ነበር፤ ከዚህ በፊትም ጽፎ አስተሳሰቡ ሁሌም የተወላገደ በመሆኑ አልፌው ነበር፤ አሁን ደግሞ ሲጽፍና በአንዳንድ የሱ ቢጤዎች አበጀህ! አበጀህ! ሲባል ሳይ አደገኛነቱን ተገነዘብሁ፤ አንዱን ጎባጣ ሀሳብ ቶሎ ካላስተካከሉት ብዙ ጎባጦችን ያፈራል፤ የተጣራና ቀና የሆነ ሀሳብን ለመግለጽ በጣም ያስቸግራል፤ ማሰብ መጨነቅን፣ ማበጠርን፣ ማጣራትን ይጠይቃል፤ አፍ እንዳመጣ መልቀቅ ቀላል ነው፤ በተለይ የሚዳኝ ከሌለ!

“በዝዋይ የታሰሩት ባለቤቴ እዛው እስር ቤት መሞታቸውን ሕዝብ ይወቅልኝ” – ወ/ሮ ፈሪሃ አብድርሃማን

rest and peaceበዳዊት ሰለሞን
(ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ እንደዘገበው) አቶ አህመድ ነጃሽ ሐሰን በ2002 ዓ.ም በተደረገ አገር አቀፍ ምርጫ በድሬዳዋ ክልል የኦሮሞ ኮንግረስ/ መድረክን በመወከል ተወዳድረው ነበር፡፡የፖለቲካ ተሳትፏቸውን እንዲያቋርጡ በተለያዩ መንገዶች ሲነገራቸው ቢቆዩም በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ማሰማትና መደራጀት ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑን በመጥቀስ ሲከራከሩ መቆየታቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ፈሪሃ አብድርሃማን የሱፍ ለፍኖተ ነጻነት አስታውሰዋል፡፡
በ2003 የመንግስት የጸጥታ ሰዎች አቶ አህመድን በኦነግ አባልነት ተጠርጥረሃል በማለት ያስሯቸዋል፡፡የ57 አመቱ አህመድ ከታሰሩ በኋላ ለአራት ወራት ያህል በህይወት ይኖሩ ወይም ይሙቱ ለቤተሰብ ሳይታወቅ ከቆዩ በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበው በኦነግ አባልነት ተከሰው ይፈረድባቸዋል፡፡ፍርዳቸውን ተከትሎም ለምርመራ ከቆዩበት ማዕከላዊ ወደ ዝዋይ ወህኒ ቤት እንዲዘዋወሩ ይደረጋሉ፡፡
ከአቶ አህመድ ነጃሽ ያገኟትን አንድ ልጅ ለብቻቸው የማሰደግ ዱብ ዕዳ የወደቀባቸው ወይዘሮ ፈሪሃ ገቢያቸው በመቋረጡ ስራ ፍለጋ ወደ አረብ አገር ያቀናሉ፡፡በአረብ አገር ያለሙትን ማግኘት ባለመቻላቸው ወደ አገር ቤት ይመለሳሉ፡፡ካልተሳካው ስራ ፍለጋ መልስ ወይዘሮዋ ባለቤታቸውን ለመጠየቅ ወደ ዝዋይ ሲያመሩ የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች ባለቤታቸው ወደ ቃሊቲ መዘዋወራቸውን ይነግሯቸዋል፡፡

በጎንደር የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የቅስቀሳ ቡድን አባላት በፖሊስ ታሰሩ

እስካሁን 14 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በጎንደር የታሰሩ ሲሆን ከታሰሩት ውስጥ አራት ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች ይገኙበታል፣

1. ጌታነሀ ባልቻ (የድርጅት ጉዳዮች ሃላፊ)
2. ብርሃኑ ተ/ያሬድ (የሀዝብ ግንኙነት)
3. ዮናታል ተስፋዬ (የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ)
4. ይድነቃቸው ከበደ (የህግ አማካሪ)
ሁለት ሹፌሮች እና አንድ ፊልም አንሺም (Cameraman) ከታሳሪዎቹ ውስጥ ናቸው፣ በአሁኑ ስዓት ታሳሪዎቹ በወረዳ ሁለት ፖሊስ ጣብያ ሲገኙ ጌታነሀ ባልቻ (የድርጅት ጉዳዮች ሃላፊ) እና አግባው ሰጠኝ ወደ ጎንደር ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ተወስደዋል።