Monday, November 18, 2013
በገዛ ሀገራችን መንግስታዊ ሽፍቶችም ሆነ በተሰደዱበት ሀገር ሰዎች መደፈሩ ፣ መዋረዱ መቼ ይሆን የሚቆመው ?
“… በየምሽቱ ሁላችንንም ወደ ምርመራ ክፍል ይወስዱናል ፡፡ ከዚያም እያንዳችንን ለያይተው ይገርፉናል ፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ስጠራ ሶስት ወንዶች በክፍል ውስጥ ይጠብቁኝ ነበር ፡፡ ወዲያዉኑ ሶስቱም በየተራ እየተፈራረቁ ደፈሩኝ ፡፡ ወደነበርንበት ጉድጓድ ስመለስ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃየሁ ነበር ፡፡ አሁን ድረስ ህክምና ማግኘት አልቻልኩም ፡፡
Sunday, November 17, 2013
ይድረስ ለኢትዮጵያ ፖሊሶችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት
በየቦታው ተበትናችሁ ለአገር የሚበጅ ስራ እየሰራን ነው ለምትሉ የፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሙሉ። እንዴት ከርማችሁልኛል? እንደ አገር ልጅ ብናፍቃችሁም እንኳ የናንተ እንጀራና የኔ ኑሮ አልገጥም ብሎ ካጠገባችሁ ከራቅሁ አመታት አልፈዋል። ብዙ ሰዎች የሰው ልብ ያላችሁ፣ አዛኝ አንጀት ያላችሁ መሆናችሁን ይጠራጠሩ ይሆናል። እኔ ግን እንደሱ አላስብም ብዙዎቻችሁ ድህነት በግዱ ገፍትሮ እዚህ ውስጥ እንደ ጨመራችሁ አውቃለሁ። ምክንያቱም ብዙ ጓደኞቼ የሚላስ የሚቀመስ ሲያጡ፣ እንደኔ ለመሰደድ መድፈር ሲያቅታችውና ቢፈልጉም እንኳን ሱዳንና ኬንያ የምታደርስ ገንዘብ በማጣታቸው እንጀራ ብለው የገቡ ብዙ እንዳሉ አውቃለሁ። እነዚህ በሙሉ የድሀ ልጆች ቤት ተቀምጦ በረሀብ ከመሞት የምችለውን አድርጌ እኖራለሁ ብለው እንደሚኖሩ አውቃለሁና በተለይ እናንተ ከዚህ የመከራ ማጥ እንድትወጡልኝ አምላኬን መለመን አልተውኩም። ግምገማ ፈርታችሁ የራሳችሁን ወገን በዱላ መጨፍጨፍ እንዴት እንደሚሰማ አውቀዋለሁ። ባዶ እጁን ያለን ሰውማ በጥይት መግደል የባሰ ነው። በተለይ ያልበላን ሆድ ተርቦ የሚያውቅ ሆድ እንዲህ ያለውን ግፍ በደንብ ያውቃል። ዞሮ ዞር የሚመታውም ሆነ የሚገደለው የናንተ ዘመድ እንኳን ባይሆን አንዱ ቦታ ተመድቦ የሚሰራ የባልደረባችሁ ዘመድ መሆኑ መች ይቀራል።
Friday, November 15, 2013
ህወሃት ፈቀደ እኛም ተዋረድን ,መንግሥት አልባ አገር!
የብዙ ሺህ ዘመናት የመንግሥትነት ታሪክ የነበራት አገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ መንግሥት አልባ አገር ናት ብሎ ደፍሮ መናገር የሚቻልበት ወቅት ላይ ደርሰናል።
ኢትዮጵያ የፀረ ቅኝ አገዛዝ ትግል ፋና ወጊና የበርካታ ጥቁር ሕዝብ የነፃነት ትግል ማነቃቂያ ምሳሌ ሆና ቆይታለች፤ ህዝቧም ክብር ያለው ነበር። አሁን ባለንበት ዘመን ግን ኢትዮጵያዊነት የሚያሳፍር የኢትዮጵያውያንም ዋጋ ከእንስሳት ይልቅ የወረደበት ወቅት ላይ እንገኛለን።
መቋጫ ያጠው የወገኖቻችን ስቃይ እና ሞት በሳውዲ አረቢያ ፡አሁንም ቀጥሏል !
ትላንት አመሻሹ ላይ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፍሃ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገርሽቶ በዋለው ተቃውሞ የተጓዳ የሞተ ባይኖርም ኢትዮጵያውያኑ ድምጻቸውን ከፍ አድረገው አንድነን አንድነን … መብታችን ይከበር ….እኛም ሃገር አለን ወዘተ… በሚል መፈክር ታጅበው ብሷታቸውን ሲያሰሙ መዋላቸውን የሚገልጹ የአይን እማኞች የሳውዲ የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞውን ለመብተን በከፈቱት ቶክስ ይሰማ በነብረው የጥይት ድምጽ አካባቢውን ወደ ጦርነት አውድማ ለውጦት ማምሸቱን የገልጻሉ።
ይህንንም ተከትሎ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ተጨማሪ ልዩ ፈጥኖ ደራሽ፡ ኮማንዶዎች ቦታው በመድረስ ተቃውሞውን መግታት ተችሎል ብለዋል ። እንዚህ ምንጮች ትላንት ተቀስቅሷ በነበረው ሁከት ጥቂት ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መደሱን ገልጸዋል። ሰምኑን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በውጭ፡ሃገር ነዋሪዎች ላይ ያወጣው ህግ የግዜ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች በኢትዮጵያውያኑ ላይ እየወስዱ ባሉት የተናጥል እርምጃ አያሌ ወገኖቻችን ወደ ሃገሩ ለመምለስ ከየመኖሪያ ቤቱ ነቅሎ አደባባይ ቢወጣም ወደ ሃገር መግባት የሚያስችሉት ነግሮች በመንግስ በኩል ባለመኖሩ ከእልቂት ተርፈው ወደ እስርቤት የተጓጓዙ ከ 20 ሺህ የሚበልጡ ወገኖቻችን በምግብ ወሃ እና የመጸዳጃ ቦታ እጦት እይተሰቃዩ እንደሚገኙ ተግልጾል።
ይህንንም ተከትሎ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ተጨማሪ ልዩ ፈጥኖ ደራሽ፡ ኮማንዶዎች ቦታው በመድረስ ተቃውሞውን መግታት ተችሎል ብለዋል ። እንዚህ ምንጮች ትላንት ተቀስቅሷ በነበረው ሁከት ጥቂት ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መደሱን ገልጸዋል። ሰምኑን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በውጭ፡ሃገር ነዋሪዎች ላይ ያወጣው ህግ የግዜ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች በኢትዮጵያውያኑ ላይ እየወስዱ ባሉት የተናጥል እርምጃ አያሌ ወገኖቻችን ወደ ሃገሩ ለመምለስ ከየመኖሪያ ቤቱ ነቅሎ አደባባይ ቢወጣም ወደ ሃገር መግባት የሚያስችሉት ነግሮች በመንግስ በኩል ባለመኖሩ ከእልቂት ተርፈው ወደ እስርቤት የተጓጓዙ ከ 20 ሺህ የሚበልጡ ወገኖቻችን በምግብ ወሃ እና የመጸዳጃ ቦታ እጦት እይተሰቃዩ እንደሚገኙ ተግልጾል።
Thursday, November 14, 2013
ዳግማዊ ሆሎኮስት በኢትዮጵያውያን ላይ? ከዲያቆን ዓባይነህ ካሤ
ኢትዮጵያውያን ደማቸው የዐረብን አስፋልት አቀለመው፡፡ ባንዲራውን በራሱ ላይ ሸብ ያደረገው የእማማዬ ልጅ የእኔ ጀግና ማንነቱን እየተናገረ በአናቱ ላይ የወረደውን የድንጋዩን ናዳ በሀገሩ ፍቅር ተቋቁሞ በክብር አሸለበ፡፡ ለእርሱ ከዚህ በላይ ሌላ ድል አልነበረምና፡፡ ድንጋዩስ እርሱን አሳርፎታል፡፡ ነፍሱን ይማርልን እንጂ! ባንዲራችን ግን እንደተመታች እንደታመመች ናት፡፡ እውን ይኽ የሆነው በእኛ ላይ ነው?

ይህቺ ባንዲራ እኮ ጨርቅ አይደለችም፡፡ ያ በሳኡዲ መሬት ተወግሮ የሞተው ወንድሜ የኮራባት በሞቱ ጊዜ የለበሳት የክብሩ፣ የማንነቱ መገለጫ እንጂ፡፡ ማንም ባይደርስለት ባንዲራው ነበረችለት፡፡ በእርሷ ተጽናና፡፡ ሞተ አልለውም መሰከረ እንጂ፡፡ ባንዲራ ለብሶ መከራን መጋፈጥ የሰማእታት ወግ ነው፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)
