ተስፋዬ ዘነበ(ኖርዌይ በርገን)
በዚች አለም በሕዝቦቻቸው ላይ የሚፈነጩ አምባገነኖችን ለማስወገድ የሚደረጉ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ሁሉ የወያኔ ዘረኛችን ለምን ሲያስደነብራቸውና በፍርሃት ሲያሸማቅቃቸው እንደሚኖር የሁሉም ሰው ጥያቄ ነው፡፡ የህውሃት ዘረኛ ቡድን በሕዝብና በሃገር ላይ የሚያደርሰው መጠነ ሰፊ ጥቃት ወይም ውድመት በተለያየ መንገድ ሕዝቡ ቅሬታውን ቢያሰማም እራሱ ለፈጠረው ዘርፈ ብዙ ችግር መፍትሄ ከመሻት ይልቅ የሕዝቡን ብሶት ለማዳፈን ሀላፊነት የጎደለው ተግባራትን እየፈፀመ ሃገርን የመበተን ስራውን ቀጥሎበታል፡፡
በአዋጅ የተደነገጉ የሕዝብን አሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የመደራጀትና የመሰብሰብ እንዲሁም ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን እየሸረሸሩና አዋጅን በተራ መመሪያ እየሻሩ የስቃይ ቀንበሩን ያከብዱበታል ፡፡በየትኛውም ሁኔታ ማለትም የሰብአዊ መብቱ የተረገጠውን፣ የሃገሬ ጉዳይ ያገባኛል ስላለ እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየታየ የሚሰቃየውን የነፃነት ታጋይ፣ በስርዓቱ ብልሹና የተዝረከረከ አሰራር በኑሮ ውድነት እየማቀቀ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ለጥያቄው ተገቢውን መልስ ወይ መፈትሄ ከመስጠት ይልቅ በተራ ካድሬያዊ ዲስኩር ከላይ ለዘረኛው ስርዓት ቃል አቀባይ ከሆነው ጠ/ሚ ተብዬው እስከ ልማታዊ ጋዜጠኛ ነን እስከሚሉት ድረስ በርሃብ ለጠወለገው ምስኪን ሕዝብ ጥጋብን፣ በገዛ ሃገሩ ፍትህ አጥቶ ለሚሰቃየው ፍትሃዊነትን እንዲሁም ሰብአዊ መብቱ ተገፎ ነፃነቱን ለተነጠቀው ሕዝብ ዴሞክራሲን ነጋ ጠባ ይሰብኩታል፡፡
Share to Facebook