Wednesday, March 19, 2014

በነፃነት ቀን ነፃነት ማጣት!

ይድነቃቸው ከበደ

Young semayawi party female activists
ሰብአዊ መብቶች እያንዳንዳችን ሰው በመሆናችን ብቻ የሚገቡን ከሰብአዊነታችን ተለይተው ሊታዩ የማያችሉ መብቶች ናቸው፡፡ መንግስታት እነዚህን በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጣቸውን ሰብአዊ መብቶች ለማክበር ለማስከበርና ለማሟላት በቀዳሚነት ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በዚህም መሰረት ኃላፊነት ከፈረሙ ቀደምት አገራት መካከል ኢትዩጵያ ትገኝበታላች፡፡

Thursday, March 13, 2014

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ግምገማ

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ ውይይት ጄኔቭ ስዊትዘርላንድ ውስጥ ዛሬ ተካሂዷል ። የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ባዘጋጁት በዚሁ ውይይት ላይ በኢትዮጵያ ይፈፀማሉ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በዝርዝር ቀርበዋል።

መንግሥት የሰብዓዊ መብት አያያዙን እንዲያሻሽል ያግዛሉ የተባሉ ሃሳቦችም ተሰንዝረዋል ። በስበሰባው ላይ የተካፈሉት የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች ለተሰነዘሩት ወቀሳዎች የበኩላቸውን መልስ መስጠታቸው ተገልጿል ።በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ያተኮረው ውይይት ዛሬ የተደረገው ከ25,ተኛው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጉባኤ ጎን ለጎን ነው ። የውይይቱ ዓላማም በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ ዝርዝር ዘገባ ለተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በመጪው ግንቦት ከመቅረቡ አስቀድሞ ስለሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው ። ስበስባውን ካዘጋጁት ዓለምዓቀፍ ድርጅቶች አንዱ መቀመጫውን ጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ያደረገው ሲቪኩስ የተባለው ድርጅት የፖሊሲና የጥብቅና ጉዳዮች መኮንን ቶር ሆድንፌልድ ስብሰባው በተለይ በሶስት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መወያየቱን ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።

Thursday, March 6, 2014

(ሰበር ዜና) መርዝ ተሰጥቷቸዋል የተባሉት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ኦቦ ዓለማየሁ አቶምሳ አረፉ

'

ዘ-ሐበሻ እንደዘገበው መርዝ ተሰጥቷቸው ነው ለዚህ የበቁት የተባሉት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ኦቦ ዓለማየሁ አቶምሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ለህክምና ብዙ ገንዘብ ወጣባቸው በሚል ሕገወጥ በሆነ መንገድ ከስልጣናቸው እርሳቸው ባላወቁበት በፈቃዳቸው እንደለቀቁ ተደርጎ የተነገረባቸው የኦሮሚያው ክልል ፕረዚዳንት ኦቦ አለማየሁ አቶምሳ በተሰጣቸው የተመረዘ ምግብ ምክንያት የጀመራቸው በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ ጸንቶ በተደጋጋሚ በተለያዩ ሃገራት ህክምናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን ዛሬ ግን በባንኮክ ታይላድ ለህክምና በሄዱበት ሆስፒታል ሕይወታቸው አልፏል።