Wednesday, March 19, 2014

በነፃነት ቀን ነፃነት ማጣት!

ይድነቃቸው ከበደ

Young semayawi party female activists
ሰብአዊ መብቶች እያንዳንዳችን ሰው በመሆናችን ብቻ የሚገቡን ከሰብአዊነታችን ተለይተው ሊታዩ የማያችሉ መብቶች ናቸው፡፡ መንግስታት እነዚህን በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጣቸውን ሰብአዊ መብቶች ለማክበር ለማስከበርና ለማሟላት በቀዳሚነት ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በዚህም መሰረት ኃላፊነት ከፈረሙ ቀደምት አገራት መካከል ኢትዩጵያ ትገኝበታላች፡፡

Thursday, March 13, 2014

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ግምገማ

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ ውይይት ጄኔቭ ስዊትዘርላንድ ውስጥ ዛሬ ተካሂዷል ። የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ባዘጋጁት በዚሁ ውይይት ላይ በኢትዮጵያ ይፈፀማሉ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በዝርዝር ቀርበዋል።

መንግሥት የሰብዓዊ መብት አያያዙን እንዲያሻሽል ያግዛሉ የተባሉ ሃሳቦችም ተሰንዝረዋል ። በስበሰባው ላይ የተካፈሉት የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች ለተሰነዘሩት ወቀሳዎች የበኩላቸውን መልስ መስጠታቸው ተገልጿል ።በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ያተኮረው ውይይት ዛሬ የተደረገው ከ25,ተኛው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጉባኤ ጎን ለጎን ነው ። የውይይቱ ዓላማም በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ ዝርዝር ዘገባ ለተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በመጪው ግንቦት ከመቅረቡ አስቀድሞ ስለሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው ። ስበስባውን ካዘጋጁት ዓለምዓቀፍ ድርጅቶች አንዱ መቀመጫውን ጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ያደረገው ሲቪኩስ የተባለው ድርጅት የፖሊሲና የጥብቅና ጉዳዮች መኮንን ቶር ሆድንፌልድ ስብሰባው በተለይ በሶስት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መወያየቱን ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።

Thursday, March 6, 2014

(ሰበር ዜና) መርዝ ተሰጥቷቸዋል የተባሉት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ኦቦ ዓለማየሁ አቶምሳ አረፉ

'

ዘ-ሐበሻ እንደዘገበው መርዝ ተሰጥቷቸው ነው ለዚህ የበቁት የተባሉት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ኦቦ ዓለማየሁ አቶምሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ለህክምና ብዙ ገንዘብ ወጣባቸው በሚል ሕገወጥ በሆነ መንገድ ከስልጣናቸው እርሳቸው ባላወቁበት በፈቃዳቸው እንደለቀቁ ተደርጎ የተነገረባቸው የኦሮሚያው ክልል ፕረዚዳንት ኦቦ አለማየሁ አቶምሳ በተሰጣቸው የተመረዘ ምግብ ምክንያት የጀመራቸው በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ ጸንቶ በተደጋጋሚ በተለያዩ ሃገራት ህክምናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን ዛሬ ግን በባንኮክ ታይላድ ለህክምና በሄዱበት ሆስፒታል ሕይወታቸው አልፏል።

Wednesday, February 26, 2014

እኛና “እነርሱ”! (ተመስገን ደሳለኝ)

‹‹…የውሳኔ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ተጠናቀቀ፡፡ የባሕር መዝገቡም ተዘጋ፡፡ …ቀፋፊ ምሽት ነበር፡፡
በእያንዳንዳችንም ፊት ፈገግታ አይታይም፡፡ ከአዳራሹ ሳንርቅ ከራሳችን ጋር ብቻ እየተነጋገርን
በሃሳብም ርቀን እየሄድን አመሸን፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ወደ አዳራሹ እንድንገባ ተነገረን፡፡

Tuesday, February 25, 2014

“ግብረሰዶማውያን ከተፈጥሮ ውጪና አጸያፊ ናቸው”

ዑጋንዳ የጸረ ግብረሰዶማውያን ሕግ አጸደቀች!

musevini

የዑጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ “አከራካሪ” ሲባል የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊ ህግ በፊርማቸው አጸደቁ፡፡ ግብረሰዶማውያንን “ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ” እና “አጸያፊ” ሲሉ ገልጸዋቸዋል፡፡ ግብረሰዶማዊነት በምዕራቡ ዓለም አማካኝነት ወደ አፍሪካ እየተስፋፋ የመጣ ነው ብለዋል፡፡

Saturday, February 22, 2014

“የረዳት አብራሪ ኃይለመድን እህት ታስራለች፣ ቤተሰቦቹ በግዳጅ ሊናገሩ ነው”


Tensay Abera (Co-pilot Hailemedhin's sister)
Tensay Abera (Co-pilot Hailemedhin’s sister)
ቦይንግ 767-300 ጄኔቭ አርፎ፣ መንገደኞቹ ወደየመድረሻቸው ተጉዘው አውሮፕላኑም ወደ ሀገሩ ተመልሷል። ነገር ግን የወሬው በረራ ማረፊያ ቦታ እንዳጣ ነው። የኃይለመድን ጉዳይ በየቦታው የመወያያ ርዕስ እንደሆነ ነው፣ ይቀጥላልም። የግምት ወሬዎች እዚህም-እዚያም እየተረጩ ነው። በተለይ የመንግስት ካድሬዎችን “ቢዚ” አድርጓቸዋል። በምን መልኩ የድራማውን ድርሰት እንደሚጽፉ ግራ ግብት ብሏቸዋል የአዕምሮ ሕመምተኛ ሊሉት ፈለጉ …ከዚያ ትዝ ሲላቸው አዕምሮ ታማሚ ሆኖ አየር መንገዱ መንግስት እንዴት እንዲያበር ፈቀደ፣ ለአብራሪዎቹ ምርመራ አያደርግም ወይ የሚሉት ጥያቄዎች ሊከተሉ ሆነ። ቀጥለው አባትዬው እቁብ ሰብሳቢ፣ አራጣ አበዳሪ… ተደርገው ተሳሉ። እእ..ደራሲዎቹ የቤተሰብ ጣጣ መሪ ተዋናዩ ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ አልታይ አላቸው። የኃይለመድን እህት ሆነው የተዋቀረ እና የተዋቃ ጽሑፍ በፌስቡክ ላይ አከታተለው ጻፉ…በርግጥ ይሄኛው የወጭ የዜና አውታሮች ዘንድ ደርሶላቸው ተራግቦላቸዋል። ተአማኒነት ባያገኝም።

Thursday, February 20, 2014

በሃገሪቱ የተነሰራፋው ዘረኝነት፣ የደህንነት ሥጋትና አድልዎ አውሮፕላን እንዲጠለፍ አድርጓል

በሃገሪቱ የተንሰራፋውን የደህንነት ስጋት በመልካም አስተዳደር እና በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አድልዎ ተከትሎ የተደረገው የአይሮፕላን ጠለፋ ህዝቦችበገዛ አገራቸው በደህንነት ላይ ምን ያህል ስጋት እንዳጠላበት እና በመኖር ህልውናቸው ላይ ኢትዮጵያውያን የስርአቱ ፖሊሲዎች እያሸማቀቋቸውእንደሚገኙ አለም ካለፈው ጊዘ በተሻለ እውነታውን ፍንትው አድርጎ እየመሰከረ ነው።

የሕወሓት መራሹ ጁንታ ወደ ስልጣን በጠበንጃ ሃይል ከመጣ ጀምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ የተደነገጉ የሰብኣዊ መብት ህጎችን ካለምንም ማርቅርቅ እናድካም ከሌሎች በመገልበጥ በወረቀት ላይ ከማስፈሩም በተጨማሪ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በአለም ላይ የሰው አገር ህግን እና አለማቀፍ ድንጋጌንከሃገራችን ሁኔታ ጋር ሳይገናዘቡ በስፋት በደመነፍስ ለፍጆታ የተጻፈበት ሃገር ኢትዮጵያ ብቻ ሲሆን በየትኛውም አለም ሃገራት ያልተከሰተ የአለምአቀፍ ህጎችን ግልባጭ በከፊል በህገመንግስት እንዲሁም የገዢ ፓርቲን የፖለቲካ ፕሮግራም በከፊል ደባልቆ በጋር እንደ አውራ ህግ የወጣባት ሃገርብትኖር ኢትዮጵያ ብቻ ናት::ኢትዮጵያ በታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የመብቶች ሕጋዊነት በተጨበጨበለት ሁኔታ እና ይህ በማይባል ደረጃየተደነገጉባት አገር ነች፡፡ እንግዲህ ይህ ሆኖ እያለ ነው በአገሪቱ የመብቶች ጥሰት ጉዳይ ከአገሪቱ ብሔራዊ አነታራኪ ፖለቲካዊ አጀንዳነት አልፎ ዓለምአቀፍ አጀንዳ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ጥላቻ በፈጠረው ፍርሃት ብቻ የሃገሪቱን ህጎች ዜጎች ለመጥለፍ እያዋሉት ነው::